Saturday, July 20, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊታዳጊዎችን ከአቪዬሽን ሳይንስ ጋር ያገናኘው መድረክ

ታዳጊዎችን ከአቪዬሽን ሳይንስ ጋር ያገናኘው መድረክ

ቀን:

በሚፈልጉት፣ በተመኙትና ባሰቡት የሥራ ዘርፍ ለመሰማራት በርትቶ መሥራት፣ ቁርጠኝነትንና ውሳኔን ይጠይቃል።

ገበሬ በጥቅምት እሸቱና ወተቱን፣ በኅዳር ምርቱን ለመሰብሰብ ከወዲሁ በክረምቱ  ዝናብና ፀሐዩን ሳይፈራ መሥራት ይኖርበታል። በዝናብ አብቅሎ በፀሐይ አብስሎ  ቤተሰብና አገሩ በልቶ ያድር ዘንድ በርትቶ መሥራት ይጠበቅበታል።

ነጋዴም ይሁን ላብ አደር፣ አስተማሪም ይሁን ተማሪ ቀጣይ ሕይወታቸውን  ለማስተካከል ያለሙትና ያቀዱትን ለማሳካት በርትተው መሥራት ይጠበቅባቸዋል።  በዜጎቿ የምትኮራ ከሙስናና ከብልሹ አሠራር የፀዳች አገርን ለማየት የሚጓጓ አስተማሪ ከወዲሁ በተማሪዎቹ ላይ መሥራት ይኖርበታል።

ታዳጊዎችን ከአቪዬሽን ሳይንስ ጋር ያገናኘው መድረክ | Ethiopian Reporter | ሪፖርተር

ስለአገር ፍቅር ስለመቻቻልና ስለአብሮነት እንዲሁም ስለእኩልነትና  ሰብዓዊነትን የተላበሱ ዜጎችን  ለማፍራት  የአስተማሪው ሚና ከፍ ያለ ነው።

በቴክኖሎጂ የበለፀገች አገርን ለመገንባት ወጣቶችና ታዳጊዎች ላይ መሠራት እንዳለበት ይነገራል። ለዚህ ደግሞ ተማሪዎችን አስቀድሞ ከቴክኖሎጂው ጋር ማስተዋወቅ አንዳንድ ትልልቅ ኢንዱስትሪዎች እንደሚያደርጉት  ተማሪዎች  ቀድመው  እንዲጎበኙትና የተግባር ልምምዶችን ቢያደርጉበት ከሁሉም በተሻለ ስለ ቴክኖሎጂ ለማወቅ የበለጠ ጉጉት ያሳድርባቸዋል።

ተማሪ ዲቦራ ተሾመና ተማሪ ኢዮብ ፈቀደ ክረምቱን በኢትዮጵያ አየር መንገድ በሚገኘው አቪዬሽን ዩኒቨርሲቲ ከዘርፉ ጋር የተያያዘ ሥልጠና ከመውሰድ ባለፈ ጉብኝቶችን ሲያደርጉ መቆየታቸውን ተናግረዋል።

 ዲቦራ ተወልዳ ያደገችው በድሬዳዋ ከተማ ሲሆን፣ የ11ኛ ክፍል ተማሪ ናት። የፈጠራ ሥራዎችን መሞከር ያስደስተኛል የምትለው ዲቦራ፣ ልምዷን በማዳበር ነገ ከምትፈልገው ደረጃ ለመድረስ ከወዲሁ የተግባር ልምምዶች ላይ ትኩረት አድርጋ እየተማረች እንደሆነ ትናገራለች።

‹‹ሥራዎችን የሚያቀሉ ሮቦቶችን መሥራት የበለጠ ያስደስተኛል፤›› የምትለው ዲቦራ፣ ክረምቱን በኢትዮጵያ አቪዬሽን  ዩኒቨርሲቲ ማሳለፏ የበለጠ እንዳነሳሳትና ለህልሟ መሳካትም ትልቅ ስንቅ ያገኘችበት እንደሆነ ተናግራለች፡፡

 ‹‹ኤሮስፔስ ኢንጂነሪግ›› መሆን እፈልጋለሁ የምትለው ታዳጊ ወጣቷ በአቪዬሽን ዩኒቨርሲቲ መቆየቷ ደግሞ ለህልሜ የበለጠ አቅርቦኛል ትላለች፡፡

ይህንን ያሰበችው ኢትዮጵያ የራሷ የሆነ አውሮፕላን  እንዲኖራት  ወይም በራሷ አምርታ እንድትጠቀም ስለምፈልግ ነው የምትለው ዲቦራ፣ ይሄንና መሰል  ሮቦቶችን  ለመሥራት ይረዳት ዘንድ እንዲሁም ወደ ዓላማዋ በር የሚያደርሳትን መንገድ ከወዲሁ እንደመረጠች ተናግራለች፡፡

ለዚህም ኤሮስፔስ ኢንጂነሪንግ ምርጫዋ አድርጋ ለመማር ዝግጅት እያደረገች እንደሆነ የተናገረች ሲሆን፣ ህልሟ ዕውን እንደሚሆንም በኢትዮጵያ አቪዬሽን ዩኒቨርሲቲ በነበራት ቆይታ እንደተገነዘበች አስረድታለች፡፡

 በቀጣይ ከዚህ በበለጠ ለዘርፉ ትኩረት ሰጥታ መሥራት እንዳለባት ነው ወጣቷ የምትናገረው፡፡ ‹‹የማይቻል ነገር የለም›› የምትለው ዲቦራ፣ ነገር ግን ይህንን ሐሳብ ስትናገር በብዛት አይቻልም የሚሉ ምላሾችን ብትሰማም በተለይ ከሥልጠናው በኋላ ተነሳሽነቷን የሚያበረታቱ ነገሮችን እንዳየች ተናግራለች፡፡

በመጪው ዓመት የኢትዮጵያ አቪዬሽን ዩኒቨርሲቲ የኤሮስፔስ ምህንድስና ትምህርት ይጀምራል መባሉ በጣም እንዳስደሰታት ገልጻለች፡፡

 ወደ አቪዬሽን ዩኒቨርሲቲ መምጣቷ ብዙ ነገሮችን ለማወቅ እንደረዳት የምትናገረው ዲቦራ፣ ከበርካታ የኢትዮጵያ ተማሪዎች መካከል በትምህርት ቤት ውስጥ  በነበራት ንቁ ተሳትፎ ለውድድር ቀርባ ባስመዘገበችው ከፍተኛ ውጤት ዕድሉን እንዳገኘች ተናግራለች፡፡

በነበራት ቆይታም ከአካዴሚያዊ ዕውቀት ባሻገር ከተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የመጡ ተማሪዎች ጋር የልምድ ልውውጥ እንዳደረገችና ከሰዎች ጋር እንዴት ተስማምቶ መኖር እንደሚቻል ትልቅ ልምድ መቅሰሟን አስረድታለች፡፡

በተመሳሳይ ለስድስት ሳምንታት ከ24 ተማሪዎች ጋር ጥሩ ቆይታ እንደነበረው የተናገረው ተማሪ ኢዮብ፣ በቆይታውም አየር መንገዱ በምን መልኩ እንደሚሠራ እንዲሁም ለወደፊቱ ተምረን በምን ዓይነት የሙያ ዘርፍ መሰማራት እንደምንችል ግንዛቤ አግኝተናል ሲል ገልጿል፡፡ እንዲሁም የነገ መዳረሻችንን ከአሁኑ አውቀን መወሰን እንድንችልና በአቪዬሽን ኢንዱስትሪው የበለጠ ተነሳሽነት እንዲኖረን የሚረዳ ሥልጠና ነበር ሲል ተማሪ ኢዮብ ተናግሯል፡፡ በነበራቸው ቆይታም የተለያዩ  ፕሮጀክቶችን በማበልፀግ ሮቦቶችንና ዌብሳይቶችን እንዴት መሥራት እንዳለባቸው የተግባር ልምምድ እንዳገኙ ነው የተናገረው።

