Sunday, September 24, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
- Advertisement -

ፌርማታ ፅሁፎች

ስኬታማ መሪዎች እንዴት ያሉት ናቸው?

ትኩስ ፅሁፎች

ስኬታማ መሪ ለመሆን ሁለንተናዊ ዕውቀትን ይጠይቃል፡፡ በመሪነት ዙሪያም ሆነ በተለያዩ ዘርፎች ሰፊ እውቀት ያስፈልጋል፡፡ ስኬታማ መሪዎች አንባቢዎች ናቸው፡፡ «They are Leading by Reading» አእምሮአቸውን ሁልጊዜ በማንበብ ያበለፅጋሉ፡፡ ግንዛቤያቸውን በማስፋት የመሪነት ብቃታቸውን ያሳድጋሉ፡፡ ስለሚያነቡ ነገሮችን ሰፋ ባለ መልኩ የማየት አቅማቸው ከፍተኛ ነው፡፡ ማንበብ እውቀት ይጨምራል፡፡ የሚያነብ መሪ መምራት አያስቸግረውም የሚባለውም ለዚሁ ነው፡፡

ስኬታማ መሪዎች የሌሎች መሪዎችን ታሪክ ያነባሉ፡፡ የስኬታማነታቸውን ምስጢር በማወቅ ራሳቸውን ያስተካክሉበታል ይማሩበታል፡፡ ስኬታማ መሪዎች ማንበብ ያፈቅራሉ፡፡ ማንበብ ራዕይን ያሰፋል፡፡ የተሻሻሉ ስትራቴጂዎችን ለመቅረፅ ያግዛል፡፡ ጠቃሚ አጋጣሚዎችን ለመለየት ያግዛል፡፡ ስኬታማ መሪዎች በማንበብ የፈጠራ ችሎታቸውን ያዳብራሉ፡፡ በራሳቸው የመተማመን ምንጩም እውቀታቸው ነው፡፡ የዘመኑን የመሪነት እውቀት ለመካን ሳያለሰልሱ ጥረት ያደርጋሉ፡፡ መጽሔት፣ ጋዜጣ መጽሐፍ እንዲሁም የተለያዩ ጥናቶች በማንበብ አቅማቸውን ይገነባሉ፡፡ በማንበብ እውቀትን ማስፋፋት ይቻላል፡፡ ትርጉም ያለው ሕይወት እንዲኖር ያደርጋል፡፡ ስኬታማ መሪዎች ከማንበብ ውጭ ሕይወት የላቸውም፡፡

  • መስፍን ባንታየሁ (ዶ/ር) ‹‹መሪነት›› (2000)
- Advertisement -
- Advertisement -

ተጨማሪ ለማንበብ

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች