Wednesday, September 27, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊበዱር እንስሳት ሀብት ህልውና ላይ አደጋ የደቀነው ሕገ ወጥ ዝውውር

በዱር እንስሳት ሀብት ህልውና ላይ አደጋ የደቀነው ሕገ ወጥ ዝውውር

ቀን:

የዱር እንስሳትና ውጤቶቻቸው ሕገ ወጥ ዝውውር፣ ድንበር ዘለልና ዓለም አቀፋዊ ሆኗል፡፡ ከዚህ አንጻር ኢትዮጵያ ብቻዋን ዝውውሩን ተከላክላ ውጤታማ መሆን እንደሚያዳግታት ብዙዎች ተስማምተውበታል፡፡

ይህም በመሆኑ ከጎረቤት አገሮች ጋር በተደራጀና በቅንጅት የታገዘ እንቅስቃሴ ማድረግ፣ የመረጃና የተሞክሮ ልውውጥ ማከናወንና ትስስር መፍጠር በእጅጉ ወሳኝ ነው የሚል እምነት አሳድሯል፡፡

የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ኩመራ ዋቅጅራ እንደገለጹት፣ ኢትዮጵያ ከጎረቤት አገሮች ጋር የሚያዋስኗት ድንበሮቿ በጣም ሰፊ ከመሆኑም በላይ ኬላዎችና የሕግ ማስከበሩ ሥራ ክፍተት የሚታይበት ነው፡፡

ሕገወጥ አዘዋዋሪዎችም ይህንን ክፍተት በመጠቀም እየተንቀሳቀሱ መሆኑን ገልጸው ይህም ሆኖ ግን ለሕገ ወጡ እንቅስቃሴ የተጋለጡ የዱር እንስሳትና የዝውውሩ መነሻና መድረሻ ቦታዎች በውል ተለይተው መታወቃቸውን ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጵያን ጨምሮ ከተለያዩ ሰባት የአፍሪካ አገሮች የተወከሉ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሙያዎችና የሕግ ማስከበር ኃላፊዎች የተሳተፉበትና ለአምስት ቀናት በመካሄድ ላይ ያለውን የአቅም ግንባታ ሥልጠና አስመልክተው ዋና ሥራ አስፈጻሚው እንዳብራሩት፣ ለሕገ ወጥ ዝውውር ከተጋለጡት የዱር እንስሳት መካከል በዋናነት የአቦ ሸማኔ ግልገሎች ይገኙባቸዋል፡፡

ግልገሎቹ ከሶማሌ ክልል ተነስተው ወደ ሶማሊያ እንደሚሻገሩ፣ ከዚያም በሶማሌላንድ አድርገው ወደ ጂቡቲ እንደሚያቀኑና በስተመጨረሻም መዳረሻዎቻቸው ወደሆኑት የመካከለኛ ምሥራቅ አገሮች እንደሚገቡ ነው የተናገሩት፡፡

የዝሆን ጥርስና ፒንጉዬን የምትባል የአዕዋፋት ዝርያ ከደቡብ ክልል በአዘዋዋሪዎች ድንበር ከተሻገሩ በኋላ መዳረሻቸው የእስያ አገሮች እንደሆነ፣ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ባለው ኩምሩክ ደግሞ የነብር ቆዳና ተያያዥነት ያላቸው ነገሮች ወደ ሱዳን እንደሚገቡ ተናግረዋል፡፡

የዱር እንስሳትና የተፈጥሮ ሀብቶችን የሚያዘዋውሩት በሚገባ የተደራጁ ሕገወጦች መሆናቸውን ገልጸው በዚህ መልኩ የተደራጀውን ኃይል ለመከላከል ራስን አስቀድሞ ማደራጀትና ማጠናከር እንደሚገባ ሳይገልጹ አላለፉም፡፡

