Wednesday, December 6, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናኢትዮጵያ ውሉ የጠፋና ተለዋዋጭ የሆነ ጊዜ ውስጥ እንደምትገኝ በማኅበራዊ ጥናት መድረክ ጥናት...

ኢትዮጵያ ውሉ የጠፋና ተለዋዋጭ የሆነ ጊዜ ውስጥ እንደምትገኝ በማኅበራዊ ጥናት መድረክ ጥናት ተገለጸ

ቀን:

አገር በቀሉ የፖሊሲ ጥናትና ምርምር ተቋም የማኅበራዊ ጥናት መድረክ (ፎረም ፎር ሶሻል ስተዲስ – FSS) ከሰሞኑ ይፋ ባደረገው ጥናት፣ ኢትዮጵያ ውሉ በጠፋና ተለዋዋጭ በሆነ ጊዜ ውስጥ እንደምትገኝ ገለጸ፡፡ ሐሙስ መስከረም 10 ቀን 2016 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ሒልተን ሆቴል የቀረበው ጥናቱ፣ የኢትዮጵያን ወቅታዊና የወደፊት መፃዒ ሁኔታ ዳሷል፡፡

‹‹ኢትዮጵያ ወዴት? ቢሆንታዎች›› በሚል ርዕስ የቀረበው ይኼው ጥናት የአገሪቱን ነባራዊ ሁኔታ መንገራገጭ፣ የሐምሌ ጨለማና ፀደይ በማለት በሦስት ቢሆንታዎች (Scenarios) ለማስቀመጥ የሞከረ ነበር፡፡ የቢሆንታዎችን ምንነትን ወደኋላ በመመለስ ከታሪካዊ ዳራ ተነስቶ ብይን ለመስጠት የሚሞክረው ጥናቱ፣ የወቅቱን የአገሪቱን ሁኔታም ፍቺ ለመስጠት ሞክሯል፡፡

‹‹በአንድ ማኅበረሰብ የመንግሥት ተዓማኒነት እየተሽከረከረ ሲሄድ፣ ማኅበረሰባዊ ትስስር ሲመነምንና በሕዝብ ዘንድ የፍትሕ መጓደል/ ተበዳይነት ስሜቶች ሲያንዣብቡ፣ ጽንፈኝነት ይነግሣል፤›› በማለት ነው ይኸው ጥናት የኢትዮጵያን ገጽታ በማስቀመጥ ወደ ሐተታው የሚንደረደረው፡፡

በአሁኗ ኢትዮጵያ እነዚህ ሁሉ ሁኔታዎች እንደሚታዩ ያተተው ጥናቱ፣ ፖለቲካዊ መግባባት በአገሪቱ መፍጠር ከምንም በላይ አስፈላጊ መሆኑን ያሰምርበታል፡፡ ያም ቢሆን ግን ባለፉት 50 ዓመታት በኢትዮጵያም ሆነ በሌሎች የአፍሪካ አገሮች ችግሮችን ተወያይቶ  የመፍታት ባህል አለመዳበሩ ትልቁ ራስ ምታት እንደሆነ ያወሳል፡፡

በዘውዳዊው ሥርዓት መውደቅ ማግሥት አምባገነናዊ ሥርዓት በኢትዮጵያ በማቆጥቆጡ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ተስፋው መምከኑን ያስረዳል፡፡ ደርግ ወድቆ በ1983 ዓ.ም. የመንግሥት ለውጥ ሲደረግ የሕዝቦች እኩልነት ይፈጠራል የሚል ተስፋ መፈጠሩን፣ ይሁን እንጂ ይህንን ለውጥ ተከትሎ የተቀረፀው ሕገ መንግሥት የብሔር ብሔረሰቦች እኩልነት ይፈጥራል ቢባልም፣ ነገር ግን በኢትዮጵያ ታሪክ ታይቶ የማይታወቅ የጭቅጭቅ ምዕራፍ መክፈቱን ያትታል፡፡

በየታሪክ ምዕራፉ ለዴሞክራሲያዊ የፖለቲካ ሽግግር ተስፋ የፈነጠቁ አጋጣሚዎችን አለፍ ገደም እያለ የሚዘረዝረው ጥናቱ፣ በ2010 ዓ.ም. የተፈጠረውን የፖለቲካ ለውጥ እንደ አንዱ አጋጣሚ ያነሳዋል፡፡ ‹‹ለውጡ ከፈጠረው ከፍተኛ የሕዝብ ፈንጠዚያ ጀርባ ግን በለውጥ አቀንቃኞችና በቀድሞ ሥርዓት ናፋቂዎች መካከል ውስጥ ውስጡን ውጥረት ሰፈነ፤›› ይላል፡፡

የአዲስ ተስፋው ፍንጣቂ በለውጡ  ማግሥት ብዙም ሳይዘገ በመጣው ‹‹የነውጥ ጊዜ›› እንደተተካም ነው የኤፍኤስኤስ የቢሆንታዎች ጥናት ያመላከተው፡፡

የኢትዮጵያ አገረ መንግሥት ታሪክ በብዙ ፈታኝ ውጣ ውረዶች ውስጥ የማለፍ አስገራሚ ፅናት የተላበሰ መሆኑን ጥናቱ ያብራራል፡፡ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ባህል ግን ፈላጭ ቆራጭነት የሰፈነበት ሆኖ መቆየቱን ይገልጻል፡፡ በኢኮኖሚውም መስክ በአስከፊ ድህነት ውስጥ አገሪቱ ተዘፍቃ መኖሯን ያትታል፡፡

ከዚህ ሁሉ ተነስቶ አገሪቱ የሐምሌ ጨለማ፣ መንገጫገጭና ፀደይ የሚል ስም የተሰጣቸው ቢሆንታዎችን ልታስተናግድ እንደምትችል ሰፊ ትንተና ያቀርባል፡፡ በሌላ በኩል የመበታተን አደጋን እንደ አንድ ቢሆንታ ያነሳዋል፡፡ ‹‹አስደንጋጭ ቢሆንም የአገሪቱ የመበታተን አደጋ የማይታሰብ ነው ለማለት አይቻልም፤›› ሲል ነው ይህንኑ ጉዳይ ጥናቱ የሚያብራራው፡፡

ጥናቱ ከአፍሪካ ቀንድ ሁኔታ እስከ አየር ንብረት ለውጥ፣ ከሃይማኖትና ፖለቲካ ፅንፈኝነት እስከ የብሔርና ያልተማከለ አስተዳደር ውጥረት አገሪቱን ሊፈትኑ የሚችሉ ነጥቦችን ይፈትሻል፡፡ ከኢኮኖሚ አለመረጋጋት እስከ የዋጋ ንረት ውጣ ውረዶንችም ያነሳል፡፡ በሌላ በኩል የአማራ ክልልና አገሪቱን ወጥረው የያዙ በየአቅጣጫው ያሉ የግጭት ሁኔታዎችን ተፅዕኖም ይፈትሻል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ታዋቂው የኤሌክትሮኒክስ ብራንድ አይቴል የስትራቴጂ ለውጥ አካል የሆነውን አዲስ አርማ እና መለዮ ይፋ አደረገ።

በአለማችን ታዋቂ ከሆኑት የኤሌክትሮኒክስ ብራንዶች መካከል አንዱ የሆነው እና...

የጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ ጥሪ ለሸገር አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ

ለሸገር አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ የሸገር አነስተኛ የፋይናንስ...

[የክቡር ሚኒስትሩ ጸሐፊ፣ የሌላ ሚኒስትር ጸሐፊ ከሆነችው የቅርብ ወዳጇ ጋር በስልክ እየተጨዋወቱ ነው]

አንቺ ግን ምን ሆነሽ ነው? ጠፋሁ አይደል? ጠፋሁ ብቻ?! ምን ላድርግ ብለሽ...

በሱዳን ላይ ያጠላው የመከፋፈል ዕጣና ቀጣናዊ ተፅዕኖው

የሱዳን ጦርነት ስምንተኛ ወሩን እያገባደደ ይገኛል፡፡ ጄኔራል አብዱልፈታህ አልቡርሃን...