Sunday, December 10, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትበርካታ ተተኪዎች የተመለመሉበት የሴንትራል ሐዋሳ የአማረች ታዳጊዎች ዋንጫ

በርካታ ተተኪዎች የተመለመሉበት የሴንትራል ሐዋሳ የአማረች ታዳጊዎች ዋንጫ

ቀን:

በሐዋሳ ከተማ የተለያዩ ሠፈሮች በሚገኙ የአሸዋ ሜዳዎች በርካታ ታዳጊዎች እግር ኳስ ሲጫወቱ መመልከት የተለመደ ነው። በእነዚህ የማዘውተሪያ ሥፍራዎች የአካባቢው ኅብረተሰብ በጉጉት የሚጠብቀውና የሚመለከተው ውድድር ሲሆን፣ በሳምንት ሁለትና ሦስት ጊዜ ውድድር ማድረግ የተለመደ ነበር። በሒደት ግን በከተማዋ ግንባታ እየተስፋፋ መምጣቱን ተከትሎ፣ ሕፃናት እንደ ቀድሞ የማዘውተሪያ ሥፍራና ውድድሮችን ማግኘታቸው ቀላል አይደለም።

በአንፃሩ መከናወን ከጀመረ 13 ዓመታትን የተሻገረው የሴንትራል ሐዋሳ አማረች ዋንጫ፣ የታዳጊዎች እግር ኳስ ውድድር ለበርካታ የከተማዋ ታዳጊዎች ዕድል ከመፍጠሩም በላይ፣ ተቀዛቅዞ የቆየውን የሠፈር ጨዋታ ድባብ ዳግም መመለሱ ይነገራል። በውድድሩ መቃረቢያ በከተማዋ የሚገኙ በርካታ ታዳጊዎች ከየሠፈሩ እየተውጣጡ በክለባቸው አማካይነት ቅድመ ዝግጅት ያደርጋሉ።

በሴንትራል ሐዋሳ ሆቴል መሥራች ወ/ሮ አማረች ዘለቀ ሐሳብ አመንጪነት፣ ላለፉት 13 ዓመት እየተካሄደ የቆየው የታዳጊ ውድድር ላይ ከ13 ዓመት በታች፣ ከ15 ዓመት በታችና ከ17 ዓመት በታች ፕሮጀክቶችን የያዘ ነው። በውድድሩ በአጠቃላይ ከ13 ዓመት በታች 14 ክለቦችና ከ17 ዓመት በታች 12 ክለቦች በቄራ ሜዳ ሲፎካከሩ ቆይተዋል። 

በውድድሩም ከ13 ዓመት በታች – ሮሀ ፕሮጀክት፣ ከ15 ዓመት በታች – ሉ ፕሮሞሽን እንዲሁም ከ17 ዓመት በታች – ወሜ ግሮሰሪ ፕሮጀክት የዋንጫ ባለቤት ሲሆኑ፣ በውድድሩ ክስተት የሆኑ ከ13 ዓመት በታች ሁለት ተወዳዳሪዎች ልዩ ተሸላሚ ሆነዋል።

በሴንትራል ሐዋሳ ሆቴል ሙሉ ስፖንሰር አድራጊነትና መሥራችነት ላለፋት 12 ዓመታት በክረምት ታዳጊዎችን ከአልባሌ ቦታ እንዲያስቀር፣ ተተኪ ስፓርተኞችን ለማፍራት፣ እንዲሁም ብቁ ዜጋ ለማፍራት ታሳቢ በማድረግ ውድድሩ ሲያካሄድ ቆይቷል።

ወ/ሮ አማረች በዚህ ራዕያቸው በርካታ ተተኪ ስፖርተኞች ያፈሩ ሲሆን፣ ከእነዚህም መካከል ከክለብ እስከ ብሔራዊ ቡድን የደረሱ ስፖርተኞችን ይገኙበታል፡፡ በዘንድሮው ውድድርም በርካታ የፕሪሚየር ሊግ ክለብ መልማዮችና አሠልጣኞች ተተኪዎችን ሲመለከቱ ነበር። 

በውድድሩ በክብር እንግድነት የተገኙት የሲዳማ ክልል ስፖርት ኮሚሽነር አቶ ፍሬው አሬራ ባደረጉት ንግግር፣ በወ/ሮ አማረች ሐሳብ አመንጪነት ሙሉ ወጪ እየተሸፈነ፣ ላለፉት 13 ዓመታት የደመቀ ውድድር ሲካሄድ መቆየቱን አስረድተዋል። በተጨማሪም ወ/ሮ አማረች የታዳጊ ሴቶች ውድድር ማየት ምኞታቸው እንደሆነ የተገለጸ ሲሆን፣ ዝግጁ ለሆኑት የሴቶች ቡድኖች በሙሉ ሙሉ ትጥቅ እንዲሁም የኳስ ድጋፍ መደረጉ ተጠቅሷል። ወ/ሮ አማረች ዘለቀ ከስድስት ወራት በፊት ማረፋቸው ይታወሳል።

በኢትዮጵያ የትምህርት ቤትና የሠፈር ውድድሮች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተመናመኑ መምጣታቸውን ተከትሎ፣ ተተኪ ተጫዋቾችን ማግኘት ከባድ እየሆነ መምጣቱ ይገለጻል። በዚህም ምክንያት በፕሪሚየር ሊግ የሚሳተፉ ክለቦች፣ አዳዲስ ተጫዋቾችን ከማፍራት ይልቅ በዕድሜ የገፉና በሊጉ ላይ የሰንበቱ ተጫዋቾችን እያዟዟሩ መጠቀምን ተያይዘውታል። ይህም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአኅጉር አቀፍ ውድድር በተወሰኑ ተጫዋቾች ላይ ብቻ የሙጥኝ ብሎ እንዲቆይ አስገድዶታል። 

እግር ኳሱን ለማሳደግ ታዳጊዎች በፕሮጀክት አቅፎ ተተኪዎችን ማፍራት ብቸኛ አማራጭ ከመሆኑም በላይ፣ በግለሰቦች ተነሳሽነት በየዓመቱ ሳይቋረጥ እየተከናወነ የሚገኘው የሴንትራል ሐዋሳ አማረች፣ የታዳጊዎች የዋንጫ ጨዋታ ማሳደግና አስፈላጊውን ድጋፍ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑ በበርካቶች ዘንድ ይነሳል። 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ለሰው ልጅ መብት መከበር ስናወራ 75 ዓመት ሞላን!

በገነት ዓለሙ ዓለም ስለሰብዓዊ መብቶች ሲያወራ፣ ሲምል፣ ሲገዘት፣ ሲፈጠም፣ ቃል...

ካልተማከለ የካፒታል ገበያ ወደ ዘመናዊና የተደራጀ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ

በእሱፈቃድ ተረፈ በአገራችን የካፒታል ገበያ አዋጅ መውጣትን ተከትሎ የተማከለ የሰነደ...

ለማይቀረው ምክክርና ድርድር እንዘጋጅ

በያሲን ባህሩ  የዘመናዊት ኢትዮጵያ ፖለቲካ ውዝግብ በትንሹ የአንድ ምዕተ ዓመት...

ደንብ አስከባሪዎች ደንብ ያክብሩ!

በአዲስ አበባ ከተማ ደንብ አስከባሪዎች፣ ሌሎች የፀጥታ አካላት፣ እንዲሁም...