Saturday, July 20, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜና ሴቶች በፖለቲካ ውሳኔዎችና በአገሪቱ ጉዳዮች የሚሳተፉበት አመቺ የሰላም ሁኔታ የለም ተባለ

 ሴቶች በፖለቲካ ውሳኔዎችና በአገሪቱ ጉዳዮች የሚሳተፉበት አመቺ የሰላም ሁኔታ የለም ተባለ

ቀን:

ሴቶች በጦርነት ዋና ተጎጂዎች የሆኑትን ያህል በሰላም ግንባታ ሒደት በሰፊው መሳተፋቸው አስፈላጊ መሆኑ የሚታመን ቢሆንም፣ በፖለቲካ ውሳኔዎችም ሆነ በአገሪቱ ጉዳዮች የሚሳተፉበት አመቺ የሰላም ሁኔታ አለመኖሩ ነው የተነገረው፡፡

የአዲስ አበባ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ባዘጋጀው የሰላም ግንባታ ላይ ትኩረቱን ባደረገ የፓናል ውይይት፣ ላይ እንደተገለጸው ሴቶች በጋራ ቆመው ጦርነት በአገሪቱ ይብቃ ብለው እንዲታገሉ ጥሪ ቀረበ፡፡

በኢትዮጵያ በየዘመናቱ የሚደጋገሙ የጦርነት አጋጣሚዎች ውዱን የሰው ሕይወት ከማሳጣትና ንብረትን ከማውደም በዘለለ፣ ሴቶችን በዋናነት ሰለባ እያደረጉ እንደሆነ፣ ኢትዮጵያዊያን በተለይም ዋና የጦርነት ሰለባ የሆኑ ሴቶች ሰላም በአገሪቱ እንዲመጣ መታገል እንዳለባቸው ትናንት ነሐሴ 30 ቀን 2015 ዓ.ም. በካፒታል ሆቴል በተደረገ ውይይት ጥሪ ቀርቧል፡፡

የአዲስ አበባ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት የሴቶች ክንፍ ፕሬዚዳንት ወ/ሪት እመቤት ቢራራ፣ ሁሉም የፖለቲካ ኃይሎች እርስ በርስ ከመፈራረጅ ወጥተው ለሰላም ግንባታ በጋራ ሊቆሙ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡ ‹‹ሴቶች የፖለቲካ ተሳትፏቸው እንዲጠናከር ሰላም ያስፈልጋል፡፡ ሰላም ከዚህ በላይ የሁሉም ነገራችን አልፋና ኦሜጋም ነው፡፡ ኢትዮጵያዊያን ስለሰላም አስፈላጊነት ከሌሎች አገሮች ወይም ከመጻሕፍት ሳይሆን፣ ከሰፊው የጦርነት ታሪካችን ምዕራፍ መረዳት እንችላለን፡፡ ዛሬ ላለንበት ድህነትና ጉስቁልና የዳረገን ያለፍንበት የጦርነት ታሪክ ነው፤›› ብለዋል፡፡

ሴቶች የፖለቲካ ተሳትፎ ማድረግ ያለባቸው በችሮታ እንዳልሆነ ያሰመሩበት ወ/ሪት እመቤት፣ ሕገ መንግሥታዊ መብት እንዳላቸው ጠቅሰዋል፡፡ ‹‹ያለው የፖለቲካ ምኅዳር ከመታሰር፣ ከሥራ ከመፈናቀል፣ ከመሞት ጋር የተገናኘ በመሆኑ ሴቶች ከፖለቲካው ይርቃሉ፤›› ሲሉ የችግሩን መነሻ አስረድተዋል፡፡

በአገር አቀፍ ደረጃ ባለው የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ውስጥ የሴቶች ክንፍ ሰብሳቢ የሆኑት ወ/ሮ ቅድስት ግርማ በበኩላቸው፣ መድረኩን በአገር ደረጃ የማስፋት ዕቅድ መኖሩን ተናግረዋል፡፡

በየዓመቱ ማርች ስምንት የሴቶች ቀን ሲመጣ ብቻ ሳይሆን ተመሳሳይ መደበኛ እንቅስቃሴዎች እንደሚያስፈልጉ ጠቁመው፣ በአገራዊ ምክክሩም ቢሆን የሴቶች ተሳትፎን የማጠናከር ሥራ ተጀምሯል ብለዋል፡፡

‹‹የሴቶች የፖለቲካ ተሳትፎ ወደኋላ የቀረ በመሆኑ ነው አገሪቱ ለሰላም ዕጦትና ለብዙ ችግሮች ተጋላጭ የሆነችው፤›› ሲሉ የተናገሩት ወ/ሮ ቅድስት፣ ይህ መለወጥ እንዳለበት አስረድተዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

አቶ ሰብስብ አባፊራ የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሆነው ተመረጡ

ከአዋጅና መመሪያ ውጪ ለዓመታት ሳይካሄድ የቆየው የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ...

ቀጣናዊ ገጽታ የያዘው የኢትዮ ሶማሊያ ውዝግብ

ከአሥር ቀናት ቀደም ብሎ በተካሄደው የፓርላማ 36ኛ መደበኛ ስብሰባ፣...

የኢንሹራንስ ኩባንያዎች በዓረቦንና የጉዳት ካሳ ክፍያዎች ላይ ተጨማሪ እሴት ታክስ መጣሉን ተቃወሙ

በአዲሱ ተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ውስጥ የኢንሹራንስ ከባንያዎች ለሚሰበስቡት...