Tuesday, October 3, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዝንቅሁለት ተኩል የውስጥ ሱሪዎች ለአዲስአባ ውልታዎች

ሁለት ተኩል የውስጥ ሱሪዎች ለአዲስአባ ውልታዎች

ቀን:

የልዑል መኰንን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እዛ የጥቁር እንጀራ ግንፍልፍል እመሰለው መርካቶ ክፈፍ ላይ ነው የተሰየመው። ከትምህርት ቤቱ ዋና መግቢያ በኩል ያለው ሰፊ አስፋልት ወደ መሳለሚያና አቡነ ጴጥሮስ ይዘልቃል። በስተሰሜን በኩል በደረቅ ቂጣና በባይተዋርነት የተፈነከተ ጠላ የሚደማ የደሀ ወገን ሠፈር ነው። በስተምዕራብ የክፍለ ሀገር አውቶቡስ ማቆሚያ ነው….. በምሥራቅ በኩል ጠርዙ በሰው ዓይነ ምድር የተዘመዘመ ጠባብ የኮረኮንች መንገድ አለ ወደ አባ ኮራን ሠፈር የሚያዘልቅ። እዚህ አስፋልት መሃል ቢቆሙ ግንባርዎ ቀና ሲል የሚላተመው ከዘመን አመጣሽ ቆርቆሮ ቤቶች፣ ከዘመን አመጣሽ ሙዚቃ ቤቶች፣ ከዘመን አመጣሽ ጎተራዎች፣ ከዘመን አመጣሽ ቡና ቤቶች፣ ከዘመን አመጣሽ ፎቶ ቤቶች፣ ከዘመን አመጣሽ ሻይ ቤቶችና ከድንቅነሽ ጊዜ ጀምሮ ከነበረው የእንጦጦ ተራራ ሰንሰለት ጋር ነው … …፡፡

የምንተነፍሰው አየር እንደ ልዩ ወጥ ያደርገዋል። ውስጡ በርበሬ፣ ሽሮ፣ የሉካንዳ ሥጋና አጥንት፣ ሽንኩርት፣ ቅመማ ቅመም፣ ቤንዚንና የሚሞቅ ብረት ጠረን ያለበት (እንደ ኢያሱ ዓይነት ቀልደኞች ‘ብረት ቦዘና’ ይሉታል)… ሌላም የማልረዳው። እነዚህ ልዑል መኰንን ከመምጣቴ በፊት መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ የተማርኩት ባልቻ አባ ነፍሶ ነበር– እዛው ልደታ እሳቸው ያቋቋሙት ሠፈር። ከዛ ስምንተኛ እንማር የነበርነው ልጆች ሚኒስትሪ ወስደን ካለፍን በኋላ አብዛኞቹ የሰፈሬ ልጆች ማርታ ኦላናን ጨምሮ ሌላ ሁለተኛ ደረጃ ትምህር ቤት ሲመደቡ፣ እኔና በደንብ የማላውቃቸው ጥቂቶች ደ’ሞ ልዑል መኰንን አጠቃላይ ገባን  (ዕድል ይሁን በዘመድ አላስታውስም)። ከጓደኞቼ ከእንዳለ ኮሮጆ፣ ከሃና ሞሲሳ (ጎረምሶች በፈረንሳዩ ንጉሥ ሉዊ አሥራ አራተኛ ሚስት ስም ማሪያ አንቶይኔት ብለው የቀፀሏት ቆንጆ)፣ ከለምለም ትግሬዋና ከለምለም ሠንጋ ተራ፣ ከዮናታን (ኣጭር በመሆኑ ‘ናፖሊዎን’ ተብሎ ቅፅል ስም የተሰጠው) እናም ከአየለ ጋና መዝሙሮች መለየቱን አልወደድኩም ነበር።

ልዑል መኰንን ሁለተኛ ደረጃ ከገባሁ በኋላ ባልቻ ትምህርት ቤቴ ስትናፍቀኝ አልፎ አልፎ በዚያ በልደታ በኩል እሄዳለሁ፡፡ ባ’ቶቡስ የማልፍ ከኾነ እንኳን ወርጄ። ታዲያ ከግቢው ውጭ ቆሜ የረገበ ሽቦ አጥሩን ተደግፌ ተማሪ የሌለበትን ግቢ አያለሁ:፡
                        – አዳም ረታ ‹‹እቴሜቴ የሎሚ ሽታ››

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ተመድንና ዓለም አቀፋዊ ሕግን ከእነ አሜሪካ አድራጊ ፈጣሪነት እናድን!

በገነት ዓለሙ በእኔ የተማሪነት፣ የመጀመርያ ደረጃ ተማሪነት ጊዜ፣ የመዝሙር ትምህርት...

የሰላም ዕጦትና የኢኮኖሚው መንገራገጭ አንድምታ

በንጉሥ ወዳጅነው ፍራንክ ቲስትልዌይት የተባሉ አሜሪካዊ ጸሐፊ ‹‹The Great Experiment...

ድህነት የሀብት ዕጦት ሳይሆን ያለውን በአግባቡ ለመጠቀም አለመቻል ነው

በአንድነት ኃይሉ ድህነት ላይ አልተግባባንም፡፡ ብንግባባ ኖሮ ትናንትም ምክንያት ዛሬም...