Tuesday, July 23, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየሒሳብ ውድድርን ለማጎልበት

የሒሳብ ውድድርን ለማጎልበት

ቀን:

በአበበ ፍቅር

ተማሪዎች አጥብቀው ይፈሩታል፡፡ አምርረው የሚጠሉትም አሉ፡፡ ከፍራቻቸውና ከጥላቻቸው የተነሳም በሒሳብ ትምህርት ክፍለ ጊዜ ከክፍል ይወጣሉ። አንዳንዶች የሒሳብ አስተማሪያቸውን ጭምር ሲጠሉ ይስተዋላሉ።

‹ሒሳብ ትምህርት ችሎታ ላላቸው የተሰጠ ነው› ብለው ሌሎች የትምህርት ዓይነቶች ላይ ትኩረታቸውን አድርገው የሚማሩ ተማሪዎችም ይስተዋላሉ፡፡

ከፍተኛ ውጤት አስመዝግበው ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም የሚገቡ ተማሪዎች ሳይቀሩ የሒሳብ ትምህርት ውጤጣቸው ከሌሎቹ የትምህርት ዓይነቶች ጋር ሲወዳደር ዝቅ ያለ እንደሆነ ይነገራል። ከችግሩ በመነሳት ወላጆች ልጆቻቸውን በሒሳብ ትምህርት ጎበዝ ይሆኑላቸው ዘንድ አጥብቀው ይሻሉ።

ወላጆችም ልጆቻቸው ለሒሳብ ትምህርት ትኩረት ሰጥተው እንዲማሩ ጥረት ያደርጋሉ፣ የግል አስተማሪ ቀጥረውም ያስተምራሉ።

አራቱን የሒሳብ ሥሌቶች ማለትም መደመር፣ መቀነስ ማብዛትና ማካፈልን በማቀላጠፍ የሚሠሩ ተማሪዎች በሁሉም የትምህርት ዓይነቶች ላይም ጥሩ ውጤትን እንደሚያስመዘግቡ ይነገራል፡፡

‹‹ለብዙ ተማሪዎች የሒሳብ ትምህርት የሚከብዳቸው ከሌላው ትምህርት የተለየ  ምስጢር ኖሮት ሳይሆን ተማሪዎች ‹ይከብዳል› ብለው ስለሚያስቡ ነው›› የሚሉት የማይ ሶሮባን ኢትዮጵያ መሥራች አቶ ከበደ አጥናፉ ናቸው።

የሒሳብ ትምህርት ይከብዳል የሚለውን የተሳሳተ ግንዛቤ ለማስቀየር፣ የረዥም ጊዜ የሥራ ልምዳቸውን በመጠቀም ‹‹ማይ ሶሮባን ኢትዮጵያ›› የተሰኘ ድርጅት መክፈታቸውን በዚህም ከ1ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ላሉ ተማሪዎች የተለያዩ ሥልጠናዎችን እየሰጡና ውድድሮችን እያዘጋጁ እንደሆነ ተናግረዋል።

‹‹ሒሳብ ከባድ ነው›› ከሚባልባቸው ምክንያቶች አንዱ ተደጋጋሚ ሙከራዎችንና ሥራዎችን ስለሚፈልግ እንደሆነ የሚገልጹት ኃላፊው፣ ተማሪዎች ሒሳብ ላይ ጎበዝ ለመሆን ጥያቄዎችን ከመሥራታቸው በፊት ትርጓሜዎችን በደንብ መረዳትና የተረዱትን ደግመው ደጋግመው መሥራት ያስፈልጋል ይላሉ።

 ለ13 ዓመታት በሒሳብ መምህርነት እንዳገለገሉ የሚናገሩት አቶ ከበደ፣  የሒሳብ ውድድሮች በተለያዩ የዓለም አገሮች የተለመደ በመሆኑ  ወደ ኢትዮጵያ  ለምን አይመጣም በሚል ተነሳሽነት እንደጀመሩ ያብራራሉ።

ኢትዮጵያም ባለፈው ዓመት በሒሳብ ትምህርት ዘርፍ በአኅጉር ደረጃ ተወዳድራ ስድስት ሜዳሊያዎችን አሽንፋ መምጣቷን ያክላሉ።

እሳቸው በተለያዩ ትምህርት ቤቶች የጀመሩትን የሒሳብ ሥልጠናና ውድድር ዳር ለማድረስና ፍሬያማ ለማድረግ መንግሥት እጁን ሊያስገባበት እንደሚገባ ተናግረው ተደራሽነቱ ሰፊ ከመሆኑም አንፃር የሁሉም ባለድርሻ አካላት ርብርብ ያስፈልጋል ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።

ማይ ሶሮባን ኢትዮጵያ ባለፉት ወራት በአሥር ከተሞች ላይ በሚገኙ ከ400 በላይ ትምህርት ቤቶች በ120ሺ ተማሪዎች መካከል የሒሳብ ትምህርትና ሥሌት ውድድር ሲያካሂድ መቆየቱን ኃላፊው አብራርተዋል፡፡

ተቋሙ ውድድሩን በአሥር ከተሞች በአምስት ቋንቋዎችና በአምስት ዙሮች ሲያካሂድ መቆዩቱንና በውድድሩ እጅግ አስገራሚና ለአገር ተስፋ የሚጣልባቸው የሒሳብ ዕውቀት ያላቸው ተማሪዎች የተከሰቱበት መሆኑን ገልጸው፣ በአገር አቀፍ ውድድር ወደ መጨረሻ ዙር ያለፉ 965 ታዳጊ ተማሪዎች ከፍተኛ ፉክክር ማድረጋቸውን አስታውሰዋል፡፡

ሶሮባ በጃፓን አገር የተፈጠረ አባከስ ሲሆን፣ ቁጥሮችን በቀላሉ ለመደመር፣ ለመቀነስ፣ ላማባዛት ወይም ለማካፈል ይረዳል።

ተማሪዎች ሒሳብን በልጅነት በአባከስ ሲማሩ በሒሳብ ትህምርት ላይ ፈጣን ከመሆናቸው በተጨማሪ ትኩረትን የመሰብሰብ ብቃታቸውንም ያሳድጋል።

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ኢትዮጵያዊ ማን ነው/ናት? ለምክክሩስ መግባባት አለን?

በደምስ ጫንያለው (ዶ/ር) የጽሑፉ መነሻ ዛሬ በአገራችን ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች ግጭቶችና...

ዴሞክራሲ ጫካ ውስጥ አይደገስም

በገነት ዓለሙ የዛሬ ሳምንት ባነሳሁት የኢሰመኮ ሪፖርት መነሻነትና በዚያም ምክንያት...

ኢትዮጵያ በምግብ ራሷን የምትችለው መቼ ነው?

መድረኩ ጠንከር ያሉ የፖሊሲ ጉዳዮች የተነሱበት ነበር፡፡ ስለረሃብ፣ ስለምግብ፣...

ደረጃውን የጠበቀ ስታዲየም በሌላት አገር ዘመናዊ ስታዲየም እየገነቡ ያሉ ክልሎች

አዲሱ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ዘመናዊ ስታዲየም ለማስገንባት ከ500 ሚሊዮን...