Tuesday, September 26, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትበግብፅ አሥር ዓመትን ያሳለፈው የዋሊያዎቹ አማካይ መቻልን ተቀላቀለ

በግብፅ አሥር ዓመትን ያሳለፈው የዋሊያዎቹ አማካይ መቻልን ተቀላቀለ

ቀን:

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን (ዋሊያዎቹ) አማካይና ለአሥር ዓመታት በግብፅ የተለያዩ ክለቦች በመጫወት ያሳለፈው ሽመልስ በቀለ ለመቻል እግር ኳስ ክለብ መፈረሙ ተረጋገጠ፡፡

የዋሊያዎቹ አምበል ሽመልስ ከግብፅ መልስ የተለያዩ የኢትዮጵያ ክለቦችን እንደሚቀላቀል ሲነገር የቆየ ሲሆን፣ በመጨረሻ በመከላከያ ሥር ባለው የመቻል ክለብ ለሁለት ዓመታት የሚያቆየውን ፊርማ ማኖሩ ይፋ ሆኗል፡፡

በአሠልጣኝ ገብረ ክርስቶስ ቢራራ የሚመራው መቻል እግር ኳስ ክለብ በዝውውሩ ከፍተኛ ልምድ ያካበተውን አማካይ የግሉ ማድረጉን አስታውቋል፡፡

ሽመልስ ከቀናት በፊት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለአይቮሪኮቱ የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ የመጨረሻ ጨዋታ ግብፅን ሲገጥሙ ተሠልፎ ነበር፡፡

የብሔራዊ ቡድን አማካዩ ከዘጠኝ ዓመታት አስቀድሞ የግብፁን ፔትሮጄትን በመቀላቀል ለስድስት ዓመታት መጫወት ችሏል፡፡ በግብፅ የእግር ኳስ ሕይወቱን የቀጠለው ሽመልስ፣ በምስሪ አልመቅሳን፣ በኤልጎውን እንዲሁም በኤንፒ እግር ኳስ ክለብ ለአንድ ዓመት መጫወት ችሏል፡፡ ሽመልስ ከግብፅ ሊግ በፊት በሱዳን ሊግ መጫወት መቻሉ ይታወሳል፡፡

በሐዋሳ ከተማ እግር ኳስ ክለብ መጫወት የጀመረው ሽመልስ ቀጣዩ ክለቡ ቅዱስ ጊዮርጊስ እግርኳስ ክለብ ነበር።በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለረዥም ዓመታት ከተጫወቱ ተጫዋቾች መካከል አንዱ ሲሆን፣ ከ31 ዓመታት በኋላ ወደ አፍሪካ ዋንጫ ሲመለስ የታሪካዊው ቡድን አባል ነበር፡፡

አዲሱ ክለብ መቻል ለ2016 ዓ.ም. የፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ቅድመ ዝግጅቱን በቢሾፍቱ እያደረገ ሲሆን፣ ቡድኑን ተቀላቅሎ ዝግጅቱን እንደሚጀምር ይጠበቃል፡፡ የዘንድሮው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር መስከረም 20 ቀን ይጀምራል፡፡ በዚህም መሠረት በመጀመርያ ሳምንት ጨዋታ መቻል ሐዲያ ሆሳዕናን ይገጥማል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የቤት ባለንብረቶች የሚከፍሉትን ዓመታዊ የንብረት ታክስ የሚተምን ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጀ

በአዋጁ መሥፈርት መሠረት የክልልና የከተማ አስተዳደሮች የንብረት ታክስ መጠን...

እንደ ንብረት ታክስ ያሉ ወጪን የሚያስከትሉ አዋጆች ከማኅበረሰብ ጋር ምክክርን ይሻሉ!

የመንግሥትን ገቢ በማሳደግ ረገድ አስተዋጽኦ እንዳላቸው የሚታመኑት የተጨማሪ እሴት...

ለዓለምም ለኢትዮጵያም ሰላም እንታገል

በበቀለ ሹሜ ያለፉት ሁለት የዓለም ጦርነቶች በአያሌው የኃያል ነን ባይ...