Tuesday, September 26, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

የቻይና አምባሳደር በቻይና የፋይናንስ ድጋፍ በትግራይ የሚተገበሩ ፕሮጀክቶችን እንደገና ለማስጀመር ይሁንታ ሰጡ

ተዛማጅ ፅሁፎች

በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ዣኦ ዚዩዋን በትግራይ ክልል የተቋረጡ በቻይና መንግሥት ፋይናንስ የሚደገፉ ፕሮጀክቶችን እንደገና ለመጀመር፣ መንግሥታቸውን ፍላጎት እንዳለው አስታወቁ፡፡

የቻይናው አምባሳደር የኤምባሲውን ዲፕሎማቶችና በኢትዮጵያ የሚንቀሳቀሱ የቻይና ኩባንያ ተወካዮችን በመያዝ፣ በትግራይ ክልል ያደረጉትን የሁለት ቀናት ጉብኝት ማክሰኞ ሰኔ 13 ቀን 2015 ዓ.ም. አጠናቀዋል፡፡

የልዑካን ቡድኑ የትግራይ ጊዜያዊ ፕሬዚዳንት አቶ ጌታቸው ረዳን ጨምሮ ሌሎች ባለሥልጣናትን አግኝቶ በትግራይ ክልል ጦርነት ምክንያት የተቋረጡትን በቻይና የሚደገፉ ፕሮጀክቶች፣ ለአብነትም የመቀሌ የውኃ አቅርቦት ፕሮጀክትና የባቡር መሠረተ ልማት ግንባታዎችን ለማስቀጠል ፍላጎት እንዳላቸው ገልጸዋል፡፡

የትግራይ ክልል ባለሥልጣናት በበኩላቸው የቻይና ኩባንያዎች ወደ ሥራ እንዲገቡ ከክልሉ መንግሥት የሚፈልጓቸውን ማናቸውንም ድጋፎች ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን እንዳሳወቋቸው፣ የጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዚዳንት አቶ ጌታቸው ገልጸዋል፡፡

በተጨማሪም የቻይና ልዑካን ቡድን አባላት የፕሪቶሪያ ስምምነት የአገሪቱን ሰላም በሚያጠናክር መንገድ ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ እንዲሆን እንደሚደግፉም አስታውቀዋል፡፡

የቻይና መንግሥት በትግራይ ክልል የታቀዱ የማገገሚያና የመልሶ ግንባታ ጥረቶችን ለመደገፍ ዝግጁ መሆኑን አምባሳደሩ ከመግለጻቸው ባሻገር፣ በአቅም ግንባታ ጥረቶች፣ በልምድ ልውውጥና በአጭር ጊዜ የሥልጠና መርሐ ግብሮች ላይ የትግራይ ክልልን ለመርዳት ቁርጠኛ መሆናቸውን አክለዋል፡፡ የልዑካን ቡድኑ በትግራይ ክልል አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለሚገኙ ተማሪዎችም የምግብ ዕቃዎችን አቅርቧል፡፡

በቻይና መንግሥት የፋይናንስ ድጋፍ ከተጀመሩ ፕሮጀክቶች መካከል ግዙፉ የኮምቦልቻ ሃራ ገበያ – መቀሌ የባቡር መንገድ ዝርጋታ ተጠቃሽ ሲሆን፣ ፕሮጀክቱ የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ከመከሰቱ አስቀድሞ መቋረጡ ይታወሳል፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች