Tuesday, October 3, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየሆቴልና ቱሪዝም አሠሪዎች ፌዴሬሽን የአባላቱን ቁጥርን ሊያሰፋ ነው

የሆቴልና ቱሪዝም አሠሪዎች ፌዴሬሽን የአባላቱን ቁጥርን ሊያሰፋ ነው

ቀን:

  • አትሌት ኃይሌ ገብረ ሥላሴ በላይነህ ክንዴን ጨምሮ ሰባት የበላይ ጠባቂ አባላትን ሰይሟል

የኢትዮጵያ ሆቴል ቱሪዝም አሠሪዎች ፌዴሬሽን በሚል እንደ አዲስ ስያሜውን የቀየረው፣ በሆቴልና መሰል አገልግሎቶች ላይ የሚሠሩ ድርጅቶችና ማኅበራት ፌዴሬሽን፣ የአባላት ቁጥር ማስፋት ላይ ትኩረት ያደረገ የአምስት ዓመታት ስትራቴጂክ ዕቅድ ይፋ አደረገ፡፡

ፌዴሬሽኑ ስትራቴጂክ ዕቅዱን ይፋ ያደረገው፣ ነሐሴ 25 እና 26 ቀን 2015 ዓ.ም. በሐያት ሪጀንሲ ሆቴል፣ ባካሄደው ጠቅላላ ጉባዔ ላይ ሲሆን በሦስት ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ ቅድሚያ ሰጥቶ እንደሚሠራ የዕቅድ ሰነዱ ያትታል፡፡

በክልሎችና ከተሞች የሚገኙ የሆቴል ቀጣሪዎችን አባላት ቁጥር ማስፋፋት፣ የከተማዎች ሆቴል ማኅበራትንና ፌዴሬሽኑን አቅም ማሳደግ፣ እንዲሁም ውክልናውን በአገር አቀፍና በዓለም አቀፍ ኩነቶች ላይ ማፅናት ሦስቱና ዋነኞቹ ዕቅዶቹ ናቸው፡፡

ፌዴሬሽኑ በአሁኑ ጊዜ 15 ከተማን ማዕከል ያደረጉ ማኅበራትን በአባልነት ያቀፈ ሲሆን፣ በአምስት ዓመቱ ዕቅድ መጠናቀቂያ ላይም የአባላት ማኅበራትን ቁጥር ወደ 30 ለማሳደግ አቅዷል፡፡ አባል በሚሆኑት 30 ማኅበራት ውስጥም ወደ ሦስት ሺሕ የሚጠጉ የሆቴልና ቱሪዝም አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አባል እንደሚሆኑ ነው ስትራቴጂ ያቀደው፡፡

ስትራቴጂክ ዕቅዱ ይፋ ሲሆን የኢትዮጵያን ሆቴልና ቱሪዝም ዘርፉ አሁናዊ ሁኔታን፣ ያለውን አቅም፣ ያለበትን ተግዳሮቶችና መልካም አጋጣሚዎች የሚዳስስ ጥናት ቀርቦ ነበር፡፡ በክብር እንግድነትም የቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር ደኤታ አቶ ስለሺ ግርማና የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ደኤታ ተሻለ በሬቻ (ዶ/ር) ተገኝተው ነበር፡፡

ፌዴሬሽኑ ከምሥረታው ጀምሮ ለሰባት ዓመታት ይጠራበት የነበረውን (የኢትዮጵያ ሆቴልና መሰል አገልግሎት ሰጪ አሠሪዎች ፌዴሬሽን) የተሰኘውን ስያሜ፣ የዚህኛው ዓመት ጉባዔ ወደ (የኢትዮጵያ ሆቴልና ቱሪዝም አሠሪዎች ፌዴሬሽን) ቀይሮታል፡፡

ጉባዔው ፌዴሬሽኑን ለበርካታ ዓመታት በፕሬዚዳንትነት የመሩት ፍትሕ ወልደ ሰንበትን (ዶ/ር) በድጋሚ የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት አድርጎ የመረጠ ሲሆን፣ በአጠቃላይ 11 የቦርድ አባላትንም መርጧል፡፡

አዲሱ ቦርድ ፕሬዚዳንቱንና ሁለት ምክትል ፕሬዚዳንቶችን ጨምሮ፣ አቶ ሳሙኤል ታፈሰ ከአዲስ አበባና ሌሎች ከዘጠኝ ከተሞች የተውጣጡ አባላትን አካቷል፡፡

ፌዴሬሽኑ ለሆቴልና ቱሪዝም ዘርፉ ባደረጉት አስተዋጽኦና በፈጠሩት የሥራ ዕድል ሰባት አባላትን የያዘ የበላይ ጠባቂና የክብር አባላትንም ሰይሟል፡፡

አትሌት ኃይለ ገብረ ሥላሴን የበላይ ጥበቃ አድርጎ የሰየመ ሲሆን፣ አቶ ጀማል አህመድ፣ አቶ ታዲዎስ ጌታቸው፣ አቶ በላይነህ ክንዴ፣ ወ/ሮ ፀደይ አሥራትና አቶ ትዕዛዙ ከፌን የክብር አባላት አድርጓል፡፡ በቤተሰቦቻቸው እንዲወከሉ ያላቸውን አቶ በቀለ ሞላን ደግሞ የምንጊዜም የክብር አባል አድርጓል፡፡                 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ተመድንና ዓለም አቀፋዊ ሕግን ከእነ አሜሪካ አድራጊ ፈጣሪነት እናድን!

በገነት ዓለሙ በእኔ የተማሪነት፣ የመጀመርያ ደረጃ ተማሪነት ጊዜ፣ የመዝሙር ትምህርት...

የሰላም ዕጦትና የኢኮኖሚው መንገራገጭ አንድምታ

በንጉሥ ወዳጅነው ፍራንክ ቲስትልዌይት የተባሉ አሜሪካዊ ጸሐፊ ‹‹The Great Experiment...

ድህነት የሀብት ዕጦት ሳይሆን ያለውን በአግባቡ ለመጠቀም አለመቻል ነው

በአንድነት ኃይሉ ድህነት ላይ አልተግባባንም፡፡ ብንግባባ ኖሮ ትናንትም ምክንያት ዛሬም...