የምጣኔ ሀብት ባለሙያና የፖሊሲ አማካሪው ቆስጠንጢኖስ በርሀ ተስፋ (ዶ/ር)፣ የኢትዮጵያ ብሪክስ አባልነት ጥያቄ ተቀባይነት ማግኘትን አስመልክተው ለኢፕድ በሰጡት አስተያየት የተናገሩት፡፡ የምጣኔ ሀብት ባለሙያው አያይዘውም ከሙስና ጋር በተያያዘ ተገቢውን አገልግሎት የማይሰጡ ተቋማትና አመራሮች ኢንቨስተሮች በሚመጡበት ጊዜ ተገቢውን አገልግሎት ባለመስጠት እንቅፋት እንዳይፈጥሩ ትኩረት ሰጥቶ መሥራት ያስፈልጋልም ብለዋል። የብሪክስ አባል አገሮች በቴክኖሎጂ የበለጸጉ፣ ከፍተኛ ዕድገት ያስመዘገቡና በፍጥነት በማደግ ላይ ያሉ ብሎም ምርታቸውን በስፋት ወደ ሌሎች አገሮች በመላክ የሚታወቁ ናቸው ያሉት የፖሊሲ አማካሪው፣ ኢትዮጵያ ያላትን ከፍተኛ የእርሻ መሬትና የውኃ ሀብት በመጠቀም የኢንቨስትመት አጋርነቷን በማጠናከር ምርታማነትን ለማሳደግና ወደ ውጭ በመላክ ከፍተኛ ገቢ ማግኘት የሚያስችል አቅም መፍጠር ያስችላታል ብለዋል።