Tuesday, September 26, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናየአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ የአማራና የኦሮሚያ ግጭቶች በስምምነት እንዲፈቱ ለማሳሰብ ሊመጡ ነው

የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ የአማራና የኦሮሚያ ግጭቶች በስምምነት እንዲፈቱ ለማሳሰብ ሊመጡ ነው

ቀን:

የአፍሪካ ቀንድ የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ ማይክ ሐመር (አምባሳደር)፣ በአማራና በኦሮሚያ ክልሎች እየተካሄዱ ላሉት ግጭቶች አስማሚ መፍትሔ እንዲመጣ ለማሳሰብና የፕሪቶርያውን ግጭት የማስቆም ስምምነት አተገባበርን ማስቀጠል ላይ ለመወያየት ወደ ኢትዮጵያ ሊመጡ ነው፡፡

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ሰኞ ነሐሴ 22 ቀን 2015 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ፣ ልዩ መልዕክተኛው ከትናንት በስቲያ ከሰኞ ነሐሴ 29 ቀን እስከ ጳጉሜን 3 ቀን 2015 ዓ.ም. ድረስ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ለመነጋገር ወደ ናይሮቢና አዲስ አበባ ጉዞ ያደርጋሉ፡፡

ማይክ ሐመር በሁለቱ አገሮች በሚያደርጉት ቆይታም ከአገሮቹ መሪዎች፣ ከአፍሪካ ኅብረት አመራሮች፣ እንዲሁም ከምሥራቅ አፍሪካ በይነ መንግሥታት የልማት ድርጅትና ከተለያዩ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ኃላፊዎች ጋር ውይይት እንደሚኖራቸው በመግለጫው ተመላክቷል፡፡

ልዩ መልዕክተኛው በኢትዮጵያ በሚያደርጉት ቆይታ በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ ከተማ የተደረሰው የፌዴራል መንግሥትና የሕወሓት የግጭት ማስቆም ስምምነት አተገባበርን ማስቀጠል በሚመለከትም እንደሚወያዩ ተገልጿል፡፡

በተጨማሪም በአማራና በኦሮሚያ ክልሎች በተከሰቱ ግጭቶች፣ ለሰላማዊ ሰዎች ጥበቃ እንዲደረግ አስማሚ የሆነ መፍትሔ እንዲገኝ ማሳሰቢያ እንደሚሰጡ ተገልጿል፡፡

‹‹በአማራና በኦሮሚያ ክልሎች ለተከሰቱ ግጭቶች አስማሚ መፍትሔ እንዲመጣና የንፁኃን ደኅንነትም እንዲረጋገጥ ያሳስባሉ፤›› ሲል የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት መግለጫ ልዩ መልዕክተኛው በኢትዮጵያ ስለሚያደርጉት ቆይታ አስታውቋል፡፡

ልዩ ልዑኩ በሁለቱ አገሮች በሚያደርጉት ቆይታ ስለሱዳን ግጭት የሚወያዩ መሆኑን፣ በቀጣናዊና በዓለም አቀፍ ጥረቶችም በሱዳን ዴሞክራሲያዊ አስተዳደርና ተጠያቂነት እንዲመጣ እንደሚወያዩ በመግለጫው ተጠቁሟል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የቤት ባለንብረቶች የሚከፍሉትን ዓመታዊ የንብረት ታክስ የሚተምን ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጀ

በአዋጁ መሥፈርት መሠረት የክልልና የከተማ አስተዳደሮች የንብረት ታክስ መጠን...

እንደ ንብረት ታክስ ያሉ ወጪን የሚያስከትሉ አዋጆች ከማኅበረሰብ ጋር ምክክርን ይሻሉ!

የመንግሥትን ገቢ በማሳደግ ረገድ አስተዋጽኦ እንዳላቸው የሚታመኑት የተጨማሪ እሴት...

ለዓለምም ለኢትዮጵያም ሰላም እንታገል

በበቀለ ሹሜ ያለፉት ሁለት የዓለም ጦርነቶች በአያሌው የኃያል ነን ባይ...