መፍትሔ ከጠፋ፤ እንለያይ ሳሚኝ፤
እኔስ አበቃሁኝ፤ ከንግዲህስ ወዲያ የምሰጥሽ የለኝ፤
በሙሉ ልቦና ተደስቻለሁኝ በመለያየቴ፤
እንደዚህ በጥራት ነፃ በመውጣቴ፤
እጅ እንጨባበጥ፤ ቃል ኪዳናችንም ይሰረዝልን፤
ምናልባት ወደፊት ከተገናኘን፤
እንዳይታይብን በግንባራችን
አንዲትም ጠብታ ከቀድሞው ፍቅራችን ምንም ስላልቀረን።
ወደ ማብቃት ሲደርስ የፍቅሩ ሲቃ፤
ስሜት ድዳ ሆኖ እየዛለ ሲሄድ ትርታው ሲያበቃ፤
ቃሬዛው አጠገብ ተንበርክካ ዕምነት፤
ዓይኖቹን ከደነች ቅን የዋህነት፤
አሁንም ከፈለግሽ ተስፋ ስለሌለው ሁሉም ሲከዳው፤
ይቀናሽ ይሆናል፤ ከሞት ወደ ሕይወት ልታስመልሺው።
ከማይክል ድሬይተን (1563 -1631)
ስድ ትርጉም በከበደ ዳግማዊ