ሮቦቲክስ ኢንጂነሪንግ ማጥናት እንደሚፈልግ፣ ለዚህም የተለያዩ የፈጠራ ሥራዎች በቤቱ እንደሚገኙ የተናገረው ኢዮብ በቀጣይም የጀመራቸውን የፈጠራ ሥራዎች በማጎልበት በሙያው ለአገሩ ብሎም ለአፍሪካ ትልቅ አስተዋጽኦ ማድረግ እንደሚፈልግ  ይናገራል።

 በነበራቸው ቆይታም በተለይ በስድስተኛው ሳምንት የግድግዳ ማፅጃዎችንና የተለያዩ ዌብ ሳይቶችን በማበልፀግ ለሙከራ አቅርበዋል።

 ‹‹በሺዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎች ያላገኙትን ዕድል በማግኘቴ በጣም ዕድለኛ ነኝ  በዚህም ፈጣሪዬን አመሠግነዋለሁ፤›› የሚለው ተማሪ ኢዮብ፣ በአቪዬሽን ዩኒቨርሲቲው የመጀመርያዎቹ ተመራቂዎች መሆናችን ደግሞ ደስታችንን እጥፍ ያደርገዋል ሲል የተሰማውን ስሜት ይናገራል።

ተማሪዎች ሳይንስና ቴክኖሎጂ በገሃዱ ዓለም እንደት እንደሚተገበር ያዩበት  ሥልጠና እንደነበር የተናገሩት ደግሞ የኢትዮጵያ አቪዬሽን ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት አቶ ካሴ ይማም ናቸው ናቸው።

ከዚህ ባሻገር በክፍል ውስጥ ተማሪዎች የ21ኛ ምዕት ዓመት ክሂሎት የሚባሉትን እንደ ሮቦቲክስ ኮዲንግና ፕሮግራሚንግ የመሳሰሉትን ጭምር መማራቸውን ፕሬዚዳንቱ አክለዋል።

በክፍል ውስጥ የተማሩትን ትምህርቶች በአየር መንገዱ የሥራ ዘርፎች እንዴት ተደርገው  እንደሚተገበሩ  ከተማሩ በኋላ፣ ተማሪዎቹ  የራሳቸውን ዲዛይን በመፍጠር ለኢትዮጵያ ትልቅ ተስፋ  የሆኑ ፈጠራዎችን ያቀረቡበት ጊዜ ነው ብለዋል።

ከ12ቱ ክልሎች አንድ ወንድና አንድ ሴት ተማሪዎች በአጠቃላይ 24 ተማሪዎችን ለስድስት ሳምንት ካሠለጠነ በኋላ ባለፈው ሳምንት ያስመረቀው አቪዬሽን ዩኒቨርሲቲው፣ እንደዚህ ያደረገው ደግሞ ቴክኖሎጂው ለሁሉም ተደራሽ ይሆን ዘንድ እንደሆነ ተጠቅሷል።

ዓላማውም ትምህርት ቤቶች በንድፈ ሐሳብ የሚያስተምሩትን በተግባር ለማስደገፍ የማቴሪያል ውስንነት ስለሚኖር፣ በንድፈ ሐሳብ የተማሩትን በተግባር ለማሳየት እንደሆነ ነው ፕሬዚዳንቱ የተናገሩት።

በ2005 ዓ.ም. የጀመሩትን የተግባር ሥልጠና በቀጣይ ከሌሎች ድርጅቶች ጋር በመተባበር ሰፋ ያለ ፕሮጀክትና ሰፋ ያለ ሥልጠና የመስጠት ዕቅድ እንዳላቸው አቶ ካሴ አክለዋል።

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

አቶ ሰብስብ አባፊራ የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሆነው ተመረጡ

ከአዋጅና መመሪያ ውጪ ለዓመታት ሳይካሄድ የቆየው የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ...

ቀጣናዊ ገጽታ የያዘው የኢትዮ ሶማሊያ ውዝግብ

ከአሥር ቀናት ቀደም ብሎ በተካሄደው የፓርላማ 36ኛ መደበኛ ስብሰባ፣...

የኢንሹራንስ ኩባንያዎች በዓረቦንና የጉዳት ካሳ ክፍያዎች ላይ ተጨማሪ እሴት ታክስ መጣሉን ተቃወሙ

በአዲሱ ተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ውስጥ የኢንሹራንስ ከባንያዎች ለሚሰበስቡት...