Tuesday, September 26, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትየኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ለኦሊምፒክ ጨዋታ ዝግጅቱን ጀመረ

የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ለኦሊምፒክ ጨዋታ ዝግጅቱን ጀመረ

ቀን:

የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን እ.ኤ.አ በ2024 በሚካሄደው የፓሪስ ኦሊምፒክ ጨዋታ ማጣሪያ ለመካፈል ዝግጅቱን ጀመረ፡፡ የማጣሪያ ጨዋታ ለማድረግ አሠልጣኝ ፍሬው ወልደ ገብርኤል ለ34 ተጫዋቾች ጥሪ አቅርቧል፡፡

የ2024 የኦሊምፒክ ጨዋታዎች የሴቶች እግር ኳስ አፍሪካ ዞን የመጀመርያ ዙር ማጣሪያ ድልድል ይፋ ሆኗል፡፡

የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን (ሉሲዎቹ) የመጀመርያ ዙር ማጣሪያውን ከቻድ አቻው ጋር የሚያደርግ ሲሆን፣ የደርሶ መልስ ጨዋታዎች ከሐምሌ 3 እስከ 11 ባሉት ቀናት ይካሄዳል፡፡

የሁለቱ አገሮች አሸናፊ በሁለተኛው ዙር ማጣሪያ ከናይጄሪያ ጋር የሚጫወት ይሆናል፡፡

 አሠልጣኝ ፍሬው ለ34 ተጫዋቾች ጥሪ ካደረገ በኋላ ማክሰኞ ሰኔ 13 ቀን 2015 ዓ.ም. ልምምድ ጀምረዋል፡፡

በሌላ በኩል በኬንያ አስተናጋጅነት የሚካሄደው የሴቶች ከ18 ዓመት በታች የሴካፋ ውድድር የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ዝግጅቱን መጀመሩን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል፡፡

በአሠልጣኝ እንዳልካቸው ጫካ  የሚመራው ብሔራዊ ቡድኑ፣ ውድድሩን ለማካሄድ ለ34 ተጫዋቾች ጥሪ ያደረገ ሲሆን፣ ከግንቦት 28 ቀን 2015 ዓ.ም. ጀምሮ ማረፊያቸውን በቱሊፕ ኦሊምፒያ ሆቴል በማድረግ ዝግጅታቸውን መጀመራቸው ተገልጿል፡፡

ብሔራዊ ቡድኑ ከመጨረሻው ስብሰብ ውስጥ ዘጠኝ ተጫዋቾችን በመቀነስ 25 ተጫዋቾችን መልምሎ ዝግጅቱን እያደረገ ነው፡፡

ዝግጅቱንም በኢትዮጵያ ስፖርት አካዴሚ እያከናወነ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ባህሩ ጥላሁን በቦታው በመገኘት ልምምዱን መመልከታቸው ጠቅስዋል፡፡

በኬንያ አስተናጋጅነት የሚካሄደው የሴካፋ ከ18 ዓመት በታች ሴቶች ውድድር ከሰኔ 17 ጀምሮ እንደሚካሄድ ተገልጾ የነበረ ቢሆንም፣ ወደ ሰኔ 22 መሸጋገሩን ሴካፋ ለአባል አገሮች አሳውቋል። በዚህ ውድድር ላይ እንደሚሳተፉ ያረጋገጡ አገሮችም አዘጋጇ ኬንያ፣ ኢትዮጵያ፣ ታንዛንያ፣ ኡጋንዳ፣ ቡሩንዲ፣ ጂቡቲና ዛንዚባር መሆናቸውን ሴካፋ አስታውቋል።

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የቤት ባለንብረቶች የሚከፍሉትን ዓመታዊ የንብረት ታክስ የሚተምን ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጀ

በአዋጁ መሥፈርት መሠረት የክልልና የከተማ አስተዳደሮች የንብረት ታክስ መጠን...

እንደ ንብረት ታክስ ያሉ ወጪን የሚያስከትሉ አዋጆች ከማኅበረሰብ ጋር ምክክርን ይሻሉ!

የመንግሥትን ገቢ በማሳደግ ረገድ አስተዋጽኦ እንዳላቸው የሚታመኑት የተጨማሪ እሴት...

ለዓለምም ለኢትዮጵያም ሰላም እንታገል

በበቀለ ሹሜ ያለፉት ሁለት የዓለም ጦርነቶች በአያሌው የኃያል ነን ባይ...