Sunday, December 10, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናበልዩ ወረዳ ምሥረታ ስም ጉራጌ ዞንን ለማዳከም የሚደረገውን ጥረት እንደሚቃወም ጎጎት ፓርቲ...

በልዩ ወረዳ ምሥረታ ስም ጉራጌ ዞንን ለማዳከም የሚደረገውን ጥረት እንደሚቃወም ጎጎት ፓርቲ አስታወቀ

ቀን:

ጎጎት ለጉራጌ አንድነትና ፍትህ ፓርቲ በልዩ ወረዳ ምሥረታ ስም የጉራጌ ዞንን ለማዳከም የሚደረገውን ጥረት እንደሚቃወም ገለጸ፡፡ ፓርቲው ዓርብ መስከረም 18 ቀን 2016 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ፣ የቀቤና ልዩ ወረዳን በማደራጀት እንዲሁም የወልቂጤ ከተማ ወሰንን በማካለል ስም የጉራጌ ዞን ሕዝቦች ጥቅምና ሕገ መንግሥታዊ መብት እየተጣሰ መሆኑን ይፋ አድርጓል፡፡

ፓርቲው በመግለጫው በጉራጌ ዞን ተካተው የኖሩት ቀቤናና ማረቆ ወረዳዎች ራሳቸውን ችለው ከዞኑ ተነጥለው በልዩ ወረዳ እንዲደራጁ መወሰኑን አስታውሷል፡፡ ሆኖም ጉራጌ ዞን በክልልነት የመደራጀትን ጨምሮ የራሱ የአደረጃጀት ጥያቄዎች እንዳሉት ያነሳል፡፡ ዞኑ ያነሳው የክልልነት ጥያቄ ሳይመለስ፣ ‹‹ማዕከላዊ ኢትዮጵያ›› በሚል ስም በተደራጀው ‹‹ሕገወጥ›› ባለው ክልል ውስጥ መደራጀቱ አግባብነት የሌለው መሆኑን ይገልጻል፡፡

የጉራጌ ዞን የአደረጃጀት ጥያቄው ባይመለስም የሌሎች ሕገ መንግሥታዊ የሆነ የመደራጀት ጥያቄ በመመለሱ እንደማይቃወም አትቷል፡፡ ይሁን እንጂ የሌሎች የአደረጃጀት ጥያቄ ሲመለስ የዞኑን ጥቅም በማይጋፋ መንገድ መሆን እንዳለበት ጠቁሟል፡፡

በሕገወጥ መንገድ የተመሠረተው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ‹‹አዳዲስ ተጨማሪ የአስተዳደር እርከን ለማቋቋም የቀረበ የውሳኔ ሐሳብ›› በሚል የፀደቀው መመርያ፣ ራሱ ገና በተግባር አለመተርጎሙን የጎጎት መግለጫ ያነሳል፡፡

ይህ ሁሉ ባለበት የቀቤና ወረዳ ራሱን የቻለ ተጠሪነቱ ለማዕከላዊ ኢትዮጵያ የሆነ ልዩ ወረዳ ይመሥረት መባሉን ይገልጻል፡፡ የማረቆን ወረዳም በተመለከተ ተመሳሳይ ውሳኔ ተላልፏል ይላል፡፡

ይህ የወረዳ ምሥረታ ሒደትና የወሰን ማስከበር ጉዳይ ግን የጉራጌ ዞን ሕዝቦችን ጥቅም እንደሚጎዳ የገለጸው ጎጎት፣ በአካባቢው ተጨማሪ አለመረጋጋት እንዳይፈጥር ሥጋቱን ያነሳል፡፡ ጎጎት እንደሚለው የልዩ ወረዳ ምሥረታና የወልቂጤ ከተማ የወሰን ማስከበር ሒደቱን ሕዝቡ በመቃወም በተለያዩ ወረዳዎች የተቃውሞ ሠልፍ አድርጓል፡፡

የጎጎት መግለጫ ሲቀጥል ቀቤናና ማረቆ ልዩ ወረዳዎች ተብለው እንዲካለሉ መወሰኑ በአሰያየም፣ አደረጃጀት፣ የማዕከላት ምርጫና ስያሜ እንዲሁም የሀብት ክፍፍልን በተመለከተ በሕዝቡ ዘንድ ቅሬታ እንደፈጠረ ይገልጻል፡፡

ስለዚሁ መግለጫ እንዲሁም ሕዝቡ ስላነሳው ተቃውሞ ተጨማሪ ማብራሪያ የተጠየቁት የጎጎት የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ጀሚል ሳኒ፣ ጉዳዩ በልዩ ወረዳዎች ማደራጀት ስም የጉራጌ ሕዝብን የረዥም ዘመን የክልልነት ጥያቄ ለማዳፈን የሚደረግ ጥረት አካል መሆኑን ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

‹‹ዛሬ ልዩ ወረዳ ሆነው ይውጡ የተባሉ አካባቢዎች በፊት በነበረው አደረጃጀት በዞኑ ሥር በወረዳ ደረጃ እንዲዋቀሩ በሚል ከሌሎች የጉራጌ ወረዳዎች ቀበሌዎችን ጭምር እንዲወስዱ ተደርጓል፡፡ ልዩ ወረዳ ሆነው ይውጡ በተባሉት ወረዳዎች ዛሬም ድረስ የጉራጌ ተወላጆች አብላጫ ቁጥር አላቸው፡፡

ወረዳዎቹ በዞንም ሆነ በከተማ ምክር ቤቶች ከጉራጌ ተወላጆች ጋር የሚመጣጠን ውክልና ተሰጥቷቸው ነው የኖሩት፡፡ ነገር ግን የጉራጌ ተወላጆችን መብትና ፍላጎት ባላከበረ መንገድ ለብቻቸው በልዩ ወረዳነት ተለይተው ይውጡ መባሉ አግባብነት የሌለው ነው፤›› በማለት አቶ ጀሚል አስረድተዋል፡፡

ሕዝብ ግንኙነቱ አክለውም ወልቂጤ ከተማ የዞኑ ነባር ዋና መቀመጫ ሆና ሳለ፣ አሁን ላይ ወደ ቀቤና ልዩ ወረዳ ትካለል መባሉም ሌላ የሕዝብ የተቃውሞ ምንጭ ይሆናል የሚል ሥጋት እንዳላቸው አንስተዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ለሰው ልጅ መብት መከበር ስናወራ 75 ዓመት ሞላን!

በገነት ዓለሙ ዓለም ስለሰብዓዊ መብቶች ሲያወራ፣ ሲምል፣ ሲገዘት፣ ሲፈጠም፣ ቃል...

ካልተማከለ የካፒታል ገበያ ወደ ዘመናዊና የተደራጀ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ

በእሱፈቃድ ተረፈ በአገራችን የካፒታል ገበያ አዋጅ መውጣትን ተከትሎ የተማከለ የሰነደ...

ለማይቀረው ምክክርና ድርድር እንዘጋጅ

በያሲን ባህሩ  የዘመናዊት ኢትዮጵያ ፖለቲካ ውዝግብ በትንሹ የአንድ ምዕተ ዓመት...

ደንብ አስከባሪዎች ደንብ ያክብሩ!

በአዲስ አበባ ከተማ ደንብ አስከባሪዎች፣ ሌሎች የፀጥታ አካላት፣ እንዲሁም...