Wednesday, September 27, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትሉሲዎቹ በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የቡሩንዲ አቻቸውን ይገጥማሉ

ሉሲዎቹ በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የቡሩንዲ አቻቸውን ይገጥማሉ

ቀን:

  • ስዋሎውስ የመልስ ጨዋታቸውን በአዲስ አበባ ያደርጋሉ

የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን (ሉሲዎቹ) በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የቡሩንዲ ብሔራዊ ቡድንን (ስዋሎውስ) ይገጥማሉ፡፡ ሉሲዎቹ ለጨዋታው ዝግጅታቸውን አጠናከረው መቀጠላቸው የተገለጸ ሲሆን፣ የመጀመርያ ጨዋታቸውን ረቡዕ መስከረም 9 ቀን 2016 ዓ.ም. በአበበ ቢቂላ ስታዲየም እንደሚያደርጉ ተገልጿል፡፡

ቡሩንዲ የመልስ ጨዋታዋን በአዲስ አበባ ለማድረግ መወሰኗን ያስታወቀው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን፣ ጨዋታው በአበበ ቢቂላ ስታዲየም የሚካሄደው ማክሰኞ መስከረም 15 ቀን ነው ብሏል።

ዋሊያዎቹ ቡድኑ መደበኛ ዝግጅታቸውን ማድረግ መቀጠላቸው የተገለጸ ሲሆን፣ ዳማ ከተባለ የወንዶች ቡድን ጋር የልምምድ ጨዋታ ማድረጉ ተጠቁሟል፡፡

የሉሲዎቹ ዋና አሠልጣኝ ፍሬው ወልደገብርኤል ዘንድሮ በሞሮኮ ለሚከናወነው የዋፍኮን 2024 ውድድር ለማለፍ ለሚደረገው የማጣሪያ ጨዋታ 26 ተጫዋቾችን መምረጡ ይታወሳል፡፡

ኢትዮጵያ በቋት ሁለት ከግብፅ፣ ኮንጎ፣ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ፣ ቶጎ፣ ጋምቢያ፣ ኬፕቨርዴ፣ ጋቦንና ጊኒ ጋር ተደልድላለች፡፡

በዚህም መሠረተ ቋት ሦስት ከሚገኙት ስዋሎዎች ጋር የሚጫወቱት ሉሲዎቹ የኢኳቶሪያል ጊኒና የሊቢያ ጨዋታ አሸናፊን ይገጥማሉ፡፡

በመጪው ጥር ወር በሞሮኮ ለሚዘጋጀው የአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ፣በማጣሪያው የሚሳተፉ 42 ብሔራዊ ቡድኖች ከመስከረም እስከ ታኅሣሥ ጨዋታቸውን ካደረጉ በኋላ፣ አዘጋጇን ጨምሮ ባሸናፊነት የሚወጡ 12 ቡድኖች በየምድቡ ተደልድለው ለዋንጫው ይፋለማሉ።

እ.ኤ.አ. በ1991 የተጀመረው የሴቶች የአፍሪካ ዋንጫ ናይጀሪያ 11 ጊዜ ዋንጫውን ማንሳት ችላለች፡፡ ሉሲዎቹ መሳተፍ ከጀመሩበት ወቅት አንስቶ እ.ኤ.አ. በ2004 በደቡብ አፍሪካ በተሰናዳው ጨዋታ እስከ ሩብ ፍፃሜ መድረስ ችለዋል፡፡

ሉሲዎቹ በ2004 የደቡብ አፍሪካ የዋንጫ ጨዋታ አራተኛ ደረጃን ይዘው ያጠናቀቁበትን ጨምሮ በአፍሪካ ዋንጫ ሦስት ጊዜ መካፈል ችለዋል፡፡

በኢትዮጵያ የሴቶች እግር ኳስ ከወንዶቹ አንፃር በአኅጉር አቀፍ ውድድሮች፣ እንዲሁም በክለብ ውድድሮች የተሻለ ውጤት እያስመዘገበ ነው፡፡ ሆኖም በተገቢው መንገድ ትኩረት አለማግኘቱ ይጠቀሳል፡፡

የሴቶች የአፍሪካ ዋንጫን ያዘጋጁ ናይጀሪያ (1998፣ 2002፣ 2006)፣ ደቡብ አፍሪካ (2000፣ 2004፣ 2010)፣ ኢኳቶሪያል ጊኒ (2008 እና 2012)፣ ሞሮኮ (2022፣ 2024)፣ ናምቢያ 2014፣ ካሜሮን 2016፣ እንዲሁም ጋና በ2018 ናቸው፡፡ 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የአማራ ክልል ወቅታዊ ሁኔታ

እሑድ ጠዋት መስከረም 13 ቀን 2016 ዓ.ም. የፋኖ ታጣቂዎች...

ብሔራዊ ባንክ ለተመረጡ አልሚዎች የውጭ አካውንት እንዲከፍቱ ለመጀመሪያ ጊዜ የፈቀደበት መመርያና ዝርዝሮቹ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ አጠቃቀምንና ተያያዥነት ያላቸው ጉዳዮችን...

እነ ሰበብ ደርዳሪዎች!

ከሜክሲኮ ወደ ዓለም ባንክ ልንጓዝ ነው። ሾፌርና ወያላ ጎማ...