ከዋናው ሥራ አስፈጻሚው ማብራሪያ ለመረዳት እንደተቻለው፣ በዓለም ውስጥ ካሉት ወይም ተለይተው ከተያዙት 34 የብዝኃ ሕይወት ጥበቃ ማዕከላት ውስጥ ሦስቱ የሚገኙት በኢትዮጵያ ነው፡፡

ኢትዮጵያ በብዝኃ ሕይወት በዓለም አቀፍ ደረጃም የታወቀች ብትሆንም ከዘርፉ ያላት ተጠቃሚነት ግን እጅግ ደካማ መሆኑን ነው ዋናው ሥራ አስፈጻሚው የተናገሩት፡፡

እንደ ዋናው ሥራ አስኪያጅ አባባል፣ ትኩረት ይሻሉ ተብለው ከተለዩት አምስት ዋና ዋና የኢኮኖሚ ምሰሶዎች መካከል አንደኛው ቱሪዝም ሆኖ ተገኝቷል፡፡ ለቱሪዝም ዕድገት ወሳኝ ከሆኑትም ውስጥ የተፈጥሮ ቱሪዝም አንዱ ሲሆን ኢትዮጵያ ግን ከተፈጥሮ ቱሪዝም እስካሁን ድረስ አሟጣ አልተጠቀመችም፡፡

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን በዚህ ዙሪያ እየተከናወነ ያለው ሥራ በእጅጉ አበረታች ውጤት እየታየበት መምጣቱን፣ ወደፊትም ከዱር እንስሳት ሀብትም በቱሪዝም አማካይነት ኢትዮጵያ ተጠቃሚ የምትሆንበት ጊዜ ሩቅ እንደማይሆን ነው ያመለከቱት፡፡

የቱሪዝም ሚኒስትር ደኤታ አቶ ስለሺ ግርማ በበኩላቸው፣ የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን በጎረቤት አገሮች ከሚገኙ ተመሳሳይ ተቋማት ጋር በቅንጅትና በትብብር ለመሥራት እያደረገ ያለው እንቅስቃሴ ውጤታማ እየሆነ መምጣቱን ተናግረዋል፡፡

ይህ ዓይነቱም እንቅስቃሴ ድንበር ዘለል የሆኑ የዱር እንስሳት በጋራ ለመጠበቅ፣ ለመንከባከብና ተገቢውንም ቁጥጥር ለማከናወን ምቹ ሁኔታ መፍጠሩን ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ ቱሪዝም በታሪክና በባህል ላይ ትኩረት ያደረገ ሲሆን፣ በየገበያ ማዕከላቱም የሚገኙ ሥዕሎችና ቅርፃ ቅርፆች አብዛኞቹ በታሪክ እውነታው ላይ የተመሠረቱ፣ ባህልና ትውፊቶችን የሚያመላክቱ ሐውልቶች፣ ሕንፃዎችና ሙዚየሞች ያሉባቸው መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ከኢትዮጵያ፣ ኬንያ፣ ዑጋንዳ፣ ኤርትራ፣ ሶማሊላንድ፣ ጂቡቲና ደቡብ ሱዳን የተውጣጡ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሙያዎች፣ የጉምሩክና የፀጥታ ተቋማት የተሳተፉበትን ሥልጠና ያዘጋጁት የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣንና ዓለም አቀፍ የዱር እንስሳት ፈንድ ናቸው፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የአማራ ክልል ወቅታዊ ሁኔታ

እሑድ ጠዋት መስከረም 13 ቀን 2016 ዓ.ም. የፋኖ ታጣቂዎች...

ብሔራዊ ባንክ ለተመረጡ አልሚዎች የውጭ አካውንት እንዲከፍቱ ለመጀመሪያ ጊዜ የፈቀደበት መመርያና ዝርዝሮቹ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ አጠቃቀምንና ተያያዥነት ያላቸው ጉዳዮችን...

እነ ሰበብ ደርዳሪዎች!

ከሜክሲኮ ወደ ዓለም ባንክ ልንጓዝ ነው። ሾፌርና ወያላ ጎማ...