Tuesday, September 26, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊበሴቶች ላይ የሚሠሩ አገር በቀል ድርጀቶች የገንዘብ ችግር እየገጠማቸው መሆኑን አስታወቁ

በሴቶች ላይ የሚሠሩ አገር በቀል ድርጀቶች የገንዘብ ችግር እየገጠማቸው መሆኑን አስታወቁ

ቀን:

በሴቶች ላይ የሚሠሩ አገር በቀል ድርጅቶች ፕሮግራሞቻቸውን ለመተግበር የገንዘብ ችግር እየገጠማቸው መሆኑን በሴቶች ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ እየሠሩ የሚገኙ አገር በቀል መንግሥታዊ ያልሆኑ ማኅበራትና ጥምረቶች አስታወቁ፡፡

የኢትዮጵያ ሴቶች ማኅበራት ቅንጅት ከአጋሮቹ ጋር በመሆን፣ ሴት መር ማኅበራትን በፆታና እኩልነት ላይ ከሚሠሩ አጋርና ለጋሽ ድርጅቶች ጋር ለማስተሳሰር ባዘጋጀው መድረክ፣ በሴት ላይ የሚሠሩ አገር በቀል ድርጅቶች ከከተማ እስከ ገጠር እስከታች ድረስ በመውረድ፣ የሴቶችን ችግሮች ለመፍታት እየሠሩና ለውጥ እያስመዘገቡ ቢሆንም፣ በተለያዩ ምክንያቶች በሚገጥሟቸው የፋይናንስ እጥረት ዓላማቸውን ለማሳካት በርካታ ተግዳሮቶች እየገጠማቸው እንደሚገኝ ተነግሯል፡፡

የቅንጅቱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ሳባ ገብረ መድኅን የሲቪል ማኅበረሰብ ሴት መር ድርጅቶች የሆኑት ቅንጅቱን ጨምሮ የኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያ ሴቶች ማኅበር፣ የኢትዮጵያ ሴቶችና ሕፃናት ማኅበራት ኅብረትና የኢትዮጵያ ሴንተር ፎር ዴቨሎፕመንት ከፕላን ኢንተርናሽናል ጋር በመተባበር ችግሩን ለመፍታት እየሠሩ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ሆኖም እነሱ ብቻቸውን የሚያደርጉት ጥረት የሴት ማኅበራቱ ከሚሠሯቸው ዘርፈ ብዙ ሥራዎች አንፃር በቂ ስላልሆኑ፣ በሀብት ማሰባሰብና ድርጅቶቹን በገንዘብ በመደገፍ በኩል የሚመለከታቸው የመንግሥት ተቋማት፣ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጀቶች፣ የሴት ማኅበራትና ባለድርሻ አካላት በሙሉ እንዲተባበሩዋቸው ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የኢትዮጵያ ሕፃናትና ሴቶች ማኅበራት ኅብረት ዳይሬክተር ወ/ሮ አዜብ ቀለመወርቅ በበኩላቸው፣ ጥሪውን ያቀረቡ አራት ድርጅቶች ቢሆኑም፣ ጉዳዩ ሁሉንም በሴት ላይ የሚሠሩ መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማትን እንደሚመለከት ጠቁመዋል፡፡

በሴቶች ዙሪያ በተለይ ገጠር ወጥተው ከማኅበረሰቡ ጎን ሆነው በሚሠሩበት ጊዜ የሎጂስቲክስ፣ የሰው ኃይልና ሰፊ የሆነ የበጀት ችግር እንዳለባቸው ገልጸዋል፡፡

የሴቶች ችግሮች ዘርፈ ብዙና ለረዥም ዓመታት ከባህል፣ ከኢኮኖሚና ከእምነት ጋር የተያያዙ በመሆኑ፣ የተቀናጁ ሥራዎች ማከናወን እንደሚያስፈልግም አክለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ሴንተር ፎር ዴቨሎፕመንት ዋና ዳይሬክተር ሐረገወይን አሸናፊ፣ በተሻሻለው አዋጅ የራስን ገቢ በማመንጨት ከዚህ ቀደም ከነበረው የተሻለ ዕድል ቢሰጥም፣ ንግድን ለመሥራት አስቻይ ሁኔታ አለመኖሩን፣ በባለሀብቶች ደረጃ መንግሥታዊ ላልሆኑ ተቋማት ገንዘብ የመስጠት ባህል አለመዳበርና አገሪቱም አቅም ስለሌላት ችግሩ ጎልቷል ብለዋል፡፡

በአራቱ ድርጀቶች አስተባባሪነት መብት ላይ የሚሠሩ 98 ማኅበራትን ፕላን ኢንተርናሽናል መድረሱን፣ ሆኖም ፕሮጀክቱ ሲያልቅ እንዳይበተኑ ለጋሽ ድርጅቶችና መንግሥት ድጋፍ እንዲያደርጉ ቅንጀቱ ጥሪ አቅርቧል፡፡

የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች አዋጅ ገቢ የማመንጨት ዕድል ቢሰጥም፣ የመነሻ ካፒታልና የቦታ እጥረት ችግር እንዳለ፣ ከጥገኝነት ለመላቀቅም ዕርዳታ እንደሚያስፈልግ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅት ባለሥልጣን ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ትዕግሥት ዳኝነት ገልጸዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የቤት ባለንብረቶች የሚከፍሉትን ዓመታዊ የንብረት ታክስ የሚተምን ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጀ

በአዋጁ መሥፈርት መሠረት የክልልና የከተማ አስተዳደሮች የንብረት ታክስ መጠን...

እንደ ንብረት ታክስ ያሉ ወጪን የሚያስከትሉ አዋጆች ከማኅበረሰብ ጋር ምክክርን ይሻሉ!

የመንግሥትን ገቢ በማሳደግ ረገድ አስተዋጽኦ እንዳላቸው የሚታመኑት የተጨማሪ እሴት...

ለዓለምም ለኢትዮጵያም ሰላም እንታገል

በበቀለ ሹሜ ያለፉት ሁለት የዓለም ጦርነቶች በአያሌው የኃያል ነን ባይ...