Sunday, December 10, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊበአገር ቤት ለመከበር የዘገየው የዓለም የቱሪዝም ቀን

በአገር ቤት ለመከበር የዘገየው የዓለም የቱሪዝም ቀን

ቀን:

የተባበሩት መንግሥታት የዓለም ቱሪዝም ድርጅት (ዓቱድ)፣ ከ1973 ዓ.ም. (እ.ኤ.አ. 1980) ጀምሮ ‹ሴብቴምበር 27 ቀን› ዓለም አቀፍ የቱሪዝም ቀንን በየዓመቱ እያከበረና እያስከበረ ይገኛል፡፡ ይህ ቀን የተመረጠው የተቋሙ የዓቱድ ሕግጋት የፀደቁበት ቀን በመሆኑ ሲሆን፣ ሕግጋቱ ተቀባይነት ማግኘታቸውም በዓለም አቀፍ ቱሪዝም ውስጥ እንደ አንድ ምዕራፍ ይቆጠራል ይላል።

የቱሪዝም ቀን በኢትዮጵያ አቆጣጠር ሦስቱን ዓመት መስከረም 17 ላይ ሲውል፣ በአራተኛው ዓመት ጳጉሜን 6 ስትሆን መስከረም 16 ላይ ይወድቃል፡፡ በዚህም መሠረት ዘንድሮ የቱሪዝም ቀኑ መስከረም 16 ቀን 2016 ዓ.ም. ከኢትዮጵያ በስተቀር በተለያዩ አገሮች ተከብሮ ውሏል፡፡

የክብረ ቀኑ ዓላማ፣ ቱሪዝም በዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ውስጥ ስላለው ሚና ግንዛቤን ለማሳደግና ያለውን ማኅበራዊ፣ ባህላዊ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ እሴትን ለማጉላት መሆኑ ይገለጻል።

ዘንድሮ በዓሉ ‹‹ቱሪዝምና አረንጓዴ ኢንቨስትመንት›› በሚል መሪ ቃል መስከረም 16 ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ የተከበረው፣ መሰንበቻውን የጌድኦ ባህላዊ መልክዓ ምድርና የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ በዩኔስኮ የዓለም ቅርስ ኮሚቴ አማካይነት በተመዘገቡባት በሳዑዲ ዓረቢያ ነው፡፡

ክብረ ቀኑን አስመልክቶ ‹‹ቱሪዝም ለኢኮኖሚም ሆነ ለኅብረተሰቡ ከዚህ የበለጠ አስፈላጊ ሆኖ አያውቅም፤›› በማለት መልዕክት ያስተላለፉት የዓለም ቱሪዝም ድርጅት ዋና ጸሐፊ ዙብራ ፖሎካሽቪሉ፣ በዓለም ቱሪዝም ቀን አጋጣሚ ቱሪዝምን ለዕድገት ለማንቀሳቀስ ያለውን አቅም ማሳደግ እንዲሁም ዕድገቱ ሁሉንም የሚያቅፍ እንዲሆን መትጋት ይገባል ብለዋል፡፡

በኢትዮጵያ ለወትሮው ቀኑ በባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር፣ በመቀጠልም በቱሪዝም ሚኒስቴር አማካይነት በተለያዩ ዝግጅቶች በየክልሉ እየተዞረ ከዋዜማው ጀምሮ ይከበር እንደነበረ ይታወሳል፡፡

የአዲስ አበባ ባህል ኪነ ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ‹‹መስከረም 17 ለሚከበረው የቱሪዝም ቀን እንኳን አደረሳችሁ›› የሚል በሞባይል ስልክ ባጭር መልዕክት ያስተላለፈ ሲሆን፣ መስከረም 21 ቀን 2016 ዓ.ም. ቢሮው በሰጠው መግለጫው ደግሞ፣ የመዲናዋን የቱሪስት መዳረሻ ሥፍራዎችን በስፋት የማስተዋወቅ ሥራ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን እየተሠራ መሆኑንም አስታውቋል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የፀደቀውን ‹‹አዲስ አበባ አፍሪካዊቷ መልሕቅ›› የተሰኘውን መለያ መሠረት በማድረግ የመዲናዋን የቱሪዝም ዘርፍ ለማስተዋወቅ እየተሠራ መሆኑን ምክትል ቢሮ ኃላፊው አቶ ሃፍታይ ገብረ እግዚአብሔር ገልጸዋል።

የዓለም የቱሪዝም ቀንን ምክንያት በማድረግ ‹‹ሕይወትን ማዳን የሚጀምረው ከአንድ የደም ጠብታ ነው›› በሚል መሪ ቃል በአዲስ አበባ ሙዚየም የደም ልገሳ መርሐ ግብር አከናውኗል።

በተያያዘ ዜና የቱሪዝም ማሠልጠኛ ኢንስቲትዩት የቱሪዝም ቀንን በስልጤ ዞን በተለያዩ መርሐ ግብሮች ሲያከብር፣ እስካሁን ጥቅም ላይ ያልዋሉ የቱሪስት መዳረሻዎችን በጥናት እየለየ መሆኑን አስታውቋል። በስልጤ ዞን ከተጎበኙት መስህቦች መካከል እንደ ሐረ ሸይጣን ሐይቅ፣ ሙጎ እንደሚገኙበት ተቋሙ በትስስር ገጹ ጠቁሟል፡፡

የቱሪዝም ሚኒስቴርም  የዓለም  የቱሪዝም ቀን ምክንያት በማድረግ፣ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ለቱሪስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ለሆቴል፣ ለፔንስዮንና ለምግብ ቤቶች ባለቤቶች እንዲሁም ሥራ አስኪያጆች የቱሪስት አቀባበልና አገልግሎት አሰጣጥ በሚመለከት ሥልጠና መስጠቱን የክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ አውስቷል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ለሰው ልጅ መብት መከበር ስናወራ 75 ዓመት ሞላን!

በገነት ዓለሙ ዓለም ስለሰብዓዊ መብቶች ሲያወራ፣ ሲምል፣ ሲገዘት፣ ሲፈጠም፣ ቃል...

ካልተማከለ የካፒታል ገበያ ወደ ዘመናዊና የተደራጀ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ

በእሱፈቃድ ተረፈ በአገራችን የካፒታል ገበያ አዋጅ መውጣትን ተከትሎ የተማከለ የሰነደ...

ለማይቀረው ምክክርና ድርድር እንዘጋጅ

በያሲን ባህሩ  የዘመናዊት ኢትዮጵያ ፖለቲካ ውዝግብ በትንሹ የአንድ ምዕተ ዓመት...

ደንብ አስከባሪዎች ደንብ ያክብሩ!

በአዲስ አበባ ከተማ ደንብ አስከባሪዎች፣ ሌሎች የፀጥታ አካላት፣ እንዲሁም...