Wednesday, September 27, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየኮዬ ፈጬ 10/90 ኮንዶሚኒየም ነዋሪዎች የጣሪያና የግድግዳ ተመን የተጋነነ ነው ሲሉ ቅሬታ...

የኮዬ ፈጬ 10/90 ኮንዶሚኒየም ነዋሪዎች የጣሪያና የግድግዳ ተመን የተጋነነ ነው ሲሉ ቅሬታ አቀረቡ

ቀን:

  • የተተመነውን ክፍያ መፈጸም ካልቻሉ ቤቱን ልቀቁ ተብለናል ብለዋል

በሸገር ከተማ የኮዬ ፈጬ 10/90 ኮንዶሚኒየም ነዋሪዎች የጣሪያና የግድግዳ የቤት ግብር ተመን የተጋነነ ነው ሲሉ ቅሬታ አቀረቡ፡፡

ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ ቅሬታ አቅራቢዎች ለሪፖርተር እንደተናገሩት፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የጣሪያና ግድግዳ የቤት ግብር አዲሱ አዋጁ ከወጣበት ጀምሮ እንደሚያስከፍል የገለጸ ቢሆንም፣ በሸገር ከተማ ኮዬ ፈጬ ክፍለ ከተማ የ2015 ዓ.ም. ግማሽ ክፍያ ከአዋጁ በፊት የነበረውን የስድስት ወራት ክፍያ ጭምር በመደመር ክፈሉ ተብለዋል፡፡

የኮዬ ፈጬ 10/90 ኮንዶሚኒየም ነዋሪዎች የጣሪያና የግድግዳ ተመን የተጋነነ ነው ሲሉ ቅሬታ አቀረቡ | Ethiopian Reporter | ሪፖርተር

በ10/90 ኮንዶሚኒየም ውስጥ በአብዛኛው በከፍተኛ ድህነት ውስጥ የሚገኙ ዜጎች፣ አካል ጉዳተኞች፣ ዓይነ ስውራን፣ እንዲሁም ጧሪ የሌላቸው አዛውንቶች እንደሚኖሩ ቅሬታ አቅራቢዎቹ ገልጸዋል፡፡  

በአብዛኛው ወርኃዊ የባንክ ዕዳውን በመክፈል ላይ ያለ ነዋሪ እንደሚገኝ የገለጹት ነዋሪዎቹ፣ የጣሪያና የግርግዳ ክፍያ ከአዲስ አበባ በአማካይ በካሬ 90 ብር የበለጠ የክፍያ ተመን መውጣቱን ተናግረዋል፡፡

በመሀል ከተማ የሚገኙ ቤቶች በሽያጭም ሆነ በኪራይ ከፍተኛ ዋጋ እንደሚያወጡ፣ ነገር ግን የእነሱ ቤቶች ዝቅተኛ ዋጋ እያወጡ ከፍተኛ ተመን ክፈሉ መባሉ ቅሬታ እንደፈጠረባቸው ተናግረዋል፡፡

የአካባቢው ነዋሪዎች የገቢ መጠን ዝቅተኛ መሆኑ እየታወቀ በመሀል ከተማ ከተተመነው ክፍያ በካሬ 43 ብር ጭማሪ በማድረግ፣ በካሬ 133 ብር በአንድ ወር ውስጥ ክፈሉ መባላቸውን አስረድተዋል፡፡

ከስምንት ወራት በፊት በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ይኖሩ እንደነበር የተናገሩት ቅሬታ አቅራቢዎቹ፣ አሁን በሸገር ከተማ የኮዬ ፈጬ ኮንዶሚኒየም ነዋሪዎች 10/90 በተለምዶ የደሀ ደሀ የሚባለው ከስድስት ዓመት በፊት በ7,000 ብር ቅድመ ክፍያ፣ በ70,000 ብር አጠቃላይ ክፍያ በመንግሥት ድጎማ የተላለፉ ቤቶች መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

ነዋሪዎቹ ያቀረቡትን ቅሬታ መሠረት በማድረግ ሪፖርተር በሸገር ከተማ የኮዬ ፈጬ ክፍለ ከተማ ምክትል ኃላፊ አቶ ቶለዋቃ ፈይሳን ጥያቄ ቢያቀርብላቸውም፣ ከነዋሪዎቹ የመጣ ምንም ቅሬታ የለም ብለዋል፡፡

እስካሁን ድረስ ከነዋሪዎቹ የደረሰ ምንም ዓይነት ቅሬታ አለመኖሩን የተናገሩት አቶ ቶለዋቃ፣ መንግሥት ያስቀመጠውን የግብር ክፍያ መክፈል የዜጎች ግዴታ መሆኑን አስታውሰዋል፡፡

ነዋሪዎቹ ግን የተተመነላቸውን የመኖሪያ ቤቶች የጣሪያና ግድግዳ ግብር የማይከፍሉ ከሆነ ቤቱን ለቅቀው እንዲወጡ እንደሚደረጉ ተገልጾልናል ብለዋል፡፡

ነዋሪዎቹ ክፍያውን የማይከፍሉ ከሆኑ ቤታቸውን ለቅቀው እንዲወጡ ይደረጋሉ ስለተባለው ጉዳይ ሪፖርተር ክፍለ ከተማውን በደብዳቤ ቢጠይቅም ምላሽ ማግኘት አልተቻለም፡፡

በተለምዶ የጣሪያና የግድግዳ ግብር እየተባለ የሚታወቀው የቤት ግብር በኢትዮጵያ ከ1937 ዓ.ም. ጀምሮ ሥራ ላይ የዋለ ሲሆን፣ በዋናነት በከተማ ማዘጋጃ ቤቶች እየተሰበሰበ ተመልሶ ለከተሞች ልማት ሲውል መቆየቱ ይነገራል።

በአዲስ አበባ ከተማ በየጊዜው እየጨመረ ከመጣው የከተማው ሕዝብ ብዛት ጋር ተያይዞ በሥራ ላይ ባለው የቦታ ኪራይና የቤት ግብር ሥርዓቱ ያልዘመነ ከመሆኑም በላይ፣ ከተማው ከዚህ ዘርፍ የሚሰበስበው ገቢ እጅግ አነስተኛ በመሆኑ የዓመታዊ ኪራይ ዋጋ ተመን ወቅታዊ መደረጉን የከተማ አስተዳደሩ ማስታወቁ ይታወሳል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የአማራ ክልል ወቅታዊ ሁኔታ

እሑድ ጠዋት መስከረም 13 ቀን 2016 ዓ.ም. የፋኖ ታጣቂዎች...

ብሔራዊ ባንክ ለተመረጡ አልሚዎች የውጭ አካውንት እንዲከፍቱ ለመጀመሪያ ጊዜ የፈቀደበት መመርያና ዝርዝሮቹ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ አጠቃቀምንና ተያያዥነት ያላቸው ጉዳዮችን...

እነ ሰበብ ደርዳሪዎች!

ከሜክሲኮ ወደ ዓለም ባንክ ልንጓዝ ነው። ሾፌርና ወያላ ጎማ...