በኢትዮጵያ የኮሜዲያን ሥራ ትልቅ ሥፍራ የነበረውና ከዓመታት በፊት ከዚህ ዓለም በሞት የተለየው ተስፋዬ ካሳ ቀጥሎ ያለችውን ቀልድ አቅርቦ ነበር፡፡
የትምህርት በሬዲዮ አቅራቢው ለተማሪዎች ስለ ኤሌክትሪክ ቻርጆች እያስረዱ ነበር፡፡ እናም ሁለት የተለያዩ የኤሌክትሪክ ገመዶች ሲገናኙ ምን እንደሚፈጥሩ ለማስረዳት፣ ‹‹መምህር፣ እባክዎ ሁለቱን ገመዶች አንዱ በግራ፣ ሌላውን ደግሞ በቀኝ እጆችዎ ይያዙ›› ይሉና ለተወሰኑ ሰከንዶች ዝም ይላሉ፡፡ ይህን የታዘዙት መምህር ድርጊቱን ሲፈጽሙ ለካ ኤሌክትሪኩ ጮኾ ጠረጴዛ ሥር ወርውሯቸዋል፡፡ ሁኔታውን ደግሞ ሁሉም ተማሪዎች አይተዋል፡፡
የሬዲዮ ትምህርት አቅራቢው ከጥቂት ዝምታቸው በኋላ፣ ‹‹በጣም ጥሩ መምህር! አሁን ደግሞ ተማሪዎች እንደ መምህራችሁ ሞክሩ›› አሉና በድጋሚ ለሰከንዶች ዝም አሉ፡፡ ከዝምታቸው ቀጥለው ‹‹ተማሪዎች ‘ማን ፉል አለ?’ አላችሁ?›› አሏቸው፡፡
‹‹አጋርነት ለልማት›› (2003)