Wednesday, September 27, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትዋሊያዎቹ በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ማላዊን ይገጥማሉ

ዋሊያዎቹ በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ማላዊን ይገጥማሉ

ቀን:

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን (ዋሊያዎቹ) በአይቮሪኮስት ለሚከናወነው የ2024 የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ ማጣሪያ ጨዋታ ማላዊን ይገጥማል፡፡

ብሔራዊ ቡድኑ የምድቡ አምስት ጨዋታውን ሰኔ 13 ቀን 2015 ዓ.ም. የሚካሄደውን በሞዛምቢክ ነው፡፡

የማጣሪያ ጨዋታውን ለማድረግም ለ23 ተጫዋቾች ጥሪ ተደርጎ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ልምምድ ማድረግ ጀምረዋል፡፡

በኢትዮጵያ የካፍ መሥፈርትን ያሟላ ስታዲየም ባለመኖሩ፣ ዋሊያዎቹ አቻቸውን በሞዛምቢክ ስታዲየም ያስተናግዳሉ፡፡

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከወራት በፊት የቡድኑ ዋና አሠልጣኝ የነበሩትን ውበቱ አባተ በማሰናበቱ በምትካቸውም የብሔራዊ ቡድኑን ቀሪ ጨዋታዎች እንዲመሩ የፌዴሬሽኑ የቴክኒክ ዳይሬክተር ኢንስትራክተር ዳንኤል ገብረ ማርያምን ዋና አሠልጣኝ ማድረጉ ይታወሳል፡፡

በሌላ በኩል አሠልጣኝ ደግአደረገ ይገዛውን ረዳት አሠልጣኝ፣ ውብሸት ደሳለኝ የግብ ጠባቂ አሠልጣኝ ተደርገዋል፡፡

ብሔራዊ ቡድኑ ከማላዊ ጨዋታ በኋላ የመጨረሻውን የምድብ ጨዋታውን ነሐሴ 29 ቀን ከግብፅ አቻው ጋር በካይሮ የሚያደርግ ይሆናል፡፡

ጊዜያዊ አሠልጣኞቹ ከተለያዩ ክለቦች ተጫዋቾችን መልምለው ይፋ ማድረጋቸውን ተከትሎ፣ ብሔራዊ ቡድኑ መደበኛ ዝግጅቱን የጀመረ ሲሆን፣ በተለይ ከአጥቂ ምርጫ ጋር በተያያዘ ቅሬታዎች ሲሰሙ ነበር፡፡

ይህም በቡድኑ ውስጥ ግብ ማስቆጠር የሚችል አጥቂ አለመኖሩ ተነስቷል፡፡ ጊዜያዊ አሠልጣኙ ስማቸው ይፋ ካደረጓቸው የፊት መስመር ተጫዋቾች ውስጥ አንድም ልምድ ያለው አጥቂ አለመኖሩ ተጠቅሷል፡፡

በምርጫው በደቡብ አፍሪካ ለሚገኘው ማሜሎዲ ሰንዳውንስ እግር ኳስ ክለብ የሚጫወተው፣ አቡበከር ናስር በጉዳት ምክንያት በዝርዝር ውስጥ መካተት አለመቻሉ ተጠቅሷል፡፡ ሌላው በካሜሮን አፍሪካ ዋንጫ እንዲሁም በቻን የማጣሪያ ጨዋታ ጥሩ እንቅስቃሴ ሲያደርግ የነበረው ዳዋ ሆጤሳ በዝርዝር ውስጥ አለመኖሩ የቡድኑን የፊት መስመር ቦታ ሥጋት ውስጥ ከቷል፡፡

በሌላ በኩል የብሔራዊ ቡድኑ አጥቂ ጌታነህ ራሱን ከብሔራዊ ቡድኑ ራሱን ማግለሉን ተከትሎና እሱን የሚተካ ሌላ ተጫዋች ባለመኖሩ ዋሊያዎቹ ግብ የሚያስቆጥርላቸው ተጫዋች ዕጦት ተጋልጠዋል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በምድቡ ሦስተኛና አራተኛ ጨዋታ ጊኒን ሲገጥም ለውጤት ማጣት ዋነኛ ምክንያት ተደርጎ የተጠቀሰው ግብ የሚያስቆጥር አጥቂ አለመኖሩ ነው፡፡

በአንፃሩ ጊዜያዊ አሠልጣኞቹ በአምስተኛው የምድብ ጨዋታ እንዲካተት ከጌታነህ ከበደ ጋር ውይይት ማድረግ ቢችሉም ተጫዋቹ ጥሪውን ሳይቀበለው መቅረቱ ተሰምቷል፡፡

ተጫዋቹ በፕሪሚየር ሊጉ ስኬታማ ጊዜ እያሳለፈ በመገኘቱ ብሔራዊ ቡድኑ፣ ያለበት ክፍተት ሊሞላ እንደሚችል ቢታመንም፣ በአንፃሩ ጌታነህ ወደ ቡድኑ ለመመለስ ዝግጁ አለመሆኑን በመጥቀስ ሙከራው ሳይሳካ መቅረቱ ተጠቁሟል፡፡

በአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ በምድብ አራት ከግብፅ፣ ከጊኒና ከማላዊ ጋር የተደለደሉት ዋሊያዎቹ በምድቡ ጥሩ ጊዜ እያሳለፉ አይደለም፡፡ ዋሊያዎቹ በምድቡ ካደረጉት አራት ጨዋታ በሦስቱ ተሸንፈው፣ አንድ ጨዋታ ብቻ አሸንፈው በሦስት ነጥብ አራተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል፡፡

ብሔራዊ ቡድኑ ከጨዋታ ጨዋታ መሻሻል እያሳየ ይመጣል የሚል ግምት ቢኖርም በተቃራኒ እያሽቆለቆለ ሄዷል፡፡

ለብሔራዊ ቡድኑ ወጥ አቋም ያለማሳየትና እያሽቆለቆለ መሄድ የተለያዩ ጉዳዮች እንደ ችግር ሲነሱ ቢደመጥም፣ መሠረታዊና በርካታ ውስብሰብ ችግሮች መኖራቸው ይነገራል፡፡

ዋሊያዎቹን ለማሠልጠን ከሁለት ዓመት በፊት የተረከቡት ውበቱ አባተ በአጠቃላይ 35 ጨዋታዎች ያደረጉ ሲሆን፣ አሥሩ ጨዋታዎች የአቋም መለኪያ ናቸው፡፡

ከእነዚህም 25 የውድድር መርሐ ግብር ጨዋታዎች፣ ዋሊያዎቹ ማሸነፍ የቻሉት 6 ጨዋታዎችን ብቻ ነው፡፡ ጠባብ ዕድል ይዘው የምድባቸውን ሁለት ቀሪ ጨዋታዎችን የሚያደርጉት የዋሊያዎቹ ስብሰብ በቀጣይ በርካታ የቤት ሥራዎች ይጠብቃቸዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የአማራ ክልል ወቅታዊ ሁኔታ

እሑድ ጠዋት መስከረም 13 ቀን 2016 ዓ.ም. የፋኖ ታጣቂዎች...

ብሔራዊ ባንክ ለተመረጡ አልሚዎች የውጭ አካውንት እንዲከፍቱ ለመጀመሪያ ጊዜ የፈቀደበት መመርያና ዝርዝሮቹ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ አጠቃቀምንና ተያያዥነት ያላቸው ጉዳዮችን...

እነ ሰበብ ደርዳሪዎች!

ከሜክሲኮ ወደ ዓለም ባንክ ልንጓዝ ነው። ሾፌርና ወያላ ጎማ...