Sunday, September 24, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ኪንና ባህልቀድሞ የመጣው የዝናቡ ኮቴና ብሂሉ  

ቀድሞ የመጣው የዝናቡ ኮቴና ብሂሉ  

ቀን:

በየካቲት መገባደጃ በቀላሉ የጀመረው የዘንድሮ የፀደይ (በልግ) ዝናብ፣ ከመጋቢት እስከ ግንቦት ዘልቋል፡፡ የፀሐይ ወር የነበረውና አርሶ አደሩ በቅጡ ፀሐይነትዋን የሚፈልግባት ግንቦት እንደወትሮው ሳትሆን በዝናብ ተረስርሳ አልፋለች፡፡ ሰኔ ከባተ አንደኛው ሳምንት ላይ ሆኖ ዝናቡም አልፎ አልፎ እየቀጠለ ቢሆንም ለሚቀጥሉት አሥር ቀናትም  ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አስታውቋል፡፡

ዛፍና ብሂሉ

‹‹ሰኔ ደግሞ መጣ ክረምት አስከትሎ

ገበሬው ተነሳ ማረሻውን ስሎ፤

ሐምሌም ተከተለ ገባ ዝናብ ጭኖ

ቀንና ሌሊቱን በዝናብ ጨፍኖ፡፡››

ከአንድ የግጥም ገበታ የተገኘው ይህ አንጓ የኢትዮጵያን ወርኃ ክረምት የያመቱን ገጽታ የሚያንፀባርቅ ነው፡፡ አርሶ አደሩ በክረምት ወቅት ከፊሎቹ አዝርዕት በሰኔ፣ ገሚሶቹን በሐምሌ እንዲሁም ሌሎቹን ደግሞ በነሐሴና በመስከረም ይዘራል፡፡ አትክልቱንም ይተክላል፡፡

ክረምቱን ተከትሎ የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች በየአካባቢያቸው ከቀደመው ጊዜ ጀምሮ ችግኝ የመትከል ልማድ እንዳለ ይታወቃል፡፡  በኢትዮጵያ ሚሌኒየም ክብረ በዓል አጋጣሚ  በሦስተኛው  ሺሕ  መቀበያ  ዋዜማ ‹‹ሁለት ዛፍ  ለሁለት ሺሕ››  እና  ‹‹ሦስት  ዛፍ ለሦስት ሺሕ›› በሚል  መሪ ቃል የችግኝ  ተከላው በወቅቱ መከናወኑ ይታወሳል፡፡

ልጄ ብቻ  አይደለም  ትምህርት  የሚያስፈልገው ደጄም ዛፍ  ማግኘት አለበት በሚል  መነሻም ‹‹ትምህርት ለልጄ፣ ዛፍ ለደጄ››  የሚለው  ብሂልም ተንፀባርቆ ነበር፡፡

ከቅርብ ዓመታት ወዲህ  መንግሥት በተለመው መርሐ ድርጊት መሠረት ‹‹የአረንጓዴ አሻራ ቀን›› በሚል መጠሪያ አገር አቀፍ ችግኝ ተከላ በመከናወን ላይ ይገኛል፡፡  የአገሪቱንና ደንና የአየር ንብረት ይዞታ እንዲያገግም ለማድረግ የታለመው የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር በየዓመቱም እንደቀጠለ ነው፡፡

ከሦስት ወራት በላይ በሚዘልቀው ወርኃ ክረምት መካከል የሚገኘው «የዛፍ ሳምንት» የሚከበርበት ሐምሌ ገናን ወር ነው፡፡ በአርሶ አደሩ «የክረምት ንጉሥ»ም ዛፍ ከችግኝነት አልፎ እንዲያብብም ያደርጋል ይባላል፡፡

በተለያዩ የዓለም ክፍል ኅብረተሰቦች ዘንድ ለዛፎች ልዩ ክብር እንደሚሰጡ በየአገሮቻቸው ሊቃውንት ስለዛፍ ከተነገሩ ቁምነገሮች መረዳት ይቻላል፡፡ የሥነ ሕይወት ባለሙያው ለገሠ ነጋሽ (ፕሮፌሰር) ካጠናቀሩት የሚከተሉት ተጠቃሾች ናቸው፡፡ «የዛፍ ምስጢሩ ውበቱ ብቻ ሳይሆን፣ ተስፋን ማጫሩ፣ ሕይወትን ማደሱ ነው»፣«እውነትን መሻት ጥሩ ነው፤ የበለጠ ጥሩው ግን ስለዛፍ እውነቱን መናገር ነው»፣     «ሠርግ ደግስ፣ ደስታህ ያንድ ቀን ነው፤ ተሾም ተሸለም፣ ደስታህ ያንድ ወር ነው፤ ዛፍ ትከል፣ ደስታህ የዕድሜ ልክ ነው»፡፡

አንድ ጸሐፊ፣ ኤመርሰን ‹‹በዛፎች  ስታጀብ  በጥበብና  በእምነት  እታጀባለሁ፤››  ብሎ የተናገረውን  ተንተርሶ፣  በጥበብና  በእምነት ለመታጀብ  ከፈለግህ ዛፍን  በተለይም  አገር በቀሉን እንትከል ብሏል፡፡

ዛፍ ከባህልና ከኪነ ጥበባት ጋርም የተቆራኘ በተረትና ምሳሌ የመገለጽ ዕድሉም የጎላ ነው፡፡ በኢትዮጵያውያን ዘንድ ዛፍ ትእምርታዊ ነው፡፡ የቤተሰብን መሠረት፣ የመኖሪያ አካባቢን በማጠናከር ረገድ ይጠቀሳል፡፡

ዛፍ የተለያየ ዓይነት ዝርያ እንዳለው ሁሉ አንዱ ከአንዱ ልዩነት ያለው በመሆኑም ለተለየ አገልግሎት የሚመረጥ ይሆናል፡፡ ከሰዎችም የሚለዩ በሥልጣን በእውቀት ወይም በሹመት የሚመረጡ ልሂቃንም ይኖራሉና፡፡ «ከሰው መርጦ ለሹመት፣ ከዛፍ መርጦ ለታቦት» የተሰኘውን አነጋገር አትርፎለታል፡፡

ኢትዮጵያ የነበራት የዛፎች ብርካቴ እየመነመነ ሄዶ መልክዓ ምድሩ መራቆቱን ደኑም መጨፍጨፉ በኅብረተሰቡም ጸዋትወ መከራ መዝለቁን ያስተዋለው አገሬው እንዲህ በሰምና ወርቅ ተቀኘ፡-

«ቆረጡት ቆረጡት

ዋርካውን ቆረጡት

ዝግባውን ቆረጡት

እነዛፍ አያውቁ

ምን ያፈራ ይሆን

ብለው ሳይጠይቁ፡፡»

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የቤት ባለንብረቶች የሚከፍሉትን ዓመታዊ የንብረት ታክስ የሚተምን ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጀ

በአዋጁ መሥፈርት መሠረት የክልልና የከተማ አስተዳደሮች የንብረት ታክስ መጠን...

እንደ ንብረት ታክስ ያሉ ወጪን የሚያስከትሉ አዋጆች ከማኅበረሰብ ጋር ምክክርን ይሻሉ!

የመንግሥትን ገቢ በማሳደግ ረገድ አስተዋጽኦ እንዳላቸው የሚታመኑት የተጨማሪ እሴት...

ለዓለምም ለኢትዮጵያም ሰላም እንታገል

በበቀለ ሹሜ ያለፉት ሁለት የዓለም ጦርነቶች በአያሌው የኃያል ነን ባይ...