Sunday, December 10, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናየኮስሞ ትሬዲንግ የቀድሞ ሥራ አስኪያጆች የ112.7 ሚሊዮን ብር ክስ ቀረበባቸው

የኮስሞ ትሬዲንግ የቀድሞ ሥራ አስኪያጆች የ112.7 ሚሊዮን ብር ክስ ቀረበባቸው

ቀን:

ከአራት ዓመታት በፊት ከመስከረም 27 ቀን 2011 ዓ.ም. ጀምሮ ኮስሞ ትሬዲንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበርን በምክትል ሥራ አስኪያጅነት እንዲመሩ ተሹመው የነበሩት አቶ ተመስገን ይልማ፣ ወ/ሮ አዜብ ምሕረተአብና አቶ ገመቹ ዲንቃ የተባሉ ግለሰቦች፣ አላግባብ ለመበልፀግ ለራሳቸው አውለውታል የተባለን 112,761,350 ብር እንዲከፍሉ ክስ ቀረበባቸው፡፡

ክሱን ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ፍትሐ ብሔር ችሎት ያቀረበው ኮስሞ ትሬዲንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ሲሆን፣ ክሱ በሪጅስትራር በኩል ተቀባይነት አግኝቶ ቀጠሮ እየጠበቀ መሆኑ ታውቋል፡፡

የኮስሞ ትሬዲንግ የቀድሞ ሥራ አስኪያጆች የ112.7 ሚሊዮን ብር ክስ ቀረበባቸው | Ethiopian Reporter | ሪፖርተር
የኮስሞ ትሬዲንግ ሕንፃ

ክሱ በሦስት የክስ ፋይሎች የቀረበ ሲሆን፣ ተከሳሾቹ ያልተገባ ብልፅግና ለማግኘት በማሰብ፣ የኮስሞ ትሬዲንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበርን የይዞታ ማረጋገጫ ሰነድ (ካርታ) አስይዘው፣ ከአዋሽ ባንክ የወሰዱትን ብድር ከነወለዱ 55,250,000 ብር በጋራ ወይም ከነወለዱ እንዲከፍሉ ማኅበሩ ዳኝነት ጠይቋል፡፡

ማኅበሩ ሌላው ያቀረበው ክስና የጠየቀው ዳኝነት፣ ተከሳሾቹ በማኅበሩ ከፍተኛ ባለድርሻና ማኔጂንግ ዳይሬክተር አቶ ኃይለየሱስ መንግሥቱ አማካይነት፣ በሥራ አስኪያጅና ምክትል ሥራ አስኪያጅነት ድርጅቱን (ማኅበሩን) እንዲመሩና እንዲያስተዳድሩ የተሰጣቸውን ኃላፊነት ተገን በማድረግ፣ ግምቱ 500 ሚሊዮን የሆነውን ባለዘጠኝ ወለል ሕንፃ ለሆቴልና ለቢሮ መገልገያነት ከተከራዩ ግለሰቦች የሰበሰቡትንና ለግላቸው ያዋሉትን 34,725,300 ብር (ከነ ወለዱ) እንዲከፍሉ መሆኑን ክሱ ያብራራል፡፡

የኮስሞ ትሬዲንግ ማኔጂንግ ዳይሬክተር አቶ ኃይለየሱስ፣ አቶ ተመስገንን ድርጅቱን እንዲያስተዳድሩ የምክትል ሥራ አስኪያጅነት ኃላፊነት ሰጥተዋቸው እያሉ፣ የኮስሞ ትሬዲንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበርን ባለዘጠኝ ወለል ሕንፃ፣ የቻይና ዜግነት ላላቸው ባዬዮንግ ለተባሉ ግለሰብ ለሆቴልና ለቢሮ መገልገያነት በ575,000 ብር ለስድስት ወር በማከራየትና በቀጣይ ለ18 ወራት በድምሩ ለሁለት ዓመት በማከራየት ከነወለዱ 22,786,050 ብር፣ ሃምሳ በመቶ ባለድርሻ ለሆኑበት ቲቲኤች ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ማስተላለፋቸው በክሱ ተብራቷል፡፡ የተጠቀሰውን ገንዘብም ፍርድ ቤቱ እንዲያስከፍለውም ማኅበሩ ዳኝነት ጠይቋል፡፡

በተያያዘ ዜና ለኮስሞ ትሬዲንግ ከፍተኛ ባለድርሻ አቶ ኃይለየሱስ መንግሥቱና ሁለት ባለድርሻዎች ፍርድ ቤት የወሰነውን ክፍያ ባለዕዳዎች ሊከፍሉ ባለመቻላቸው፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ የአዋሽ ባንክ፣ የአቢሲኒያ ባንክ፣ የዳሸን ባንክ፣ የወጋገን ባንክና የንብ ባንክ ዋና መሥሪያ ቤቶች 1,202,850 ብር ካልከፈለው ጄጄ ፕሮፐርቲ ማኔጅመንት ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ቁጠባ ላይ እንዲያግዱና በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 የቤት ቁጥር 308 የሆነውንና በወ/ሮ አዜብ ምሕረተአብ ስም ተመዝግቦ የሚገኘው መኖሪያ ቤት እንዳይሸጥ እንዳይለወጥና ለሦስተኛ ወገን እንዳይተላለፍ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ለሰው ልጅ መብት መከበር ስናወራ 75 ዓመት ሞላን!

በገነት ዓለሙ ዓለም ስለሰብዓዊ መብቶች ሲያወራ፣ ሲምል፣ ሲገዘት፣ ሲፈጠም፣ ቃል...

ካልተማከለ የካፒታል ገበያ ወደ ዘመናዊና የተደራጀ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ

በእሱፈቃድ ተረፈ በአገራችን የካፒታል ገበያ አዋጅ መውጣትን ተከትሎ የተማከለ የሰነደ...

ለማይቀረው ምክክርና ድርድር እንዘጋጅ

በያሲን ባህሩ  የዘመናዊት ኢትዮጵያ ፖለቲካ ውዝግብ በትንሹ የአንድ ምዕተ ዓመት...

ደንብ አስከባሪዎች ደንብ ያክብሩ!

በአዲስ አበባ ከተማ ደንብ አስከባሪዎች፣ ሌሎች የፀጥታ አካላት፣ እንዲሁም...