የካህሊል ቀበሮ በጠዋት ተነስታ፣ ጀርባዋን ለፀሐይ ትሰጥና
ከትልቅ ተራራ ጫፍ ላይ ጉብ ትላለች። ከፊት ለፊቷ የተዘረጋ
ጥላዋን ስታይ እጅግ ግዙፍና ግርማ ሞገሳም ሆኖ ታገኘዋለች። በዚህ ጊዜ ‹‹በቃ፣ ዛሬ ምሳዬን ግመል ነው ምበላው!›› ብላ በኩራት ትናገራለች፡፡ ግመል ለማደን ስትኳትን ፀሐይ አናት ሆና ስለነበር ሐሩሯ እርግብግቢቷን ሊያፈነዳው ሲል እያለከለከች ትቆማለች፡፡ ጥላዋን ለማየት ድጋሚ ስታጎነብስ ሚጢጢ ሆኖ ይታያታል፡፡ ይብስ እያለከለከች ‹‹አይ አይጥ ይበቃኛል!››
- ማይንድሴት መጽሔት