Monday, December 11, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊለአደጋ መከላከልና ምላሽ ለመስጠት የሚያግዝ ቴክኖሎጂ በ300 ሚሊዮን ብር ወጪ ተግባራዊ ሊደረግ...

ለአደጋ መከላከልና ምላሽ ለመስጠት የሚያግዝ ቴክኖሎጂ በ300 ሚሊዮን ብር ወጪ ተግባራዊ ሊደረግ ነው

ቀን:

በአዲስ አበባ ከተማ የድንገተኛ እሳትና አደጋን ለመከላከልና በፍጥነት ምላሽ ለመስጠት የሚያስችል 316 ሚሊዮን ብር ወጪ የተደረገበት አዲስ ቴክኖሎጂ ሊተገበር መሆኑን፣ ኢትዮ ቴሌኮምና የከተማው የእሳትና አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን በጋራ አስታወቁ፡፡

ማክሰኞ መስከረም 15 ቀን 2016 ዓ.ም. ኢትዮ ቴሌኮምና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ የኮንትራት ስምምነት ሲደረግ፣ ቴክኖሎጂው በአደጋ ጊዜ ድጋፍ አሰጣጥን በማዘመን ወጪ ቆጣቢ አሠራር የሚከተል ነው ተብሏል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ የእሳትና አደጋ ሥራ አመራር ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አቶ ይክፈለው ወልደ መስቀል፣ ከተማዋ እሳትና ጎርፍን ጨምሮ ለአሥር ዓይነት አደጋዎች የተጋለጠች መሆኗን ገልጸዋል፡፡

ከዚህ ቀደም የድንገተኛ አደጋ ምላሽ አሰጣጥ በቴክኖሎጂ የተደገፈ ባለመሆኑ፣ ችግሮችን በቶሎ መለየትና ምላሽ መስጠት ላይ ብዙ ክፍተቶች እንደነበሩ ጠቁመዋል፡፡

ይሁን እንጂ ከ2015 ዓ.ም. ጀምሮ የኮሚሽኑን የድንገተኛ የጥሪ ማዕከል ከማኑዋል ወደ ዲጂታል በመቀየርና ሐሰተኛ ጥሪዎችን በመለየት፣ ትክክለኛ ጥሪዎችን ማስተናገድ መጀመሩን ምክትል ኮሚሽነሩ ተናግረዋል፡፡

የዲጂታል ሥርዓቱ አካል የሆነው ስማርት የእሳትና የአደጋ አመራር ሶሉዩሽን ለመተግበር፣ ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር ስምምነት ላይ መደረሱን አስረድተዋል፡፡

ስምምነቱ በዋናነት የተቀናጀ ግንኙነት፣ በቴክኖሎጂ የተደገፈ ሥምሪት፣ አካባቢያዊ የመረጃ ሥርዓት በመዘርጋት ውጤታማ የአደጋ ጊዜ ሥራ አመራርን መደገፍ የሚያስችል ቴክኖሎጂ ሥራ ላይ ማዋል መሆኑን አክለዋል፡፡

የኢትዮ ቴሌኮም ቺፍ ማርኬቲንግ ኦፊሰር አቶ ሰይድ አራጋው በበኩላቸው፣ ኩባንያው ከኮኔክቲቪቲ አገልግሎት ባሻገር የፋይናንስ አካታችነትን በማረጋገጥ የዲጂታል አገልግሎት በስፋት ተደራሽ እያደረገ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የዲጂታል ኢትዮጵያን ራዕይ ለማሳካት ዘርፈ ብዙ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆናቸውን ገልጸው፣ የእሳት አደጋና ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽንን ፕሮጀክት ዕውን ለማድረግ የሚያስችል የሶሉዩሽን ትግበራም የሥራው አንዱ አካል መሆኑን አስረድተዋል፡፡

በድንገተኛ አደጋ ወቅት ምላሽ ለመስጠት አገልግሎት ላይ ይውላል የተባለው ቴክኖሎጂ፣ ከሦስት ወራት በኋላ ሥራውን ይጀምራል ተብሎ ይጠበቃል ተብሏል፡፡

ከዚህ ቀደም የኮሚሽኑ የድንገተኛ አደጋ ምላሽ አሰጣጥ አተገባበር ኋላቀር (ማኑዋል) እንደነበረ፣ ከሦስት ወራት በኋላ ቴክኖሎጂው ሲተገበር ዘጠኙም ቅርንጫፎች የተገናኙ በመሆናቸው አደጋ ሲደርስ አቅራቢያ ያለው ቅርንጫፍ ምላሽ የሚሰጥበት ዘመናዊ አሠራር እንደሚኖረው ተናግረዋል፡፡

የድንገተኛ አደጋ ሠራተኞችም በእጅ ስልካቸው አደጋ የደረሰበትን ቦታ መረጃ የሚደርሳቸው ከመሆኑ ባሻገር፣ ከመረጃ ማዕከሉ በቀጥታ የሚገናኙበት አሠራር እንዳለው አስረድተዋል፡፡

በአዲስ አበባ የእሳትና አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን የቴክኖሎጂና የማሽነሪ ጥገና ዘርፍ ኃላፊ አቶ አሸናፊ ቶላ፣ በተቋሙ የተለያዩ የሪፎርም ሥራዎች መጀመራቸውን፣ ከከተማዋ ዕድገት ጋር እኩል የሚራመድ የአደጋ መከላከልና ፈጣን ምላሽ አሰጣጥ ጉድለት መለየቱን ተናግረዋል፡፡

ኮሚሽኑም ያለውን ክፍተት ለመሙላት በአምስት ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ ትኩረት በማድረግ፣ የአደጋ መከላከልና ምላሽ አሰጣጥ የማዘመን ሥራዎችን እየተገበረ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡

ትኩረት ከተሰጣቸው ጉዳዮች መካከል ኮሚሽኑን በቴክኖሎጂ ማዘመን አንዱ መሆኑን የገለጹት አቶ አሸናፊ፣ በሰውና በንብረት ላይ የሚደርሰውን አደጋ ለመከላከል ቴክኖሎጂን ማዘመንና ማሳደግ ዋነኛው ትኩረት ነው ብለዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ለሰው ልጅ መብት መከበር ስናወራ 75 ዓመት ሞላን!

በገነት ዓለሙ ዓለም ስለሰብዓዊ መብቶች ሲያወራ፣ ሲምል፣ ሲገዘት፣ ሲፈጠም፣ ቃል...

ካልተማከለ የካፒታል ገበያ ወደ ዘመናዊና የተደራጀ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ

በእሱፈቃድ ተረፈ በአገራችን የካፒታል ገበያ አዋጅ መውጣትን ተከትሎ የተማከለ የሰነደ...

ለማይቀረው ምክክርና ድርድር እንዘጋጅ

በያሲን ባህሩ  የዘመናዊት ኢትዮጵያ ፖለቲካ ውዝግብ በትንሹ የአንድ ምዕተ ዓመት...

ደንብ አስከባሪዎች ደንብ ያክብሩ!

በአዲስ አበባ ከተማ ደንብ አስከባሪዎች፣ ሌሎች የፀጥታ አካላት፣ እንዲሁም...