ፕሬዚዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ፣ በኬንያ ናይሮቢ እየተካሄደ ባለው የአፍሪካ የአየር ንብረት ጉባዔ ላይ የተናገሩት፡፡ አፍሪካ በአየር ንብረት ለውጥ ላይ የሚሠሩ የምርምር ተቋማት ላይ ሙዓለ ንዋይ ማፍሰስ ይገባታል ያሉት ፕሬዚዳንቷ፣ በኢትዮጵያ ባለፈው አሠርት የአየር ንብረት ለውጥ በፈጠራቸው ቀውሶች ድርቅ፣ ጎርፍ እና የአንበጣ መንጋ ሚሊዮኖች ለጉዳት መዳረጋቸውን አንስተዋል። በሌላ በኩል፣ ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል በአስር ዓመት የልማት መሪ ዕቅድ ውስጥ ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር አረንጓዴ ኢኮኖሚን የመገንባትን ጉዳይ አካታ እየሠራች ስለመሆኑም ገልጸዋል።