Tuesday, September 26, 2023
- Advertisment -
- Advertisment -

[ክቡር ሚኒስትሩ ከፖለቲካ አማካሪያቸው ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ እየተወያዩ ነው]

  • ክቡር ሚኒስትር ከማኅበረሰባችን በተለያየ መልኩ ከፍተኛ ተቃውሞ እየደረሰብን መሆኑ ሥጋት ፈጥሮብኛል።
  • አትሥጋ… መፍትሔ መፈለግ እንጂ መሥጋት ጥሩ አይደለም፡፡
  • ለመፍትሔውም እኮ አቅም ያስፈልጋል።
  • እንዴት? አቅም የለንም እያልክ ነው?
  • ክቡር ሚኒስትር ነገሩ የተለመደው የተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲዎች ጫና ሳይሆን ከፍተኛ የኢኮኖሚ አቅም የሚጠይቅ የማኅበረሰብ ተቃውሞ ነው።
  • እንደለመድከው የኑሮ ውድነቱ ከቁጥጥር ውጪ እየወጣ ነው ልትል ነው አይደል?
  • እሱ አንደኛው ነው ነገር ግን ሌላም ችግር ተከስቷል።
  • የምን ችግር?
  • የአፈር ማዳበሪያ ችግር።
  • የማዳበሪያ ችግር ዓለም አቀፍ እንጂ በእኛ ሀገር ብቻ የተከሰተ አለመሆኑን አታውቅም?
  • ቢሆንም ክቡር ሚኒስትር ይህንን ለአርሶ አደሩ ማስረዳት አስቸጋሪ ነው።
  • ለምን?
  • መሬቱን አባልጋችሁ ዛሬ ማዳበሪያ የለም ማለት አትችሉም ብሎ እያመጸ ነው።
  • እያመጸ ነው ማለት?
  • በተለያዩ አካባቢዎች ሰለማዊ ሠልፍ እየወጣ ሲሆን በአንዳንድ አካባቢዎች ደግሞ…
  • እ… በአንዳንድ አካባቢዎች ምን?
  • የማዳበሪያ መጋዘኖችን በመስበር መቆጣጠርና ያለውን ክምችት በራሱ መንገድ መከፋፈል ጀምሯል።
  • ከአርሶ አደሩ ያልተለመደ ፀባይ ነው።
  • ክቡር ሚኒስትር ይህንን ችግር ቶሎ መፍትሔ መስጠት ካልቻልን አደገኛ ልምምድ ነው። ለመንግሥት ሥልጣንም አስጊ ነው።
  • የመንግሥትን ሥልጣን ለምን ያሠጋል?
  • ክቡር ሚኒስትር በዚህ ሁኔታ ማለቴ ከከተማ እስከ ገጠሩ አርሶ አደር ተቃውሞ እያነሳብን ቀጣዩን ምርጫ እናሸንፋለን ብለው ያስባሉ?
  • አትጠራጠር!
  • እንዴት?
  • እኛ የዚህን አገር የፖለቲካ ውድድር ጣሪያ ከፍ አድርገነዋልና አትሥጋ፣ የሚደረስብን የለም።
  • እንዴት?
  • እኛ ያደረግነውን መፈጸም የሚችል ተፎካካሪ የለም።
  • ተፎካካሪ ፓርቲዎች ማድረግ የማይችሉት ምን የተለየ ነገር እኛ አደረግን።
  • ለባለቤቱ ስላማይታይ እንጂ ብዙ የተለዩ ነገሮችን አድርገናል።
  • ለምሳሌ ምን?
  • የደካሞችን መኖሪያ ቤት ማደስ።
  • እ…
  • ችግኝ መትከል
  • እ….
  • ማዕድ ማጋራት።
  • ክቡር ሚኒስትር አርሶ አደሩ እኮ የተቆጣው አሥግቶት ነው።
  • ምን አሥግቶት?
  • ማዕድ አጋሩኝ ማለት።

[ክቡር ሚኒስትሩ በአገሪቱ የተከሰተው ከፍተኛ የዋጋ ግሽበትን ለመቆጣጠር ያለመ ውይይት ከኢኮኖሚ ጉዳዮች አማካሪያቸው ጋር እያደረጉ ነው]

  • የዋጋ ግሽበትን ለመቆጣጠርና ወደ ነጠላ አኃዝ ለማውረድ ለሕዝብ ቃል ብንገባም ግሽበቱ ተባብሶ ቀጥሏል።
  • እውነት ነው ክቡር ሚኒስትር። ግሽበቱ ተባብሶ ቀጥሏል!
  • ተባብሶ መቀጠሉን እንድታረጋግጥልኝ አይደለም የጠራሁህ?
  • ገብቶኛል ክቡር ሚኒስትር። በፍጥነት መፍትሔ ካልሰጠነው ነገሮች ከቁጥጥራችን ውጪ ሊወጡ ይችላሉ፡፡
  • እሱን እንድትነግረኝ አይደለም የጠራሁህ!
  • ታዲያ ለምንድነው ክቡር ሚኒስትር?
  • መሠረታዊ ሸቀጦች ላይ የተጣሉ ቀረጥና ታክስ፣ በተለይም ቫት ቢነሳ ግሽበቱን መቆጣጠር ይቻላል ባልከው የመፍትሔ ሐሳብ መሠረት እንዲነሳ ተደረጓል ነገር ግን ግሽበቱ ተባብሶ ቀጥሏል።
  • እውነት ነው ክቡር ሚኒስትር። የመፍትሔ ሐሳቡ ይሠራል ብለን ቀረጥና ታክስ ብናነሳም የሸቀጦች ዋጋ ሊወርድ አልቻለም። እንደውም ተባብሶ ቀጥሏል።
  • እሱን እንድታረጋግጥልኝ አይደለም የጠራሁህ!
  • እሺ ለምንድነው?
  • ያቀረብከው ሐሳብ መፍትሔ ያመጣል ባልከው መሠረት በስድስት ወራት ውስጥ 18 ቢሊዮን ብር የሚሆን ቀረጥና ታክስ እንዳይሰበሰብ ተደርጎ ምርቶች እንዲገቡ ተደርጓል ነገር ግን የዋጋ ግሽበቱ ተባብሶ ቀጠለ እንጂ አልተረጋጋም።
  • እውነት ነው ክቡር ሚኒስትር። እንደተባለው 18 ቢሊዮን ብር የሚሆን ቀረጥና ታክስ እንዳይከፈል ቢደረግም የዋጋ ግሽበቱ ቀጥሏል።
  • እኮ ይህን ያህል ገቢ ቀሪ ተደርጎ እንዴት ዋጋ ማረጋጋት አልተቻለም?
  • እሱ የእኛም ጥያቄ ነው ክቡር ሚኒስትር። ነገር ግን የምጠረጥረው ነገር አለ።
  • ምንድነው የጠረጠርከው?
  • እኛ ቀረጥና ታክስ እንዳይከፈል ብንወስንም አስመጪዎቹ ግን ይከፍሉ እንደነበር እጠረጥራለሁ። ለነገሩ ጥርጣሬ ብቻ አይደለም።
  • እንዴት? ይከፍሉ ነበር እያልክ ነው?
  • ክቡር ሚኒስትር እኛ ቀረጥና ታክስ እንዲነሳ ብንወስንም ማዕከላዊ ባንኩ የዶላር ምንዛሪ ተመንን በየቀኑ ከፍ እያደረገ ስለነበር ቀረጥና ታክስ መነሳቱ ትርጉም አልነበረውም።
  • እንዴት? ምን አገናኘው?
  • አስመጪዎቹ ዶላር መንዝረው የዘይትና ሌሎች ሸቀጦች ግዥ ፈጽመው ሸቀጡ አገር ውስጥ ሲደርስ የዶላር ምንዛሪ ተመን በከፍተኛ ደረጃ ጨምሮ ያገኙታል።
  • እኮ ምን አገናኘው? ያስመጡትን ዘይት በዶላር አይሸጡ?
  • በዶላር ቢሸጡትማ ጉዳት አይገጥማቸውም ነበር።
  • ምን እያልክ ነው?
  • በመቶ ዶላር የገዙት ዘይት አዲስ አበባ ሲደርስ የመቶ ዶላር የብር ምንዛሪ አሻቅቦ ይጠብቃቸዋል። አሱ ላይ ትርፍ ጨምረው ዘይቱን ይሸጡታል። ስለዚህ የዘይትን ዋጋ ያስወደዱት አስመጪዎች ብቻ ናቸው ማለት አስቸጋሪ ነው።
  • አሃ… መንግሥት የዕለት ፍጆታ ሸቀጦችን በውጭ ምንዛሪ እያስገባ በጎን በኩል ደግሞ የብር የመግዛት አቅምን ማዳከም መቀጠሉ ትክክል አይደለም እያልክ ነው? አሁን እያልክ ያለኸው ገብቶኛል መሰለኝ፣ አይደል?
  • ልክ ነዎት ክቡር ሚኒስትር። ችግሩን በትክልል ተረድተውታል። በአጠቃላይ ከውጭ የሚገባ ዘይት ላይ መንግሥት ሳያውቀው ዋጋ እየጨመረ ነበር ማለት ይቻላል።
  • እህ… እና ምን ማድረግ ይሻላል ትላለህ?
  • የአጭር ጊዜ መፍትሔው የብር ምንዛሪን የማዳከም ሒደት ለጊዜው እንዲቆም ማድረግ ነው። ሌላው …
  • ሌላው የረዥም ጊዜ መፍትሔ ነው።
  • ምንድነው?
  • ቢያንስ የዕለት ፍጆታ ሸቀጦችን በአገር ውስጥ ማምረት ወይም መተካት ካልቻልን ከችግሩ በዛላቂነት መውጣት አንችልም። የዋጋ ግሽበት የአገሪቱ አዙሪት ሆኖ ይቀጥላል።

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች

- Advertisment -

ትኩስ ፅሁፎች

በቀይ ባህር ፖለቲካ ላይ በመከረው የመጀመሪያ ጉባዔ ለዲፕሎማቲክና ለትብብር አማራጮች ትኩረት እንዲሰጥ ጥሪ ቀረበ

ሰሞኑን በአዲስ አበባ ለመጀመርያ ጊዜ በቀይ ባህር ቀጣና የፀጥታ...

የቤት ባለንብረቶች የሚከፍሉትን ዓመታዊ የንብረት ታክስ የሚተምን ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጀ

በአዋጁ መሥፈርት መሠረት የክልልና የከተማ አስተዳደሮች የንብረት ታክስ መጠን...

እንደ ንብረት ታክስ ያሉ ወጪን የሚያስከትሉ አዋጆች ከማኅበረሰብ ጋር ምክክርን ይሻሉ!

የመንግሥትን ገቢ በማሳደግ ረገድ አስተዋጽኦ እንዳላቸው የሚታመኑት የተጨማሪ እሴት...

ለዓለምም ለኢትዮጵያም ሰላም እንታገል

በበቀለ ሹሜ ያለፉት ሁለት የዓለም ጦርነቶች በአያሌው የኃያል ነን ባይ...

የመጀመርያ ምዕራፉ የተጠናቀቀው አዲስ አበባ ስታዲየም የሳር ተከላው እንደገና ሊከናወን መሆኑ ተሰማ

እስካሁን የሳር ተከላውን ጨምሮ 43 ሚሊዮን ብር ወጪ ተደርጓል ዕድሳቱ...
spot_img

ተዛማጅ ፅሁፎች

[ክቡር ሚኒስትሩ ለሁለት ቀናት የተካሄደውን የፓርቲያቸውን የሥራ አስፈጻሚ ስብሰባ አጠናቀው ወደ ቢሯቸው ሲመለሱ ቢሯቸው ውስጥ አማካሪያቸው አንድ ጽሑፍ በተመስጦ እያነበበ አገኙት]

ምንድነው እንደዚህ መስጦ የያዘህ ጉዳይ? መጡ እንዴ ክቡር ሚኒስትር፣ የፓርቲው ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ያወጣውን መግለጫ እያነበብኩ ነው፡፡ ግን እኮ ፊትህ ላይ የመገረም ስሜት ይነበባል፡፡ አዎ፣ መግለጫው ላይ...

[ክቡር ሚኒስትሩ እየጠራ ያለውን ሞባይል ስልካቸውን ተመለከቱ፣ የህዳሴ ግድቡ ተደራዳሪ መሆናቸውን ሲያውቁ ስልኩን አነሱት]

ሃሎ... ጤና ይስልጥኝ ክቡር ሚኒስትር? ጤና ይስልጥልኝ ክቡር ተደራዳሪ... የጥረትዎን ፍሬ በማየትዎ እንኳን ደስ አለዎት፡፡ እንኳን አብሮ ደስ አለን፣ ምን ልታዘዝ ታዲያ? የውኃ ሙሌቱንና አጠቃላይ የግድቡን የግንባታ ሁኔታ...

[የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሩ ክቡር ሚኒስትር ሌሊቱን በእንቅልፍ ልባቸው በህልም እየተወራጩ ሳለ የሞባይል ስልካቸው ጥሪ አነቃቸው። አለቃቸው ስለነበሩ ስልኩን በፍጥነት አነሱት]

በሌሊት ስለደወልኩኝ ይቅርታ፡፡ ችግር የለውም ክቡር ሚኒስትር፣ ምን ልታዘዝ? አንድ የአውሮፓ ባለሥልጣን ነገ በጠዋት ወደ አዲስ አበባ ይገባል። እሺ። ሌሎች የመንግሥት አመራሮች ስላልቻሉ እርስዎ መንግሥትን ወክለው ቦሌ ኤርፖርት...