Sunday, September 24, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
- Advertisement -

ፌርማታ ፅሁፎች

ወደ ገሃነም ሄዶ የሆነውን መሆን

ትኩስ ፅሁፎች

ሰማህ! አንተ ሰው፤ አንተ መሬት ነህ የተባልኸው ምን ልታበቅል ነው? ወይስ ምን ሊበቅልብህ ይሆን? ሃይማኖትን ልታበቅልና ሃይማኖት ሊበቅልብህ ነው እንጂ መሬት የተባልኸው እንደ ትቢያ በንነህ ልትቀር አይደለም፡፡

አንተነትህን ትተህ የክፋትና የተንኮል የክህደትና የወንጀል መብቀያ ልትሆን ትፈልጋለህ፡፡ መሬት እንደመሆንህ መጠን ወደ መሬት ተመላሽ ነህና መልስ በተጠራህ ጊዜ እነማን ይሆኑ የሚከተሉህ?

ኧረ ለመሆኑ ሰውን በፍጡርነቱ የሚያስገድደው ግዳጅ ምንድን ነው? የሰው ዋና ግዴታው ሃይማኖት አይደለምን? እንዲህ ከሆነ ሰው ሃይማኖቱን እንደ ቀላል ነገር ለምን ይመለከተዋል? ደግ ነገር የማይጠራለት ይህ ዓለም እያታለለው ይሆን፡፡

ይህ አሮጌው ዓለም እንዳያታልለው የፊተኛይቱ ሰማይና የፊተኛይቱ ምድር ታልፋለች ተብሎ የለምን፡፡ ታዲያ በነሱ ፋንታ ሌላ ምን ሊተካ ይሆን? በእነሱስ ፋንታ አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር ይተካል ሲል ዮሐንስ በራዕይ ነግሮናል፡፡

ኧረ የሆነስ ሆነና በዚህ አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር የሚኖርበት ማነው? የሚኖርበት ያው ሰው ነዋ!! ሌላ ማን ይመጣል? አሄሄ አሄሄ!! ታዲያ ምን ትለኛለህ? ይህን አዲስ ዓለም እንደገና ሰውማ ከወሰደው ያው የተሰለቸው የሰው ተንኮል ተከትሎ ሊሄድ አይደለምን? ሰው የሚኖርበት ቦታ እንደምን ደግ ሊሆን ይችላል?

ሁለት ሰዎች ስለዚሁ ነገር ሲወያዩ አንደኛው ወደ መንግሥተ ሰማያት ከመግባትና ወደ ገሃነም ከመውረድ የትኛው ይሻላል ቢለው ሁለተኛው ሲመልስ በመንግሥተ ሰማያት ለብቻ ከመኖር ሰው ወደ መላበት ወደ ገሃነም ሄዶ የሆነውን መሆን ይሻላል አለው ይባላል፡፡

  • ብላታ ወልደ ጊዮርጊስ ወልደ ዮሐንስ ‹‹አምስት መንገደኞች›› (1954)  
- Advertisement -
- Advertisement -

ተጨማሪ ለማንበብ

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች