Tuesday, September 26, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትየአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ከፈረንሣዩ የቴሌቪዥን ሥርጭት ካናል ፕላስ ጋር በአጋርነት ሊሠራ ነው

የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ከፈረንሣዩ የቴሌቪዥን ሥርጭት ካናል ፕላስ ጋር በአጋርነት ሊሠራ ነው

ቀን:

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ከፈረንሣዩ የቴሌቪዥን ሥርጭት ተቋም ካናል ፕላስ ጋር እንደሚሠራ አስታወቀ፡፡

ሰኞ ሐምሌ 17 ቀን 2015 ዓ.ም. የአጋርነት ስምምነት መደረጉን የገለጸው ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ፣ ከአጋር ድርጅቱ ጋር በጋራ በመሆን ከአትሌቲክስ ማሠልጠኛ ፕሮጀክቶች ጀምሮ እስከ ብሔራዊ ቡድን ድረስ በጋራ ለመሥራት የሚያስችል ውይይት ማድረጉን ጠቅሷል፡፡

በአጋርነት ስምምነቱ መሠረት፣ ካናል ፕላስ የብሔራዊ ፌዴሬሽኑ ስፖንሰር ከመሆን ባሻገር፣ በፌዴሬሽኑ የሚከናወኑ የአገር ውስጥ ውድድሮችን በጣቢያው የማስተላለፍ ዕቅድ እንዳለው ጭምር ተጠቁሟል፡፡

በአትሌቲክስ የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ እንዲቻል የራሱ አስተዋጽኦ እንደሚኖረውም ተጠቅሷል፡፡

ሁለቱ ተቋማት በቀጣይ በጋራ ሊሠሩት ያቀዱትን ዝርዝር ጉዳይ ይፋ እንደሚያደርጉ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ገልጿል፡፡  

በሌላ በኩል ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ ከአዋሽ ባንክ ጋር በአጋርነት ለመሥራት መወያየቱንና ባንኩ የፌዴሬሽኑ ስፖንሰር ለመሆን የሚያስችለው ስምምነት ላይ መድረሱ ተጠቅሷል፡፡

እ.ኤ.አ. በ1984 የቴሌቪዥን ሥርጭት የጀመረው ካናል ፕላስ በተለያዩ አገሮች ሥርጭት አለው፡፡ በአፍሪካ በተለይ በፈረንሣይኛ ተናጋሪ በሆኑ አገሮች ሥርጭቱ ይታወቃል፡፡ በክፍያ የተለያዩ የመዝናኛ ሥርጭቶችን የሚያቀርበው ጣቢያው በኢትዮጵያ ሥርጭቱን ከጀመረ ሦስት ዓመት ሊሆነው ነው፡፡

ድርጅቱ በቀጣይ ከብሔራዊ ፌዴሬሽኑ ጋር በሚኖረው ስምምነት መሠረት የአገር ውስጥ ውድድሮችን ማስተላለፍ ከቻለ በብሔራዊ ፌዴሬሽኑ ዘንድ የሚነሳው የበጀት እጥረት ጥያቄ ምላሽ ሊያገኝ እንደሚችል ይታመናል፡፡  

ይህም ፌዴሬሽኑ አትሌቲክሱን ወደ ገበያ ማውጣት የሚያስችለውን ዕድል ይፈጥርለታል ተብሏል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የቤት ባለንብረቶች የሚከፍሉትን ዓመታዊ የንብረት ታክስ የሚተምን ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጀ

በአዋጁ መሥፈርት መሠረት የክልልና የከተማ አስተዳደሮች የንብረት ታክስ መጠን...

እንደ ንብረት ታክስ ያሉ ወጪን የሚያስከትሉ አዋጆች ከማኅበረሰብ ጋር ምክክርን ይሻሉ!

የመንግሥትን ገቢ በማሳደግ ረገድ አስተዋጽኦ እንዳላቸው የሚታመኑት የተጨማሪ እሴት...

ለዓለምም ለኢትዮጵያም ሰላም እንታገል

በበቀለ ሹሜ ያለፉት ሁለት የዓለም ጦርነቶች በአያሌው የኃያል ነን ባይ...