በሃንጋሪ መዲና ቡዳፔስት ነሐሴ 13 ቀን የተጀመረው 19ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና፣ ዛሬ ነሐሴ 21 ቀን ፍጻሜውን ያገኛል፡፡ እስከ ነሐሴ 18 ሐሙስ ድረስ በነበረው የደረጃ ሠንጠረዥ አሜሪካ በ7 ወርቅ፣ 6 ብር፣ 6 ነሐስ ስትመራ፤ ስፔን በ4 ወርቅ፣ ጃማይካ በ2 ወርቅ፣ 3 ብር፣ 3 ነሐስ ሁለተኛና ሦስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ፡፡ እንግሊዝ በ2 ወርቅ፣ 2 ብር፣ 1 ነሐስ 4ኛ፣ ካናዳ በ2 ወርቅ 5ኛ ሲሆኑ፣ ኢትዮጵያ በ1 ወርቅ፣ 3 ብር፣ 2 ነሐስ 6ኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች፡፡ የቅዳሜና የእሑድ በ5000 ሜትርና በማራቶን በሁለቱ ጾታዎች የኢትዮጵያውያኑ አትሌቶች ውጤት የደረጃውን ሠንጠረዥ ሊቀይረው እንደሚችል ይጠበቃል፡፡ ፎቶዎቹ የዓለም ሻምፒዮናውን ሁነቶች በከፊል ያስቃኛሉ፡፡
ፎቶ የዓለም አትሌቲክስ