Sunday, September 24, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
- Advertisement -

ፌርማታ ፅሁፎች

የስብሐት ተረቶች

ትኩስ ፅሁፎች

አንድ ቀን ስብሐት ገ/እግዚአብሔር ለአማጭነት ሽምግልና ይላካል። የላኩት ልጆች መጋባት ፈልገው የሴቷ አባት እንዲፈቅዱ ለወግ ያህል ሽምግልና ከሌሎች ሽማግሌዎች ጋር አጩት። ስብሐት “ሆድ ሲያውቅ ዶሮ ማታ” እንደሆነ ገብቶታልና በሽምግልና የሚጠፋው ጊዜና ጉልበት ከወዲሁ አድክሞታል። ሽማግሌዎቹ ልጅቷ ቤት ደርሰው በር ተከፍቶላቸው እንደገቡ አባቷ ይመጣሉ። ተጨባብጠው አረፍ እንዳሉ ስብሐት ተሽቀዳድሞ:-“የመጣነው ልጅዎትን አንድ የእኛ ልጅ ጠይቆ ነው። እዚህ ውስጥ እርስዎም ሆኑ እኛ ምንም መብት የለንም። እምቢ ቢሉ እንኳን እነሱ ለመጋባት ቆርጠው ጨርሰዋል። ስለዚህ ይጋባሉ። አሁን በከንቱ ከመታከት ደስ የሚለንን ሌላ ጨዋታ እየተጫወትን እንቆይ። ምን ይመስልዎታል” አለ። አባትየው ስብሐትን ያውቁት ኖሮ ስቀው “ጥሩ” አሉና ሌላ ጉዳይ ሲጨዋወቱ ቆዩ።

  • ዓለማየሁ ገላጋይ ‹‹ስብሐት ገብረእግዚአብሔር ሕይወትና ክህሎት››
- Advertisement -
- Advertisement -

ተጨማሪ ለማንበብ

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች