Wednesday, December 6, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
- Advertisement -

ፌርማታ ፅሁፎች

የውሳኔ ሰዓት

ትኩስ ፅሁፎች

‹‹በአንድ የክረምት ወቅት አስታውሳለሁ አባቴ የማገዶ እንጨት ሲፈልግ አንድ የሞተ ዛፍ ያገኝና ይቆርጠዋል፡፡ ፀደይ ሲመጣ በተቆረጠው ዛፍ ግንድ ዙሪያ ማቆጥቆጡን አየ፡፡ እንዲህም አለኝ፣ ‹‹ዛፉ እንደሞተ ቆጥሬ ነበር፣ በክረምቱ ቅጠሎቹ ረግፈው ነበር፣ ቅርንጫፎቹ ሁሉ ከቅዝቃዜው የተነሳ ጭራሮ ሆነው ደርቀው በዛፉ ላይ ሕይወት የሚባል ነገር አይታይም ነበር፡፡ አሁን ግን በዋናው ሥር ላይ እስካሁን ድረስ ሕይወት አያለሁ፤›› አለ፡፡ ከዚያ ቀና ብሎ አየኝና እንዲህ አለኝ፣ ‹‹ቦብ፣ ይህ አስፈላጊ ትምህርት እንዳትረሳ፣ በክረምት ወቅት ዛፍን አትቁረጥ፤ ነገሮች በከፉም ሰዓት አሉታዊ ውሳኔ አትውሰድ፤ ልብህ በወደቀበት ሰዓት በመልካም መንፈስ ውስጥ በሌለህበት ጊዜ አስፈላጊ ውሳኔዎችን አትወስን፡፡ ጠብቅ፤ ታገስ፡፡ ማዕበሉ ያልፋል፡፡ ፀደይም ይመጣልና›› አለኝ፡፡

የውሳኔ ሰዓት | Ethiopian Reporter | ሪፖርተር

  • ኃይል ከበደ ‹‹ጉርሻ እና ፌሽታ›› (2006)
- Advertisement -
- Advertisement -

ተጨማሪ ለማንበብ

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች