መሰንበቻውን ‹‹ኢሄው ላዴ›› የተሰኘ የበጎ አድራጎት ማኅበር፣ በሥልጤ ዞን የበርበሬ ወረዳ የሙጎ ቀበሌ አካባቢ ዘመናዊ ትምህርት እንዲገባ፣ የበጎ አድራጎትና ልማት እንዲስፋፋ ላደረጉት ሐጂ ስርጋጋ ዳሪ፣ ‹‹የአገር ባለውለታና የልማት አርበኛ›› በማለት የምሥጋናና የዝየራ ሥነ ሥርዓት ግንቦት 27 ቀን 2015 ዓ.ም. አድርጎላቸዋል፡፡ ላበረከቱት የላቀ አስተዋጽኦም በሥልጤ ባህል ‹‹ገራድ›› በሚል የሚታወቀውን ማዕረግም በአገር ሽማግሌዎች ተሰጥቷቸዋል፡፡ ማዕረጉም የሽማግሌዎቹ አውራ፣ የገራድ ስርጋጋ ዳሪን ቀኝ ጆሮ በመያዝ (በፎቶው እንደሚታየው) እና በመመረቅ ሰጥተዋቸዋል፡፡
- ፎቶ ታምራት ጌታቸው