Monday, December 11, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናበትግራይ ክልል የሐዘን ቀን እንደሚታወጅ ጊዜያዊ አስተዳደሩ አስታወቀ

በትግራይ ክልል የሐዘን ቀን እንደሚታወጅ ጊዜያዊ አስተዳደሩ አስታወቀ

ቀን:

በዳንኤል ንጉሤ

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ በሰሜኑ ጦርነት ምክንያት ሕይወታቸውን ላጡ ዜጎች ሰሞኑን የሐዘን ቀን እንደሚታወጅ አስታወቁ፡፡ ፕሬዚዳንቱ ይህንን ያስታወቁት የመስቀል ደመራ በዓል በመቀሌ ከተማ ጮምአ በሚባለው ሥፍራ ሲከበር ባደረጉት ንግግር ነው፡፡

‹‹ይህ አንፃራዊ ሰላም እንዲገኝ ሺዎች መስዋዕትነት ከፍለዋል፤›› ያሉት አቶ ጌታቸው፣ ‹‹ይህንን በዓል የምናከብረው የትግራይን ህልውና ለማረጋገጥ ሕይወታቸውን የከፈሉ የክልሉ ሰማዕታት፣ ክብራቸውን በሚመጥን መንገድ ለመዘከር በምንዘጋጅበት ወቅት ነው፤›› ብለዋል።

በተያያዘ ዜና ሰሞኑን በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች በጦርነቱ ሕይወታቸውን ያጡ የሟች ቤተሰቦች ማርዳት መጀመሩን ለማወቅ ተችሏል፡፡

አቶ ጌታቸው፣ ‹‹የመስቀል በዓልን በትግራይ ከሦስት ዓመታት በኋላ አንፃራዊ ሰላም አግኝተን የምናከብረው ቢሆንም፣ አሁንም በችግር፣ በጭንቀት፣ በስደት፣ በመፈናቀልና በረሃብ ውስጥ ያሉ ዜጎቻችንን በማሰብ የምናከብረው በዓል መሆኑን ልንረሳ አይገባም፤›› ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ለሁለት ዓመት ያህል በዘለቀው ጦርነት የተከፈለው መስዋዕትነት የትግራይ ክልል ህልውናን ለማረጋገጥ እንደሆነ የተናገሩት አቶ ጌታቸው፣ የተደረገው ትግል የትግራይን ባህል፣ ቋንቋና ማንነት አስጠብቆ ለመቀጠል መሆኑን ገልጸዋል። እስካሁን ተፈናቅለው የሚገኙ የትግራይ ተወላጆች ወደ ቀዬአቸው እስኪመለሱና ነፃ ባልወጡ የትግራይ ግዛቶች ውስጥ በከፋ መከራ ውስጥ የሚገኙ ነዋሪዎች፣ ሙሉ ለሙሉ ነፃ እስከሚወጡ ድረስ ትግሉ እንደሚቀጥል፣ ለዚህም ጊዜያዊ አስተዳደሩ በሙሉ አቅሙ እየሠራበት እንደሆነ አስታውቀዋል።

የመቀሌ ከተማ ከንቲባ አቶ ይትባረክ አብርሃ በበኩላቸው የትግራይ ሕዝብ ከፍተኛ መከራና ችግር ደርሶበታል ብለው፣ ፅናቱንና የተደራጀ አቅሙን ወደ ልማት በማዞር ካለበት ኢኮኖሚያዊና ሥነ ልቦናዊ ችግር ማውጣት ይገባል ሲሉ አስረድተዋል፡፡

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት አቶ ጌታቸው፣ ትግራይን መልሶ ለመገንባት በሚደረገው እንቅሰቃሴ፣ የክልሉ የፀጥታ ኃይልን ጨምሮ መስዋዕትነት እየከፈሉ መሆናቸውን፣ ትግራይን ለዚህ ቀን ያበቁ ሁሉም ዜጎች በተደራጀ መንገድ የጀመሩትን እንቅስቃሴ አጠናክረው እንዲቀጥሉ፣ እንዲሁም የክልሉን የፀጥታና የፍትሕ ሥርዓት በፍጥነት በማስተካከል የትግራይ ሕዝብ በሰላም ተንቀሳቅሶ ወደ ቤቱ የሚመለስበትን ሁኔታ ለመፍጠር ይሠራል ብለዋል።

‹‹ጊዜያዊ አስተዳደሩ በአጭር ጊዜ ለውጥ ማምጣት የሚያስችል አቅም አለው፤›› ያሉት አቶ ጌታቸው፣ ከሁሉም በላይ ግን በትግራይ ሕዝብ አቅም ሙሉ እምነት እንዳላቸው ገልጸዋል፡፡ በአስተዳደሩ ላይ የሚታዩ ጉድለቶችን ከሕዝቡ ጋር በመወያየትና ተቀናጅቶ በመሥራት በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ተሻለ ደረጃ እንደሚደረስ ተናግረዋል።

የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት የትግራይ ሕዝብን ፍላጎት በሚያሟላ መንገድ የሚፈጸምበትን ሁኔታ ለመፍጠር፣ የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር በሙሉ አቅሙ እየሠራ መሆኑንም አክለዋል፡፡  

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ለሰው ልጅ መብት መከበር ስናወራ 75 ዓመት ሞላን!

በገነት ዓለሙ ዓለም ስለሰብዓዊ መብቶች ሲያወራ፣ ሲምል፣ ሲገዘት፣ ሲፈጠም፣ ቃል...

ካልተማከለ የካፒታል ገበያ ወደ ዘመናዊና የተደራጀ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ

በእሱፈቃድ ተረፈ በአገራችን የካፒታል ገበያ አዋጅ መውጣትን ተከትሎ የተማከለ የሰነደ...

ለማይቀረው ምክክርና ድርድር እንዘጋጅ

በያሲን ባህሩ  የዘመናዊት ኢትዮጵያ ፖለቲካ ውዝግብ በትንሹ የአንድ ምዕተ ዓመት...

ደንብ አስከባሪዎች ደንብ ያክብሩ!

በአዲስ አበባ ከተማ ደንብ አስከባሪዎች፣ ሌሎች የፀጥታ አካላት፣ እንዲሁም...