ብሔራዊ ባንክ-የፋይናንስ ዘርፉ አቅርቦቱና ፍላጎቱ የተመጣጠነ እንዳልሆነም ተጠቁሟል
ከአንድ ባንክ በስተቀር ሌሎች ሁሉም የንግድ ባንኮች የጥሬ ገንዘብ እጥረት (ሊኪዩዲቲ) እንደሌለባቸው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ምክትል ገዢ አቶ ሰለሞን ደስታ አስታወቁ።
ምክትል ገዥው ዛሬ ለስድስተኛ ጊዜ በኢትዮጵያ ስካይላይት ሆቴል እየተከናወነ ባለው የምስራቅ አፍሪካ የፋይናንስ ስብሰባ(Summit”) እንደገለጹት፣ “የገንዘብ እጥረት አለ ከተባለም ሁለት ወይም አንድ ባንክ ላይ ነው” ብለዋል።
አቶ ሰለሞን የጥሬ ገንዘብ እጥረት እንዳለበት የጠቆሙትና ስሙን ለመጥቀስ ያልፈለጉት ባንክ ግን ማኔጅመንቱ ላይ ማስተካከያ የሚፈልግ መሆኑን ተናግረዋል።
ምክትል ገዢው ምንም እንኳን የጥሬ ገንዘብ እጥረት እንደሌለ ቢናገሩም ፣ አገሪቱ ከብዙ ነገር እንደመውጣቷ፣ ብዙ የገንዘብ ፍላጎት አለ።
ስለሆነም ኢኮኖሚውን ለማንቀሳቀስ የሚያስፈልገውን ነገር በአንድ ጊዜ ማቅረብ ለኢትዮጵያ ቀላል እንደማይሆንና የፋይናንስ ዘርፉ አቅርቦቱና ፍላጎቱ የተመጣጠነ አለመሆኑን በመግለጽ፣ ችግሩ መኖሩን አመላካች ሀሳብ ሰንዝረዋል።
የምስራቅ አፍሪካ የፋይናንስ ስብሰባ(Summit” ለስድስተኛ ጊዜ በኢትዮጵያ ስካይላይት ሆቴል እየተከናወነ ሲሆን፣ በጉባዔው የተመሰረከላቸው የሂሳብ ባለሙያዎች፣ መድን ሰጪዎች፣ የፋይናን ተቋማት ባለሙያዎችና ሃላፊዎች እንዲሁም ቴክኖሎጂ አቅራቢዎች ተገኝተዋል።