Monday, December 11, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
- Advertisement -

ፌርማታ ፅሁፎች

የስብሐት ተረቶች

ትኩስ ፅሁፎች

አንድ ቀን ስብሐት ገ/እግዚአብሔር ለአማጭነት ሽምግልና ይላካል። የላኩት ልጆች መጋባት ፈልገው የሴቷ አባት እንዲፈቅዱ ለወግ ያህል ሽምግልና ከሌሎች ሽማግሌዎች ጋር አጩት። ስብሐት “ሆድ ሲያውቅ ዶሮ ማታ” እንደሆነ ገብቶታልና በሽምግልና የሚጠፋው ጊዜና ጉልበት ከወዲሁ አድክሞታል። ሽማግሌዎቹ ልጅቷ ቤት ደርሰው በር ተከፍቶላቸው እንደገቡ አባቷ ይመጣሉ። ተጨባብጠው አረፍ እንዳሉ ስብሐት ተሽቀዳድሞ

“የመጣነው ልጅዎትን አንድ የእኛ ልጅ ጠይቆ ነው። እዚህ ውስጥ እርስዎም ሆኑ እኛ ምንም መብት የለንም። እምቢ ቢሉ እንኳን እነሱ ለመጋባት ቆርጠው ጨርሰዋል። ስለዚህ ይጋባሉ። አሁን በከንቱ ከመታከት ደስ የሚለንን ሌላ ጨዋታ እየተጫወትን እንቆይ። ምን ይመስልዎታል” አለ። አባትየው ስብሐትን ያውቁት ኖሮ ስቀው “ጥሩ” አሉና ሌላ ጉዳይ ሲጨዋወቱ ቆዩ።

* * *

ስብሐት ጫት ሲቅም የደረሰ አንድ ወጣት ይመክረዋል። “ጋሽ ስብሐት አይቃሙ። መቃም ሱስ ያስይዛል። እኔ አልቅምም” ስብሐት ዝም ይልና ሲጋራ ይለኩሳል። ወጣቱ ምክሩን ይቀጥላል። ጋሽ ስብሐት አያጭሱ። ማጨስ ሱስ ያስይዛል። እኔ አላጨስም። ስብሐት ዝም ይልና ቡና ያዛል። “ትጠጣለህ?” ሲል ወጣቱን ጋበዘው። “ቡና አልጠጣም ሱስ ያስይዛል” ወጣቱ መለሰ። ስብሐት ዝም ይለዋል። በመጨረሻ ሁሉም አልቆ መጠጣት ሲጀምር ወጣቱ “መጠጥ ሱስ ያስይዛል፤ አይጠጡ። እኔ ሱስ እንዳይዘኝ አልጠጣም” አለው። ስብሐት ገረፍ አድርጐ አየውና “ከሱስ አላመለጥክም፣ ሱስ የመፍራት ሱስ አለብህ” አለው።

ዓለማየሁ ገላጋይ ‹‹ስብሐት ገብረእግዚአብሔር ሕይወትና ክህሎት››

- Advertisement -
- Advertisement -

ተጨማሪ ለማንበብ

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች