‹‹በምድር ላይ ስኖር አንድ የተረዳሁት ነገር ቢኖር በሀብታምና በደሀ መካከል ካለው ልዩነት ይልቅ በተማረውና ባልተማረው መካከል ያለው እጅግ የሰፋ መሆኑን ነው፤›› የሚለን ፌዶሮቭ፦ «የተማረው ከሥራ ይልቅ በማሰብ ላይ ይበረታል፤ ያልተማረው ብርታት ደግሞ ከማሰብ ይልቅ ሥራ ላይ ነው፡፡ ታዲያ የተማረውን ስለ ገነት ወይም ስለ ዘላለማዊ ሕይወት ብትነግረው ‘መጀመሪያ ላስብበት’ ይልሀል፡፡ አስቦበት ሲመለስ ደግሞ መልሱ ‘ገነት የሚባል ነገር የለም፤ ይልቅ ገነትን እዚሁ ምድር ላይ እንስራው’ ነው፡፡ ያልተማረው ለማሰብ ጊዜ ስለሌለው ገነት አለ የሚለው የአንተ ንግግር ለእሱ በቂው ነው፤ በዚያው እምነት ይኖራል፤ በዚያው እምነትም ይሞታል… ፌዶሮቭ ይሄን ጠይቆ ከሞት በኋላ ስለሚኖረን ሕይወት እንዲህ ይላል፡-
‹‹እኔ ለምሳሌ አንድ ሰው ነኝ፣ ማመን የምችለውም አንድ ነገር ነው፤ መሆንም የምችለው አንድ ነገር ነው፤ ገነት የሚገቡት ደግሞ የተመረጡት ናቸው፤ ካልተመረጥኩ የዘላለም እሳት ይጠብቀኛል፡፡ ትልቁ ጥያቄ ደግሞ ለመመረጥ የሚያበቃው መመዘኛ (Criteria) እንደ ሃይማኖቱ የተለያየ ከመሆኑ ላይ ነው፡፡ የአንዱ የገነት መግቢያ ለሌላው የገሃነም ደጅ ነው፡፡ ለአንዱ እግዚአብሔርን መምሰያ ለሌላው የሰይጣን ወንድምነት ይሆናል።
‹‹እንደ እኔ እምነት ዘላለማዊ መሆንና እግዚአብሔርን መምሰል ከፈለግን የጋራ ገነት መፍጠሩ የተሻለ ይመስለኛል፡፡ የእሱ ፈጣሪዎች ደግሞ እኛ የተማርነው ነን›› ይለናል፡፡
«እንግዲያውስ ስለዘላለማዊነት ንገረን?» በማለት ፌዶሮቭ ተጠየቀ፡፡
«እሱን እንድነግራችሁ መጀመሪያ አስቀድሞ የሞቱት ሲነሱ ማየት አለብኝ›› ብሎናል፡፡
«እግዚአብሔርን ስለመምሰልስ…?›› ተባለ፡፡
ሁላችንም የምንመስለው ሳይሆን የምንሆነው እንደ እግዚአብሔር ነው፡፡ ጨካኝም ብትሆን ደግ፤ ቁጡም ብትሆን ታጋሽ፤ የምትገድል፡፡ ብትሆን የማትገድል… እሱን ነው የምትሆነው… ምክንያቱም እግዚአብ ሁሉንም ነውና ብሏል፡፡
ፌዶሮቭ እግዚአብሔርን ስለመምሰል ባሰፈረው ሀተታ ደግሞ እግዚአብሔር ስጋና ደም የለውም ትላላችሁ እንግዲህ አስቀድሞ ሲፈጥራችሁ እሱን አስመስሎ ካልሰራችሁ – እሱን መምሰል ለምን ፈለጋችሁ? በማለት ይጠይቃል።
ጲላጦስ ‹‹ጥበብ››