የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ምክትል ፕሬዚዳንት ሌተና ጄኔራል ጻድቃን ገብረ ትንሣዔ፣ በክልሉ በተካሄደው የአስተዳደሩ ስብሰባ ላይ የተናገሩት፡፡ በመስከረም 2016 የመጀመርያ ሳምንት በነበረው መድረክ፣ ምክትል ፕሬዚዳንቱ አያይዘውም በሕገወጥ መሣሪያ ዝውውር፣ በሰብዓዊ ዕርዳታ የመሠረታዊ ፍጆታዎች ላይ የሚፈጸመው ስርቆት ምንም መፍትሔ ሳይሰጣቸው እንደ ተራ ነገር እየተቆጠሩ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ የአገዛዝ ሲስተሙ በሙሉ የተበላሸ መስሎ ይሰማኛልም ብለዋል፡፡