Tuesday, September 26, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናመንግሥት ላቀደው የሦስት ዓመት የኢኮኖሚ ፕሮግራም ማስፈጸሚያ 12 ቢሊዮን ዶላር ብድር ጠየቀ

መንግሥት ላቀደው የሦስት ዓመት የኢኮኖሚ ፕሮግራም ማስፈጸሚያ 12 ቢሊዮን ዶላር ብድር ጠየቀ

ቀን:

  • ብድሩን ለማግኘት የሚያስችል ድርድር በቅርቡ ይጀመራል ተብሏል

መንግሥት ለሁለተኛው አገር በቀል የኢኮኖሚ ፕሮግራም ማስፈጸሚያ 12 ቢሊዮን ዶላር የፋይናንስ ድጋፍ ጠየቀ፡፡

ለሦስት ዓመታት የሚቆየውን የኢኮኖሚ ፕሮግራም ለማስፈጸም ከሚያስፈልገው አጠቃላይ በጀት ውስጥ 12 ቢሊዮን ዶላር የሚሆነው ከዓለም የገንዘብ ድርጅት አይኤምኤፍ፣ ከዓለም ባንክና ኢትዮጵያ ያለባትን የውጭ ዕዳ መልሶ ከማሸጋሸግ ለማግኘት መታቀዱን፣ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የኢኮኖሚ ጉዳዮች አማካሪ አቶ ተክለ ወልድ አጥናፉ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

በተለይ በአሁኑ ወቅት የገንዘብ ተቋማቱ ዋነኛ ባለድርሻ ከሆኑት እንደ አሜሪካ፣ ፈረንሣይና የመሳሰሉት አገሮች ከኢትዮጵያ ጋር ያላቸው ግንኙነት በጣም ጥሩ እየሆነ በመምጣቱ፣ የብድርና የብድር ማሸጋሸጊያ ጥያቄው አስፈላጊው ድርድር ከተደረገበት በኋላ ይለቃል የሚል ተስፋ በኢትዮጵያ በኩል መኖሩን አቶ ተክለ ወልድ አስረድተዋል፡፡

የአሜሪካ በኮንግረስ ኢትዮጵያ ላይ ጥሎት የነበረውን ገደብ እ.ኤ.አ. በጁላይ ወር መጨረሻ ላይ ያነሳል ተብሎ እንደሚጠበቅ፣ ይህም ገንዘቡን ለማግኘት ወደ የሚያስችል ድርድር ለመግባት እንደሚያስችል ጠቁመዋል፡፡  

ይህ ያስፈልጋል ተብሎ የቀረበው የገንዘብ መጠን በአገር ደረጃ ከኤክስፖርትና ከሌሎች ምንጮች ከሚገኘው የውጭ ምንዛሪ ውጭ ያለውን ክፍተት ለመሙላት እንደሚውል ተናግረዋል፡፡

ይህንን ገንዘብ ለማግኘት ወሳኝ የሆነ ድርድር በቅርቡ እንደሚጀመር የገለጹት አቶ ተክለ ወልድ፣ የመጨረሻ ወሳኔ ላይ የሚደረሰውም ድርድሩ በሚያስገኘው ውጤት መሠረት ይሆናልም ብለዋል፡፡ ገንዘቡን ለማግኘት ኢትዮጵያ ከተቋማቱ የሚቀርቡ ጥያቄዎችን ሚዛናዊ በሆነ መንገድ ለማስተናገድ በሚያስችል ደረጃ ዝግጅት ተደርጎ ወደ ድርድር እንደሚገባም ገልጸዋል፡፡

 ከሚፈለገው ከ12 ቢሊዮን ዶላር ውስጥ ምን ያህል ሊገኝ እንደሚችል የተጠየቁት አቶ ተክለ ወልድ፣ ‹‹በእኛ ፕሮጀክሽን በእነሱና በእኛ መካከል የነበረው ክፍተት አሁን በጣም ጠቧል፡፡ ነገር ግን ገንዘቡ ብቻ ሳይሆን ከገንዘብ ጋር የሚመጡ መሥፈርቶች ስላሉ በዚህ ላይ ተከራክሮ መስማማት ያስፈልጋል፤›› ብለዋል፡፡

በተለይም ከውጭ ምንዛሪ ሥርዓት ላይ ሪፎርሙ ተግባራዊ በሚሆንበት የጊዜ ገደብ ላይ ከፍተኛ ክርክር ሊኖር እንደሚችል ገልጸዋል፡፡

በአጠቃላይ ድርድሩ እንደሚፈለገው ከሄደ የአውሮፓውያኑ ዓመት ከማለቁ በፊት ብድሩ ሊገኝ እንደሚችል ጠቁመዋል፡፡  

አሁን ያለው ሁኔታ ተስፋ ያለው ነው የሚባለውም ድርድሩ ከቆመበት እንዲቀጥል በር በመከፈቱና የገንዘብ ተቋማቱ የኢትዮጵያን ጥያቄ ለመመለስ ቀና ሆነው መገኘታቸው መሆኑን ያመለከቱት አቶ ተክለ ወልድ፣ በተለይ የአሜሪካ ኮንግረስ የተጣሉትን ገደቦች ካነሳ በሌሎች የመደራደሪያ ጉዳዮች ላይ ከሁለቱም ወገን ግማሽ መንገድ ድረስ ሄደው ጉዳዩን እንዲሳካ ማድረግ የሚችሉበት ዕድል መኖሩን አክለዋል፡፡

ድርድሩ ቀላል ባይሆንም እነሱ ገንዘበ ለመልቀቅ የሚጠይቋቸውን መሥፈርቶች በጥንቃቄ ዓይቶ ውሳኔ መስጠትን የሚጠይቅም መሆኑን፣ ነገር ግን እነሱ የጠየቁት ጥግ ድረስ መንግሥት እንደማይሄድ አቶ ተክለ ወልድ አስታውቀዋል፡፡

ለምሳሌ የውጭ ምንዛሪ ፖሊሲው በምን ዓይነት መንገድ ሊስተካከል እንደሚችልም በዚሁ ድርድር የሚወሰን ስለመሆኑ ጠቅሰዋል፡፡

ከዚህ ቀደም ከዓለም ባንክና የዓለም የገንዘብ ድርጅት ይሰጣል የተባለው ገንዘብ ሳይለቀቅ መቅረቱን ያስታወሱት አቶ ተክለ ወልድ፣ አሁን ስምምነት ላይ ከተደረሰ ከቀድሞ የተሻለ ገንዘብ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የቤት ባለንብረቶች የሚከፍሉትን ዓመታዊ የንብረት ታክስ የሚተምን ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጀ

በአዋጁ መሥፈርት መሠረት የክልልና የከተማ አስተዳደሮች የንብረት ታክስ መጠን...

እንደ ንብረት ታክስ ያሉ ወጪን የሚያስከትሉ አዋጆች ከማኅበረሰብ ጋር ምክክርን ይሻሉ!

የመንግሥትን ገቢ በማሳደግ ረገድ አስተዋጽኦ እንዳላቸው የሚታመኑት የተጨማሪ እሴት...

ለዓለምም ለኢትዮጵያም ሰላም እንታገል

በበቀለ ሹሜ ያለፉት ሁለት የዓለም ጦርነቶች በአያሌው የኃያል ነን ባይ...