Sunday, September 24, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዝንቅለይቅርታ የጠነከረ ልብ

ለይቅርታ የጠነከረ ልብ

ቀን:

 ለሥነ ጽሑፍ ሥራዋ ያለውን አድናቆት ሊገልጽላት፣ እንግሊዛዊ ባለ ቅኔና ጸሐፌ ተውኔት ሮበርት ብራውኒንንግ እ.ኤ.አ ጥር 10 ቀን 1845 ዓ.ም. ለባለ ቅኔዋ ኤሊዛቤት ባሬት ደብዳቤ ይጽፍላታል፡፡ የጀርባ ሕመም ለከፊል አካል ጉዳተኛነት የዳረጋት ኤሊዛቤት ባሬት በዚህ ጊዜ የ39 ዓመት ያላገባች ሴት ነበረች፡፡ እንዲህ የተጀመረው የደብዳቤ ልውውጥ አድጎ ከ19ነኛ ክፍለ ዘመን ታላላቅ የፍቅር ታሪኮች አንዱ ለመሆን ይበቃል፡፡

ሴት ልጃቸው በትዳር ተጣምራ ማየት አብዛኞቹን ወላጆች የሚያስደስት ቢሆንም፣ ኤሊዛቤት ግን ለዚህ አልታደለችም፡፡ ከእናቷ እልፈት በኋላ፣ አባቷ የቅርቡ ሰው፣ ምስጢረኛውና መመኪያው ስላደረጋት ተቃወመው፡፡ የሮበርት ብራውኒንግ ቤተሰብም ቢሆን በኤሊዛቤት አስተማማኝ ያልሆነ ጤንነት ላይ ጥርጣሬ አድሮባቸው ነበር፡፡ ከብዙ ደብዳቤዎች ልውውጥ በኋላ ጥንዶቹ መስከረም 12 ቀን 1846 ዓ.ም. በምስጢር ተጋቡ፡፡

      አንድ ወንድ ልጅም ወልደው የጋብቻቸውን ፍሬአማነት ቢያስመሰክሩም፣ ኤሊዛቤትና አባቷ ግን በጭራሽ አልታረቁም፡፡ ከሠርጋቸው በኋላ ጥንዶቹ ወደ ኢጣሊያ ተጉዘው ቀሪ ዘመናቸውን በዚያ መኖር ጀመሩ፡፡

       አባቷ ልጅነቷን ቢክዳትም ኤሊዛቤት ግን ከአባቷ ጋር ያላት ሕብረት እንዳይቋረጥ፣ ተስፋ ሳትቆርጥ በየሳምነቱ ደብዳቤ ብትጽፍለትም፣ አንድም ምላሽ አላገኘችም፡፡ ከ10 ዓመታት በኋላ በፖስታ አድራሻዋ አንድ ትልቅ ሳጥን መጣላት፤ በውስጡ ያገኘችው አንዳቸውም ሳይከፈቱ ለአባቷ የላከቻቸውን ደብዳቤዎች ነበር፡፡ ዛሬ እነዚህ ደብዳቤዎቿ በእንግሊዝኛ ሥነ ጽሑፍ ውስጥ ዘመን አይሽሬ ተብለው እጅግ በጣም ከሚወደዱት ውስጥ የሚመደቡ ናቸው፡፡ ወላጅ አባቷ ጥቂቱን እንኳ አንብቦት ቢሆን ከኤሊዛቤት ጋር የነበራቸው ሕብረት ሊታደስ ይቻል ነበር፡፡

      ከ15 ደስታማ የትዳር ዓመታት በኋላ ሰኔ 29 ቀን 1861 ዓ.ም. ኤሊዛቤት በሮበርት እቅፍ ውስጥ ለመጨረሻ አንቀላፋች፡፡

  • ኃይል ከበደ ‹‹ምስካይ›› (2004)
spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የቤት ባለንብረቶች የሚከፍሉትን ዓመታዊ የንብረት ታክስ የሚተምን ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጀ

በአዋጁ መሥፈርት መሠረት የክልልና የከተማ አስተዳደሮች የንብረት ታክስ መጠን...

እንደ ንብረት ታክስ ያሉ ወጪን የሚያስከትሉ አዋጆች ከማኅበረሰብ ጋር ምክክርን ይሻሉ!

የመንግሥትን ገቢ በማሳደግ ረገድ አስተዋጽኦ እንዳላቸው የሚታመኑት የተጨማሪ እሴት...

ለዓለምም ለኢትዮጵያም ሰላም እንታገል

በበቀለ ሹሜ ያለፉት ሁለት የዓለም ጦርነቶች በአያሌው የኃያል ነን ባይ...