Sunday, September 24, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናመንግሥት ለውጭ አየር መንገዶች በአስቸኳይ 95 ሚሊዮን ዶላር እንዲከፍል ተጠየቀ

መንግሥት ለውጭ አየር መንገዶች በአስቸኳይ 95 ሚሊዮን ዶላር እንዲከፍል ተጠየቀ

ቀን:

የዓለም አቀፉ የአየር ትራንስፖርት ማኅበር (IATA)፣ የኢትዮጵያ መንግሥት እስካሁን ለውጭ አየር መንገዶች ያልከፈለውን 95 ሚሊዮን ዶላር የተከማቸ ዕዳ በአስቸኳይ እንዲከፍል ጠየቀ፡፡

ገንዘቡ የውጭ አየር መንገዶች በኢትዮጵያ ትኬት ሲሸጡና አገልግሎት ሲሰጡ ያመነጩት የሽያጭ ገቢ ሲሆን፣ አየር መንገዶች ገንዘባቸውን ወደ አገራቸው ለመውሰድ ወደ ዶላር ተቀይሮ እንዲሰጣቸው የሚያስገድድ ሕግ አለ፡፡ ይሁን እንጂ በኢትዮጵያ ባለው የውጭ ምንዛሪ እጥረት ምክንያት የኢትዮጵያ መንግሥት ግዴታውን መወጣት አልቻለም ተብሏል፡፡

‹‹የኢትዮጵያ መንግሥትና ብሔራዊ ባንክ በቂ ምንዛሪ ለአቪዬሽን ኢንዱስትሪ ክፍያ መበጀት ስላልቻሉ 95 ሚሊዮን ዶላር ተይዞ ቀርቷል፡፡ ይኼ ጥሩ ያልሆነ ምልክት ነው፡፡ ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ሕጎችን መከተል አለባት፡፡ ኢትዮጵያ ራሷም ከዚህ ሕግ ነው የምትጠቀመው፡፡ አትዮጵያ ገንዘቡን ካልከፈለች የአየር ግንኙነቷ አደጋ ሊገጥመው ይችላል፤›› ሲሉ የዓለም አቀፍ አየር ትራንስፖርት ማኅበር ዋና ዳይሬክተር ዊሊ ዊልሽ አስታውቀዋል፡፡ ማኅበሩ በአዲስ አበባ የሁለት ቀናት ስብሰባ እያደረገ ሲሆን፣ በየአገሩ ሳይከፈሉ በቀሩ የአየር መንገዶች ገንዘብ ጉዳይ አሳሳቢ መሆኑን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል፡፡

በዓለም ዙሪያ 2.5 ቢሊዮን ዶላር ሳይከፈል የቀረ የአየር መንገዶች ገንዘብ እንዳለ ተገልጾ፣ ከዚህ ውስጥ 1.8 ቢሊዮን ዶላር በአፍሪካ መንግሥታት የተያዘ ነው ተብሏል፡፡ በተለይ የናይጄሪያ መንግሥት 800 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ የውጭ አየር መንገዶችን ገንዘብ መክፈል ባለመቻል ዋናው ተወቃሽ ሆኗል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በበኩሉ የውጭ መንግሥታት ያልከፈሉት 180 ሚሊዮን ዶላር እንደተያዘበት አስታውቋል፡፡ ‹‹በተለይ በናይጄሪያ፣ በኤርትራና በሌሎች አገሮች የተያዘብን ገንዘብ ከፍተኛ ነው፡፡ እነዚህ አገሮች የዶላር እጥረት ልክ እንደ ኢትዮጵያ እያጋጠማቸው ስለሆነ ሊከፍሉን አልቻሉም፤›› ሲሉ ስማቸው እንዳይጠቀስ ያልፈለጉ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ኃላፊ ተናግረዋል፡፡

‹‹ኢትዮጵያ ያልከፈለችው 95 ሚሊዮን ዶላር ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር አይገናኛም፡፡ ገንዘቡን በምንዛሪ ቀይሮ ለውጭ አየር መንገዶች መክፈል ያለበት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ነው፤›› ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው በበኩላቸው፣ አየር መንገዱ በውጭ መንግሥታት የሚያዝበት ገንዘብ እየበዛ በመሆኑ፣ ከፍተኛ ችግር እየተፈጠረበት መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በዚህ ዓመት መጨረሻ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ 6.1 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ያገኛል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፣ ይህም ካለፈው ዓመት 20 በመቶ ከፍ ያለ እንደሆነ ታውቋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የቤት ባለንብረቶች የሚከፍሉትን ዓመታዊ የንብረት ታክስ የሚተምን ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጀ

በአዋጁ መሥፈርት መሠረት የክልልና የከተማ አስተዳደሮች የንብረት ታክስ መጠን...

እንደ ንብረት ታክስ ያሉ ወጪን የሚያስከትሉ አዋጆች ከማኅበረሰብ ጋር ምክክርን ይሻሉ!

የመንግሥትን ገቢ በማሳደግ ረገድ አስተዋጽኦ እንዳላቸው የሚታመኑት የተጨማሪ እሴት...

ለዓለምም ለኢትዮጵያም ሰላም እንታገል

በበቀለ ሹሜ ያለፉት ሁለት የዓለም ጦርነቶች በአያሌው የኃያል ነን ባይ...