ምን አገኛቸው
ብሎ ለጠየቀው እስቲ ይነገረው
እኔ አሁን ላብራራው
አልጋ ምጣድ ሆኖ የሚጋግሩበት
አብስለው አውጥተው የሚመገቡበት
ስንት ሰዎች አሉ፤ ብዙ የሆኑበት
እሳቱን ለኩሰው ጭረውት
እራሳቸው ነደው ሊጡን ሲያፈሱበት
እንዲህ እየተባለ ብዙ ሌሊት ነጋ
የእንጀራ እና አልጋ
ቀን እየተቦካ ሌሊት በጋገራ
በሦስት በአራት ቀን ከውጭ ነው እንጀራ
በአምስተኛው ቀን ሌላ እስከሚቦካ
የጋለ ምጣድ ፈካ
አይ እንጀራ እና አልጋ
ብዙ ስናወራ
ሌሊቱ እኮ ነጋ
ቤተልሔም ዘላለም ‹‹የጨለመባቸው›› (2006 ዓ.ም.