በይፋዊ መጠርያው፣ እውነተኛው የክርስቶስ ኢየሱስ መስቀል የተገኘበት (Finding of the True Cross of Christ) ክብረ በዓል፣ መስከረም 17 ቀን 2016 ዓ.ም. በኢትዮጵያና በባህር ማዶ በሚገኙ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያናት ተከብሯል፡፡ በተለይ በአዲስ አበባ ከተማ መስቀል አደባባይ የበዓሉ መገለጫው ደመራ፣ በቤተ ክርስቲያን የሥርዓተ አምልኮ የዘመን አቆጣጠር፣ የመስከረም 17 መነሻ በሆነው መስከረም 16 ቀን፣ ከምሽቱ 12፡30 የተለኮሰበት ሲሆን፣ ክርስቲያናዊ መርሐ ግብሩም ፕሬዚዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ በተገኙበት በክብር ተከናውኗል፡፡ በዕለቱ ከተገኙት ታዳሚያን መካከል የሩሲያ ኦርቶዶክስ ተማሪዎች የክብረ መስቀል ዝማሬያቸውን አሰምተዋል፡፡ ፎቶዎቹ ያከባበሩን ከፊል ገጽታ ያሳያሉ፡፡
- ፎቶ መስፍን ሰሎሞን