Tuesday, September 26, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ፍሬከናፍር‹‹በአዲሱ ዓመት የሰው ሕይወትን የሚቀጥፉ የመሣሪያ አፈ ሙዞች በሙሉ ወደ መጋዝን መግባት...

‹‹በአዲሱ ዓመት የሰው ሕይወትን የሚቀጥፉ የመሣሪያ አፈ ሙዞች በሙሉ ወደ መጋዝን መግባት አለባቸው››

ቀን:

ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ፣ አዲሱን ዓመት 2016 ዓ.ም. አስመልክቶ  ከዋሽንግተን ዲሲ አሜሪካ ባስተላለፉት መልዕክት ያስተጋቡት ኃይለ ቃል፡፡ ችግሮችን በውይይት፣ አሊያም በሕግ እየተፈቱ የአገርና የሕዝብ ሉዓላዊነት ነፃነትና አንድነት መረጋገጥ አለበት ያሉት ቅዱስ ፓትርያርኩ፣ በአዲሱ ዓመት ይህንን ለማድረግ በቁርጥ ከተነሳን ሰላማችን ወደነበረበት ይመለሳል፡፡ አገራችንም በበረከት ትሞላለች፤ ስለዚህም ኢትዮጵያውያን የሆናችሁ ልጆቻችን ሁሉ ይህንን ጥሪያችንን ተቀብላችሁ የጥፋት መሣሪያችሁንም አስቀምጣችሁ ወደ ሰላም ማእድ ቀርባችሁ በወንድማማችነት መንፈስ ችግራችሁን በክብ ጠረጴዛ በውይይት በመፍታት የአገሪቱንና የሕዝቡን አንድነት እንድታስቀጥሉ ሁሉን በሚያይ እግዚአብሔር ስም እንማጸናችኋለን ብለዋል፡፡ ያለፈው ዓመት ያሳረፈብንን ሁለንተናዊ ተጽዕኖ በሚገባ አስተውለን፣ ዳግም ወደ አዲሱ ዓመት እንዳይሸጋገርብን ካላደረግን አዲሱ ዓመት ለኛ የሚሰጠን ትርጉም ምንድን ነው? ባለፉት ዓመታት በሃይማኖት፣ በባህል፣ በታሪክ፣ በኢኮኖሚ፣ በማኅበራዊና ፖለቲካዊ እንዲሁም በሕዝባችን ሥር የሰደደውን የእርስ በርስ መጠራጠር ከልብ መርምረን ወደ ድሮው እኛነታችን ካልተመለከትንስ አዲስ ዘመን እያልን ማክበራችን ምን ፋይዳ አለው? ይህንን ሁሉ በአዲሱ ዓመት በማጤን ያለፈውን ጎጂ ነገር በመተው፤ ጠቃሚውን ግን ይበልጥ በማጠናከር አዲሱን ዓመት መቀበል አለብን ሲሉም አጥብቀው አሳስበዋል፡፡  አያይዘውም እንዳስገነዘቡት፣ ከሁሉ በላይ ለአገራችንና ለሕዝባችን የሚጠቅመው ምንድነው? በሚለው በምር መሥራት አለብን፤ በመለያየት፣ በመፎካከር፣ በመበቃቀል፣ በመናናቅ፣ የራስን ጥቅም ብቻ ለማስጠበቅ በመጣር፣ ጊዜ አገኘሁ ብሎ ኃይልን በመጠቀም፣ የሕዝብን ጥቅም ማስከበርና የአገርን አንድነት ማስቀጠል አይቻልም፤ አገራችንንና ሕዝባችንን ወደ ዕመቀ ዕመቅ እየከተቱ ያሉ እንደዚህ ያሉ አስተሳሰቦች ናቸውና እነዚህ ሁሉ ከአሮጌው ዓመት ጋራ አብረው መወገድ አለባቸው፡፡  

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የቤት ባለንብረቶች የሚከፍሉትን ዓመታዊ የንብረት ታክስ የሚተምን ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጀ

በአዋጁ መሥፈርት መሠረት የክልልና የከተማ አስተዳደሮች የንብረት ታክስ መጠን...

እንደ ንብረት ታክስ ያሉ ወጪን የሚያስከትሉ አዋጆች ከማኅበረሰብ ጋር ምክክርን ይሻሉ!

የመንግሥትን ገቢ በማሳደግ ረገድ አስተዋጽኦ እንዳላቸው የሚታመኑት የተጨማሪ እሴት...

ለዓለምም ለኢትዮጵያም ሰላም እንታገል

በበቀለ ሹሜ ያለፉት ሁለት የዓለም ጦርነቶች በአያሌው የኃያል ነን ባይ...