Tuesday, October 3, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየደም እጥረት በክረምቱ ሊከሰት ስለሚችል ኅብረተሰቡ ደም እንዲለግስ ጥሪ ቀረበ

የደም እጥረት በክረምቱ ሊከሰት ስለሚችል ኅብረተሰቡ ደም እንዲለግስ ጥሪ ቀረበ

ቀን:

በየዓመቱ በክረምት ወራት ትምህርት ቤቶችና ዩኒቨርሲቲዎች ዝግ ሲሆኑ የደም ለጋሾቹ ቁጥር አነስተኛ ስለሚሆን፣ ኅብረተሰቡ ደም በመለገስ ኃላፊነቱን እንዲወጣ  የኢትዮጵያ ደምና ኅብረ ህዋስ ባንክ አገልግሎት ጥሪ አቀረበ፡፡

የደምና ኅብረ ህዋስ ባንክ አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀብታሙ ታዬ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ በአገር አቀፍ ደረጃ በመደበኛነት በየሦስት ወሩ ደም የሚለግሱ ወገኖች ቁጥር አነስተኛ በመሆኑ በክረምት ወቅት ትምህርት ቤቶች ሲዘጉ የደም እጥረት ችግር ይከሰታል፡፡

አብዛኛውን ጊዜ በክረምትና በሃይማኖት ተቋማት የፆም ወቅት የደም ለጋሾች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ ዝቅ እንደሚልና ችግሩም በተደጋጋሚ ይታያል፡፡

በ2014 በጀት ዓመት በክረምት ወቅት ተቋሙ 120 ሺሕ ሊትር ደም ለመሰብሰብ አቅዶ፣ 80 ሺሕ ሊትር ደም ብቻ መሰብሰቡን የሚናገሩት አቶ ሀብታሙ፣ ዘንድሮ እንደ ዓምናው ዓይነት ችግር እንዳይታይ የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሐ ግብር ለማከናወን እየተሠራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ከዚሁ ጎን ለጎን አንድ ሰው 450 ሚሊ ሊትር ደም ከለገሰ በኋላ ሦስት ወይም አራት የደም ተዋፅዖዎች እንደሚወጡ፣ ከእነዚህ ውስጥ ‹ፕሌትሌት› የሚባለው የደም ተዋፅዖ አብዛኛውን ጊዜ የካንሰር ሕሙማን በስፋት የሚጠቀሙበት የደም ዓይነት መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በሌላ በኩል ‹ኦ ኔጌቲቭ› የሚባል የደም ዓይነት ከብዙ ሰዎች ስለማይኖር የለጋሾች ቁጥር አነስተኛ መሆኑን፣ ይሄም የደም ዓይነት ለሁሉም ሰዎች የሚሰጥ ስለሆነ የዚህ የደም ዓይነት እጥረት በተለየ ሁኔታ እንደሚገጥማቸው አብራርተዋል፡፡

‹ኦ ኔጌቲቭ› የደም ዓይነት በጦርነት ወቅት፣ በወሊድ ምክንያት ብዙ ደም ለሚፈሳቸው እናቶች፣ ሌሎች ጉዳት ላጋጠማቸው ወገኖች የደም ዓይነቱ እንደሚያገለግልና ይህንንም ደም በተፈለገው ልክ ለመሰብሰብ ችግር ውስጥ እንደሚገቡ ጠቁመዋል፡፡

በ2015 በጀት ዓመትም 490 ሺሕ ሌትር ደም ለመሰብሰብ ታቅዶ እስካሁን 320 ሺሕ ደም መሰብሰቡንና ይሄ ዘንድሮ ከታቀደው አንፃር ሲታይ ጉድለት መኖሩን አቶ ሀብታሙ አስረድተዋል፡፡

ዘንድሮ ትግራይ ክልልን ሳይጨምር ደም ማሰባሰቡ የተከናወነ ሲሆን በደቡብ ምዕራብ፣ ጋምቤላ፣ ወለጋ፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝና በአብዛኛው የደቡብ ቦታዎች የሚገኙ የደም ባንኮች አፈጻጸም ዝቅተኛ በመሆኑ የታቀደውን ያህል ለመሰብሰብ አልተቻለም ብለዋል፡፡

የዘንድሮ የዓለም የደም ለጋሾች ቀንን ‹‹ደም ይለግሱ ሕይወትን ዘወትር ያጋሩ›› በሚል መሪ ቃል ሰኔ 7 ቀን 2015 ዓ.ም. በአሶሳ ከተማ ለማክበር ቅድመ ዝግጅት መደረጉን ተገልጿል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ተመድንና ዓለም አቀፋዊ ሕግን ከእነ አሜሪካ አድራጊ ፈጣሪነት እናድን!

በገነት ዓለሙ በእኔ የተማሪነት፣ የመጀመርያ ደረጃ ተማሪነት ጊዜ፣ የመዝሙር ትምህርት...

የሰላም ዕጦትና የኢኮኖሚው መንገራገጭ አንድምታ

በንጉሥ ወዳጅነው ፍራንክ ቲስትልዌይት የተባሉ አሜሪካዊ ጸሐፊ ‹‹The Great Experiment...

ድህነት የሀብት ዕጦት ሳይሆን ያለውን በአግባቡ ለመጠቀም አለመቻል ነው

በአንድነት ኃይሉ ድህነት ላይ አልተግባባንም፡፡ ብንግባባ ኖሮ ትናንትም ምክንያት ዛሬም...