Wednesday, September 27, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊከሱዳንና ከተለያዩ አካባቢዎች ተፈናቅለው በጎንደር ከተማ የሚገኙ ተፈናቃዮች በከፍተኛ ችግር ውስጥ መሆናቸው...

ከሱዳንና ከተለያዩ አካባቢዎች ተፈናቅለው በጎንደር ከተማ የሚገኙ ተፈናቃዮች በከፍተኛ ችግር ውስጥ መሆናቸው ተጠቆመ

ቀን:

በዳንኤል ንጉሤ

በሱዳን ጦርነትና በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች በነበሩ የሰላም ዕጦቶች ምክንያት ተፈናቅለው በጎንደር ከተማ የሚገኙ ከአምስት ሺሕ በላይ ዜጎች በአስቸጋሪና የመሠረታዊ አገልግሎት ዕጦት ምክንያት እየተሰቃዩ መሆኑን፣ የጎንደር ከተማ አስተዳደር የተፈናቃዮች አስተባባሪ የሆኑት አቶ መላኩ ገብሬ ለሪፖርተር ገለጹ።

ኃላፊው እንዳሉት ከሱዳን ጦርነት ብቻ ተሰደው በጎንደር የሚገኙ ትውልደ ኢትዮጵያውን፣  አባወራዎች ከ1,442 እንደሚበልጡ ጠቅሰው፣ ከእነዚህም ውስጥ 975 የሆኑት ከአምስት ዓመት በታች ዕድሜ ያላቸው ሕፃናት፣ 50 አካል ጉዳተኞች፣ 417 የሚያጠቡ እናቶችና 256 ነፍሰ ጡሮች ይገኙበታል።

በተጨማሪም ከትግራይ፣ ከኦሮሚያና ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ በፀጥታ ችግር ምክንያት የተፈናቀሉ ዜጎች ከፍተኛ ቁጥር እንዳላቸው አቶ መላኩ ጠቅሰው፣ ለእነዚህ ሰዎች የሚሆን መሠረታዊ የምግብ፣ የመጠለያና የሕክምና አገልግሎት ማቅረብ ባለመቻሉ ስደተኞቹ ለከፋ ችግር መጋለጣቸውን ገልጸዋል።

‹‹ችግሩን ለሚመለከተው የክልሉ የምግብ ዋስትና ኮሚሽንና ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን በተደጋጋሚ አሳውቂያለሁ፤›› ያሉት አቶ መላኩ፣ ነገር ግን ከተሞቹ በጎ ምላሽ አለማግኘታቸውን ጠቅሰው፣ በአማራ ክልል ተከስቶ በነበረው የፀጥታ ችግር፣  ለተፈናቃዮቹ መታወቂያ ባለመሰጠቱ ምክንያት በፀጥታ አስከባሪዎች ከፍተኛ እንግልት እንደደረሰባቸው ጠቁመዋል።

‹‹እነዚህን ተፈናቃዮች ለማገዝ የጎንደር ከተማ አስተዳደር፣ ከክልሉ አስተዳደርና ከፌዴራል መንግሥት በጋራ መሥራት አለብን፤›› ያሉት አቶ መላኩ፣ በእነዚህ አካላት መካከል የተቀናጀ ሥራ ባለመኖሩ ስደተኞቹ ገፈት ቀማሾች እየሆኑ ስለሆነ፣ የሚመለከተው አካል በሙሉ እንዲደርስላቸው ጠይቀዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የአማራ ክልል ወቅታዊ ሁኔታ

እሑድ ጠዋት መስከረም 13 ቀን 2016 ዓ.ም. የፋኖ ታጣቂዎች...

ብሔራዊ ባንክ ለተመረጡ አልሚዎች የውጭ አካውንት እንዲከፍቱ ለመጀመሪያ ጊዜ የፈቀደበት መመርያና ዝርዝሮቹ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ አጠቃቀምንና ተያያዥነት ያላቸው ጉዳዮችን...

እነ ሰበብ ደርዳሪዎች!

ከሜክሲኮ ወደ ዓለም ባንክ ልንጓዝ ነው። ሾፌርና ወያላ ጎማ...