Sunday, September 24, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየመንግሥት የጤና ተቋማት ያልከፈሉት የመድኃኒት ግዥ 1.3 ቢሊዮን ብር ውዝፍ ዕዳ እንዳለባቸው...

የመንግሥት የጤና ተቋማት ያልከፈሉት የመድኃኒት ግዥ 1.3 ቢሊዮን ብር ውዝፍ ዕዳ እንዳለባቸው ተገለጸ

ቀን:

የዩኒቨርሲቲ ሆስፒታሎችን ጨምሮ የመንግሥት የጤና ተቋማት ያልከፈሉት የመድኃኒት ግዥ 1.3 ቢሊዮን ብር ውዝፍ ዕዳ እንዳለባቸው፣ የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት አስታወቀ፡፡

አገልግሎቱ ማክሰኞ ነሐሴ 23 ቀን 2015 ዓ.ም. ለሪፖርተር እንደገለጸው፣ የ1.3 ቢሊዮን ብር ውዝፍ የመድኃኒት ግዥ ዕዳ እንዳልተከፈለና ዕዳቸውን ካልከፈሉት የመንግሥትና የጤና ተቋማት ውስጥ የዩኒቨርሲቲ ሆስፒታሎች ይገኙበታል፡፡

የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ንጉሤ፣ የመድኃኒቶች ግዥ ክፍያ የመፈጸም ችግር ሙሉ በሙሉ ያልተፈታ ቢሆንም፣ አንዳንድ የጤና ተቋማት የክፍያ ሥርዓታቸውን ማሻሻላቸውን ገልጸዋል፡፡

ከአንዳንዶቹ የጤና ተቋማት ጋር በመግባባት ክፍያ እንዲፈጽሙ መደረጉን፣ የቆየ ውዝፍ ዕዳ ያሉባቸውን ደግሞ በሕግ በመጠየቅ እንዲከፍሉ መደረጋቸውን ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ ገልጸዋል፡፡

ይሁን እንጂ አሁንም ቢሆን ለተቋሙ 1.3 ቢሊዮን ብር የመንግሥት ሆስፒታሎችና ሌሎች የጤና ተቋማት እንዳልከፈሉት አቶ ሰለሞን ገልጸዋል፡፡

ክፍያውን ካልፈጸሙ የመንግሥት ተቋማት ውስጥ ከ600 እስከ 700 ሚሊዮን የሚጠጋው ውዝፍ ያለባቸው በአዲስ አበባ የሚገኙ ሆስፒታሎች መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

አገልግሎቱ ከሆስፒታሎች ጋር ለመነጋገገር ለጤና ሚኒስቴር መረጃ መስጠቱን ምክትል ዳይሬክተሩ ጠቁመው፣ በሚኒስቴሩ ድጋፍ ለመክፈል መስማማታቸውን አስረድተዋል፡፡

በአንድና በሁለት ወራት ውስጥ ችግሩን በመፍታትና አሠራሩም በተገባለትና በተያዘለት በጀት የአቅርቦት ሥርዓት ለመዘርጋት እየተሠራ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

ባለፈው ሳምንት በአዲስ አበባ ከተማ ከሚገኙ ሆስፒታሎች ጋር አገልግሎቱ በነበረው ውይይት ወደ ውል መግባታቸውን፣ በስምምነቱም መሠረት አቅርቦቱን እንደሚጀምሩ ገልጸዋል፡፡

በዚህ ስምምነት መሠረት ለ28 ሆስፒታሎች በቅድመ ክፍያ ውል መድኃኒቶች ሊቀርብ መሆኑን፣ አገልግሎቱ ከሆስፒታሎቹ ጋር ውል የገባው ፍላጎትን መሠረት ያደረገ የአሠራር ሥርዓት እንደሚከተልና በኢትዮጵያ የሚታየውን የመድኃኒት አቅርቦት ችግር 80 በመቶ የሚፈታ ነው ተብሏል፡፡

አገልግሎቱ በግንቦት ወር በዘጠኝ ወራት ውስጥ ከ3.4 ቢሊዮን ብር በላይ ከጤና ተቋማት በዱቤ የሰጠውን ክፍያ መሰብሰቡን ገልጿል፡፡

አገልግሎቱ ከ2014 በጀት ዓመት ቀሪ ያልተሰበሰበ  ሒሳብና በ2015 በጀት ዓመት ከሰጠው 5,300,665,607 ብር ውስጥ ከሦስት ቢሊዮን ብር በላይ መሰብሰብ መቻሉን አስታውቋል፡፡  

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የቤት ባለንብረቶች የሚከፍሉትን ዓመታዊ የንብረት ታክስ የሚተምን ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጀ

በአዋጁ መሥፈርት መሠረት የክልልና የከተማ አስተዳደሮች የንብረት ታክስ መጠን...

እንደ ንብረት ታክስ ያሉ ወጪን የሚያስከትሉ አዋጆች ከማኅበረሰብ ጋር ምክክርን ይሻሉ!

የመንግሥትን ገቢ በማሳደግ ረገድ አስተዋጽኦ እንዳላቸው የሚታመኑት የተጨማሪ እሴት...

ለዓለምም ለኢትዮጵያም ሰላም እንታገል

በበቀለ ሹሜ ያለፉት ሁለት የዓለም ጦርነቶች በአያሌው የኃያል ነን ባይ...