Wednesday, September 27, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየሶደሬ ሪዞርትን አክሲዮኖች በ60 ሚሊዮን ብር መነሻ ዋጋ ለመሸጥ የወጣው ሐራጅ መታገዱ...

የሶደሬ ሪዞርትን አክሲዮኖች በ60 ሚሊዮን ብር መነሻ ዋጋ ለመሸጥ የወጣው ሐራጅ መታገዱ ተሰማ

ቀን:

በሳሙኤል ቦጋለ

በ60 ሚሊዮን ብር መነሻ ዋጋ የሶደሬ ሪዞርትን 60 ሺሕ አክሲዮኖች በሐራጅ ለመሸጥ፣ በፌዴራል ፍርድ ቤቶች ፍርድ አፈጻጸም ዳይሬክቶሬት ወጥቶ የነበረው ሐራጅ መታገዱ ታወቀ፡፡

የሶደሬ ሪዞርት ሆቴል ከመንግሥት ወደ ግል ከተዛወረ በኋላ በባለሀብቱ በአቶ ድንቁ ደያስ ይተዳደር የነበረ ሲሆን፣ ግለሰቡም የሚያስተዳድሩት ዲኢኬ ኦሮሚያ ቢዝነስ ኢንቨስትመንት ለመንግሥት መክፈል የነበረበትን ከፍሎ ባለመጨረሱ ነበር በሪዞርቱ ያለው የባለቤትነት ድርሻ እንዲሸጥ ተወስኖ የነበረው፡፡

ዲኢኬ የተሰኘው ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር የቅድመ ክፍያውን 35 በመቶ ከከፈለ በኋላ በየዓመቱ መክፈል የነበረበትን ግዴታ ባለመፈጸሙ፣ የሪዞርቱ ባለቤት የነበረው የመንግሥት የልማት ድርጀቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ (አሁን አስተዳደር) በፌዴራል የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት ክስ አቅርቦ ነበር፡፡

ፍርድ ቤቱም ሚያዝያ 26 ቀን 2015 ዓ.ም. በዋለው ችሎት እያንዳንዳቸው  አንድ ሺሕ ብር ዋጋ ያላቸው 60 ሺሕ አክሲዮኖችን፣ በአጠቃላይ በ60 ሚሊዮን ብር መነሻ ዋጋ በሐራጅ እንዲሸጡ ትዕዛዝ ሰጥቶ ነበር፡፡

የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ዳይሬክቶሬትም በትዕዛዙ መሠረት የሪዞርቱን ድርሻዎች በሐምሌ ወር የሐራጅ ሽያጭ ዝርዝሮቹ ውስጥ አካቶ የነበረ ሲሆን፣ ሐምሌ 13 ቀን 2015 ዓ.ም. ከረፋዱ አምስት ሰዓት ላይ ሽያጩን ለማካሄድ አቅዶ ነበር፡፡

የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኃላፊዎች ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ የፍርድ አፈጻጸሙ እንዳይካሄድ ዲኢኬ አቤቱታውን ለፍርድ ቤት አቅርቦ ፍርድ ቤቱም ሐራጁ እንዳይካሄድ ታግዷል፡፡

‹‹ዋነኛ ባለሀብቱ አቶ ድንቁ ደያስ ናቸው፡፡ ችግሩ የተፈጠረውም የገዙበትን ዋጋ በገቡት ውል መሠረት ስላልፈጸሙ ነው፤›› ሲሉ፣ የአስተዳደሩ ኃላፊዎች ተቋማቸው ወደ ፍርድ ቤት ሙግት የሄደበትን ምክንያት አስረድተዋል፡፡

‹‹የመጀመርያውን 35 በመቶ ቅድሚያ ክፍያ ተከፍሏል፡፡ ከዚያ በኋላ በየዓመቱ መከፈል የነበረበትን ሳይፈጸም ቀርቷል፤›› ያሉት አንድ ኃላፊ፣ በመጨረሻም ፍርድ ቤቱ በሐራጅ እንዲሸጥና ለአስተዳደሩ ገንዘቡ ገቢ እንዲደረግ መወሰኑን አስታውሰዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የአማራ ክልል ወቅታዊ ሁኔታ

እሑድ ጠዋት መስከረም 13 ቀን 2016 ዓ.ም. የፋኖ ታጣቂዎች...

ብሔራዊ ባንክ ለተመረጡ አልሚዎች የውጭ አካውንት እንዲከፍቱ ለመጀመሪያ ጊዜ የፈቀደበት መመርያና ዝርዝሮቹ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ አጠቃቀምንና ተያያዥነት ያላቸው ጉዳዮችን...

እነ ሰበብ ደርዳሪዎች!

ከሜክሲኮ ወደ ዓለም ባንክ ልንጓዝ ነው። ሾፌርና ወያላ ጎማ...