Sunday, September 24, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
- Advertisement -

ፌርማታ ፅሁፎች

ዲቪ ሎተሪ

ትኩስ ፅሁፎች

ምን ዓይነት ዘመን ነው የጉድ የፈንጣጣ

አንዱም ልውጣ ይላል አንደኛው ሲመጣ

ያኛው መረረኝ ሲል ካገሩ ሊወጣ

እኔስ የፈራሁት ያ ሲከንፍ ይህ ሲከንፍ

ሰዎች በጉዞ ላይ እንዳንተላለፍ

   እኔስ የፈራሁት አለ አንድ ነገር

   ሁሉም ሂዶ ሂዶ ቤቱ ብቻ እንዳይቀር

    ካልያም የሔደው ሁሉም ተመልሶ

    አውሮፓ ኒዮርክ ቤሩት ቢሆን ፈልሶ

ሰፋፊው ጎዳና የሚጠርገው ሲያጣ

ስደተኛው ሁሉ ሀገሩ ሲመጣ፡፡

የዲቪ ሎተሪ በብዛት መጣልን

ይኸው ሠልፍ ይዘናል በየፖስታ ቤት

ሴቶችና ወንዶች ወጣት አዛውንት

አግብተን የፈታን አምና እንደሄዱት

ዲቪዋን ቢደርሰን እንደታደሉት

በጠዋት ተስለናል ለሚሰማን ጌታ

በሩቅ ለሚታየን ባሕር ማዶ ፌሽታ፡፡

  • አሥራት አንለይ ‹‹የመጀመሪያዪቱ›› (2000)
- Advertisement -
- Advertisement -

ተጨማሪ ለማንበብ

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች